Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Orthodoxs Daily

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxs — Ethiopian Orthodoxs Daily E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiopianorthodoxs — Ethiopian Orthodoxs Daily
የሰርጥ አድራሻ: @ethiopianorthodoxs
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.31K
የሰርጥ መግለጫ

በቤተ ክርስቲያናችን በየቀኑ የሚታሰብ ቅዱሳን፤ የመፅሐፍ ቅዱስ ምንባባት ፤ ብሂለ አበው እና አስተማሪ የሆኑ መንፈሳዊ ፅሁፎች ያገኙበታል::Share https://t.me/ethiopianorthodoxs //like page on facebook fb.me/ethiopianorthodxs ለሀሳብ አስተያየትዎ
@Yakob520

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-12 07:56:06 #የዓርብ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ

ድንግል ሆይ! የደናግል ኹሉ መመኪያቸው አንቺ ነሽ፡፡ ከእናንተ መካከል “መመኪያነቷ እንዴት ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡-
፩ኛ) ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንዲህ ሲል ይመልስልናል፡- “ወበከመ አውፅአ ብእሲ ብእሲተ ዘእንበለ ብእሲት ከማሁ አውፅአት ብእሲት ብእሴ ዘእንበለ ብእሲ ወሀሎ ዕዳ ላዕለ ትዝምደ አንስት፤ ወበእንተዝ ኮነት ፈዳዪተ ዕዳሃ ለሔዋን - ለወንዶች የሚከፈል ዕዳ በሴቶች ላይ ነበረ፤ ያለ እናት ሔዋን ተገኝታ ነበርና፡፡ ስለዚህም የሔዋንን ብድራት ለአዳም ትከፍለው ዘንድ ድንግል ያለ ዘርዐ ብእሲ (ያለ ወንድ ዘር) ክርስቶስን ወለደችው፡፡ አዳም ያለ እናት ሔዋንን ስላስገኘ እንዳይመካ ድንግል ያለ አባት ክርስቶስን ወለደችው፡፡ ድንቅ በሚኾን አንድነት ይህ አንድ የፍጥረት እኩልነት ይታወቅ ዘንድ” /ሃይ.አበ.፷፮፥፳፱/፤
፪ኛ) ቀድሞ ወንዶች ሴቶችን በእናንተ ምክንያት ከገነት ወጣን እያሉ ርስት አያካፍሏቸውም ነበር፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “ብእሲ ወብእሲት አሐደ እሙንቱ በክርስቶስ - ወንድም ሴትም የለም፤ ኹላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና” ብሎ እስኪያስተምር ድረስ /ገላ.፫፡፳፰/ በሔዋን ምክንያት ከገነት ብትወጡ በእመቤታችን ምክንያት ገነት መንግሥተ ሰማያት ገብታችሁ የለምን? ብለው የሚመኩ ኹነዋልና፤
፫ኛ) ደግሞ ለደናግላን አስበ ድንግልናቸውን (የድንግልናቸውን ዋጋ) ስለምታሰጣቸው ሊቁ “ምክሆን ለደናግል” ብሏታል፡፡

