Get Mystery Box with random crypto!

ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት | የፓስፖርት አገልግሎት (passport service)

ኤጀንሲው የሰነድ ማረጋገጫ ማህተም አሰራርን ቀየረ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ እየተበራከተ የመጣውን ሰነድ አስመስሎ የመስራት ወንጀል ለመቀነስ ኤጀንሲው በሚሰጣቸው የልደት፣ የጋብቻ ፣ የፍቺ ፣ የያላገባ እንዲሁም ሌሎች ማስረጃዎች አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረውን የማረጋገጫ አሰራር በዘመናዊ አሰራር በመተካት ፎርጀሪ እያደረሰ ያለውን ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳት ለመቀነስ የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ተቋሙ በዋና መስሪያ ቤት የሚሰጠውን ለፖስፖርት አገልግሎት፣ ለውጭ ሃገራት የቪሳ ጥያቄ ፣ ለተለያዩ የውጭ እና የሃገር ውስጥ ጉዳዮች የሚውሉ ማስረጃዎች የሚረጋገጥበትን የቀድሞ የማህተም አሰራር በማስቀረት በውጭ ሃገር አሰርቶ ባስገባው ዘመናዊ የሆሎግራም ማረጋገጫ አሰራር ከዛሬ ህዳር 13 2014 ዓ.ም ጀምሮ በመተካት ተግባራዊ ያደርጋል።

ይህ አሰራር ከፖስፖርት እና ከውጭ ጉዳዮች ጋር ተያይዞ በየቦታው ተመሳስሎ በመስራት ለማለፍ የሚሞከሩ ሌብነቶች ኤጀንሲውን እንዳያልፉ እገዛ የሚያደርግ እንደሚሆን ታምኖበታል።

በተያዘው በጀት ተቋሙ የሚሰጣቸውን ሰርተፍኬቶች የደህንነት ደረጃ ከፍ ለማድረግ አዲስ የPersonalization ቴክኖሎጂ ባላቸው ፕሪንተሮች ለመተካት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ምንጭ፦ ወ/ኩ/ም/መ/ኤጀንሲ