Get Mystery Box with random crypto!

ባለሃብቱ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር አበረከቱ ! ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ | ሰበር ዜና ETHIOPIA

ባለሃብቱ ለወጣቶች ስራ ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር አበረከቱ !

ኢትዮጵያዊው ባለሀብት አቶ በላይነህ ክንዴ ፤ #ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰማ።

አቶ በላይነህ ለሰከላ ወረዳ ወጣቶች ነው የስራ ዕድል መፍጠሪያ የሚውል 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉት፤ ድጋፉንም ሰከላ ወረዳ ግሽ ዓባይ ላይ ተገኝተው ለወጣቶቹ አስረክበዋል።

ባለሀብቱ አቶ በላይነህ ክንዴ በርክክብ ፕሮግራሙ ላይ ለወጣቶቹ የህይወት ተሞክሯቸውን እና ምክር አካፍለዋል።

አቶ በላይናህ ክንዴ በርክክብ መድረኩ ላይ ፦

" መንግስት ብቻ ሳይሆን ባለሀብቱ #ለወጣቶች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ትልቅ ሀላፊነት አለበት።

ወጣቶቻችን የስራ ዕድል ካልተፈጠረላቸው እና ሀብት ማፍራት ካልቻሉ የባለሀብቱ ዕድገትም ይገታል። ስለሆነም ለወጣቶቻችን የስራ ዕድል በመፍጠር ተያይዘን ማደግና ሀገር መለወጥ ይገባናል።

ለእኛ ሀብታችን ወጣቶቻችን ናቸው ፤ ወጣቶች በገቢ እራሳቸውን ችለው ለቤተሰብና ለሀገር እንዲተርፉ እንደ ዜጋ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል።

ወጣቶችም የትኛውንም ስራ ሳይንቁ መስራት አለባቸው። እኔ ከዝቅተኛ ስራ እና ከትንሽ ገንዘብ ተነስቼ ነው እራሴን እየለወጥኩ የመጣሁት።

ይህ በድጋፍ የተሰጠ 10 ሚሊዮን ብር በተዘዋዋሪ ብድር መልክ ነው።

ወጣቶች አሁን የወሰዳችሁትን ገንዘብ ቁምነገር ላይ በማዋል አቅም እንድትፈጥሩ እና ብድሩን በመመለስ ለሌሎች ወንድሞቻችሁ የስራ ዕድል መፍጠሪያ እንዲሆን መስራት አለባችሁ " ሲሉ ተናግረዋል። (APP)