ቅድመ ዓለም የነበረ እርሱ ሰው ኹኗልና (ካንቺ ተወልዷልና) የእኛን ሥጋ ነሥቶ የርሱን ሕይወት ሰጥቶ ከርሱ ጋራ አስተካከለን፡፡ በቸርነቱ ብዛት እንድንመስለው አደረገን /ፊል.፫፥፲-፲፩/፡፡ ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ፡፡ ክብር የክብር ክብር ካላቸው ከብዙ ሴቶች አንቺ ትበልጫለሽ /ሉቃ.፩፥፳፰/፡፡ ንጉሥ በከተማው እንዲኖር ዘጠኝ ወር ካምስት ቀን ማኅፀንሽን ዓለም አንድርጎ ኖሮብሽልና አምላክን የወለድሽ ድንግል ማርያም ሆይ! ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በኪሩቤል በሱራፌል አድሮ የሚኖረው እርሱን በማኽል እጅሽ ይዘሽዋልና ልዑል እግዚአብሔር የከተመብሽ ረቂቅ ከተማ ነሽ፡፡ በቸርነቱ ብዛት ፍጥረቱን ኹሉ በዝናም አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ አንድም ለሰውን (ለመንፈሳውያን) ኹሉ ሥጋውን ደሙን ሰጥቶ የሚመግበው እርሱ ጡትሽን ይዞ ጠባ፡፡ ይኸውም ፈጣሪያችን መድኃኒታችን ነው፡፡ እንሰግድለት እናመስግነውም ዘንድ በሐዲስ ተፈጥሮ በጥንተ ተፈጥሮ ፈጥሮናልና ለዘለዓለሙ ይጠብቀናል /ዮሐ.፮፥፴፯/፡፡ ሰጊድ (አምልኮ) ከሚገባው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፬. ድንግል ማርያም ዕፍረተ ምዑዝ (መዓዛው የጣፈጠ) የተባለ ጌታችንን የወለደች ሙዳየ ዕፍረት (የሽቱ መኖርያ) /፩ኛ ሳሙ.፲፥፩ አንድምታው/፤ ዳግመኛም የማየ ሕይወት (የሕይወት ውኃ የክርስቶስ) ምንጭ ናት /መኃ. ፬፥፲፪ አንድምታው/፡፡ የማኅፀኗ ፍሬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ኹሉ አድኗልና፡፡ ከእኛ መርገመ ሥጋን መርገመ ነፍስን አጠፋልን፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ፡- “በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ኹሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና” እንዲል /ቈላ.፩፡፲፱-፳/ በመካከል ኾኖ በመስቀሉ አስታረቀን፡፡ ልዩ በኾነ ትንሣኤውም ሰውን ዳግመኛ ወደ ገነት መለሰው፡፡ ከእናንተ መካከል፡- “ልዩ በኾነ ትንሣኤ ሲል ምን ማለቱ ነው?” ብሎ የሚጠይቅ ሊኖር ይችላል፡፡ እኛም እንዲህ ብለን እንመልስለታለን፡- ከእነ አልዓዛር ትንሣኤ የተለየ መኾኑን ለማሳየት ነው፡፡ ምክንያቱም፡-
፩ኛ) እነ አልዓዛር አስነሺ ይሻሉ፤ እርሱ ግን “ላኖራት ሥልጣን አለኝ፤ ደግሞም ላነሣት ሥልጣን አለኝ” ብሎ እንደተናገረ /ዮሐ.፲፥፲፰/ የተነሣው በገዛ ሥልጣኑ ነውና፡፡ በተለያየ ሥፍራ “አብ አንሥኦ (አብ አስነሣው)፤ መንፈስ ቅዱስ አንሥኦ (መንፈስ ቅዱስ አስነሣው)” ቢልም አንድ ነው፡፡ ምክንያቱም ዕሪናቸውን መናገር ነውና፡፡
፪ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ በብሉይ ሥጋ ነው፤ የእርሱ ግን በሐዲስ ሥጋ ነው፡፡
፫ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ሞትን ያስከትላል፤ የእርሱ ግን ሞትን አያስከትልም፡፡
፬ኛ) የእነ አልዓዛር ትንሣኤ ትንሣኤ ዘጉባኤን ይጠብቃል፤ የእርሱ ግን አይጠብቅምና፡፡

አዳምን ዳግመኛ ወደ ገነት ከመለሰ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡

፭. አንዳንድ ተረፈ ንስጥሮሳውያን እንደሚሉት ንጽሕት ድንግል ማርያም ላቲ ስብሐትና “ወላዲተ ሰብእ” አይደለችም፤ የታመነች አምላክን የወለደች ናት እንጂ፡፡ የመናፍቃን መዶሻ የተባለው፣ በተለይም የቅድስት ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክነት የካደውን ንስጥሮስን የረታው ቅዱስ ቄርሎስ እሳተ መለኮት አምላክን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማኅፀኗ የተሸከመች፣ በጀርባዋ ያዘለች፣ በዝናብ አብቅሎ በፀሐይ አብስሎ የፈጠረውን ፍጥረት የሚመግበው አማኑኤልን የድንግልና ጡቶቿን ወተት የመገበችውን የወላዲተ አምላክን ክብር ያልተረዱትን ንስጥሮሳውያን መናፍቃንን ሲወቅስ “ወለዛቲ እንተ መጠነዝ ዐባይ ጾረት መለኮተ እፎ ይከልእዋ እምክብራ ለወላዲተ አምላክ ወላዲተ አምላክኬ ቅድስት ድንግል - ይኸንን ያኽል ታላቅ ኾና መለኮትን የተሸከመችቱን የአምላክ እናት ክብርን እንደምን ይነፍጓታል፤ ይከለክሏታል፡፡ የአምላክ እናት ማለት ድንግል ማርያም ናታ” በማለት የተሰጣትን ክብር በማድነቅ አስተምሯል /ተረፈ ቄርሎስ/፡፡

