Get Mystery Box with random crypto!

#ፓስፖርት የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፥ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኦንላይን ላይ | የፓስፖርት አገልግሎት (passport service)

#ፓስፖርት

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፥ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኦንላይን ላይ ቀጠሮ አስይዘው በተለያየ ምክንያት የቀጠሮ ጊዜ ያለፈባቸው ተገልጋዮች ከዚህን ቀደም በቅጣት በማንኛውም የስራ ቀን አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን ገልጾ ከፊታችን ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ግን በስራ ሰዓት አርብ አርብ ቀን ብቻ በቅጣት አገልገሎት የሚያገኙ መሆኑን አሳውቋል።

ተገልጋዮች ይህን አውቀው በዕለቱ ብቻ እንዲገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪም ፦ የቀጠሮ ጊዜያቸው ከ1 ወር በላይ ያለፈባቸው ተገልጋዮች #በኦንላይን ላይ ዳግም ማመልከት እንዳለባቸው ገልጿል።

#ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም " የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ " ይባል የነበረው ተቋም ስያሜው የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም መሠረት " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት / Immigration and citizenship service " በሚል ስያሜ ተቀይሯል።