እንዲህም ስለኾነ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት፡፡ የዚህ ዓለም ሰዎች አማልዱኝ ቢባሉ ነገር አጽንተው ይመለሳሉ፤ እርሷ ግን “ማእምንት ሰአሊተ ምሕረት - የታመነች የምሕረት አማላጅ ናት” /ዮሐ.፪፥፩-፲፩/፡፡ ሰአሊተ ምሕረት ሆይ! ኃጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ከልጅሽ ዘንድ አማልጅን፡፡ ኃጢአታችንን ከሚያስተሠርይልን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡


ሊንኩን ተጭነው ሙሉውን ያንብቡ

https://mekrez.blogspot.com/2013/08/blog-post_1585.html?m=1

@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
@beteafework @beteafework
1.5K views04:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 10:30:18
1.4K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-09 07:50:51 ፨፨ አንቺ ባትኖሪልኝ፨፨
የመኖሬ ትርጉም ቅኔው ሲጠፋብኝ፣
የህይወቴ መፅሐፍ ገፁ ሲምታታብኝ፣
የኔነቴ ዋጋ ባዶ ሲሆንብኝ፣
የሀጢያት ሐረግ ሲንጠላጠልብኝ፣
ሙቼ መራመዴ ለኔ ሲታወቀኝ፣
ምን ይውጠኝ ነበር አንቺ ባትኖሪልኝ?
አልቅሼ ስነግርሽ አለሁሽ ባትዪኝ፣
የመዳንን መድህን ልዑል ባትወልጂልኝ፣
በምልጃ ፀሎትሽ ቤቴ ባይሞላልኝ፣
በይቅር ባይነትሽ ኑሮ ባይቀናልኝ።
ማን ያስበኝ ነበር አንቺ ባታስቢኝ?
ሀጥያት ተፀይፈሽ ፊት ያላዞርሽብኝ፣
ብርሀንን ወልደሽ ፀሀይ የሆንሽልኝ፣
ለውለታሽ ገላጭ ምንም ቃላት የለኝ፣
አማላጇ እናቴ ሁሌም ክበሪልኝ፣
ድንግል እመቤቴ ከፍ ከፍ በይልኝ።
@ethiopianorthodoxs
@ethiopianorthodoxs
1.8K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:48:29 የጾም ትርጉም በቤተ ክርስቲያን

የቤተ ክርስቲያናችን የሥርዓት መድብል የሆነው ፍትሐ ነገሥት ጾምን እንዲህ ይተረጉመዋል፡-

ጾምስ በታወቀው ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከልበት መከልከል ነው፡፡

አንድም ጾም ሰውን ከምግብ መከልከል ነው፡፡

ይህም ኃጢአቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ፈቅዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥጋን ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ማዘጋጀት ማብቃት ነው፡፡
ፍት.ነገ.ፍት. መ. አንቀጽ15፣564

በዚህ መሠረት ጾም ማለት ከጥሉላተ መባልዕት /ሥጋ ፣ ቅቤ፣ ወተት፣ እንቁላል እንዲሁም የአልኮል መጠጦች/ መታቀብ ነው፡፡

ጾም ከክፉ ሐሳብ፣ ከክፉ ሥራ ማሰብም መራቅም ነው።

ጾም እግርና እጅን፣ ልብንና ሕሊናን ከመጥፎ ቦታዎች ማቀብ /ወደ መጠጥ ቤት፣ ጭፈረና ዘፋኝ ቤት፣ ጥንቆላና ባዕድ አምልኮ ከመትወስድ መንገድ የምትከለክል ናት።

ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው፡፡

ጾም ለፈቃደ ሥጋም መንፈሳዊ ልጓም ነው፡፡

ጾም ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለመልምበት ስንቅ ነው፡፡

ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ናት።

ጾም ጸጋ እግዚአብሔርን የምታሰጥ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው መገለጫቸው፣ የጸሎት ምክንያት /እናት/፣ የእንባ መገኛ ምንጭ፣ አርምሞን የምታስተምር፣ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፣ ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትኅትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት፡፡
@ethiopianorthodoxs
2.1K views05:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 09:04:27 የነሐሴ ፩ ቅዳሴ ምንባብ
(የዮሐንስ ወንጌል ምዕ. 19)
----------
28፤ ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ። ተጠማሁ አለ።

29፤ በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት።

30፤ ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ። ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።

31፤ አይሁድም የማዘጋጀት ቀን ስለ ሆነ ያ ሰንበት ትልቅ ነበረና ሥጋቸው በሰንበት በመስቀል ላይ እንዳይኖር፥ ጭናቸውን ሰብረው እንዲያወርዱአቸው ጲላጦስን ለመኑት።

32፤ ጭፍሮችም መጥተው የፊተኛውን ጭን ከእርሱም ጋር የተሰቀለውን የሌላውን ጭን ሰበሩ፤

33፤ ወደ ኢየሱስ በመጡ ጊዜ ግን እርሱ ፈጽሞ እንደ ሞተ አይተው ጭኑን አልሰበሩም፤

34፤ ነገር ግን ከጭፍሮች አንዱ ጎኑን በጦር ወጋው፤ ወዲያውም ደምና ውኃ ወጣ።

35፤ ያየውም መስክሮአል፤ ምስክሩም እውነት ነው፤ እናንተም ደግሞ ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነት እንዲናገር ያውቃል።

36፤ ይህ የሆነ። ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመጽሐፉ ቃል እንዲፈጸም ነው።

37፤ ደግሞም ሌላው መጽሐፍ። የወጉትን ያዩታል ይላል።

38፤ ከዚህም በኋላ አይሁድን ስለ ፈራ በስውር የኢየሱስ ደቀ መዝሙር የነበረ የአርማትያስ ዮሴፍ የኢየሱስን ሥጋ ሊወስድ ጲላጦስን ለመነ፤ ጲላጦስም ፈቀደለት። ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን ሥጋ ወሰደ።

39፤ ደግሞም አስቀድሞ በሌሊት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረ ኒቆዲሞስ መቶ ንጥር የሚያህል የከርቤና የእሬት ቅልቅል ይዞ መጣ።

40፤ የኢየሱስንም ሥጋ ወስደው እንደ አይሁድ አገናነዝ ልማድ ከሽቱ ጋር በተልባ እግር ልብስ ከፈኑት።

41፤ በተሰቀለበትም ስፍራ አትክልት ነበረ፥ በአትክልቱም ማንም ገና ያልተቀበረበት አዲስ መቃብር ነበረ።

42፤ ስለዚህ መቃብሩ ቅርብ ነበረና ስለ አይሁድ ማዘጋጀት ቀን ኢየሱስን በዚያ አኖሩት።
@ethiopianorthodoxs
1.5K views06:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-05 07:22:51 የዕለቱ መልዕክት
(ገላ 5 )
------------
14 ሕግ ሁሉ በአንድ ቃል ይፈጸማልና፥ እርሱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የሚል ነው።

15 ነገር ግን እርስ በርሳችሁ ብትነካከሱና ብትበላሉ እርስ በርሳችሁ እንዳትጠፋፉ ተጠንቀቁ።

16 ነገር ግን እላለሁ፥ በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ።

17 ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም።

18 በመንፈስ ብትመሩ ግን ከሕግ በታች አይደላችሁም።

19 የሥጋ ሥራም የተገለጠ ነው እርሱም ዝሙት፥ ርኵሰት፥ መዳራት፥

20 ጣዖትን ማምለክ፥ ምዋርት፥ ጥል፥ ክርክር፥ ቅንዓት፥ ቁጣ፥ አድመኛነት፥ መለያየት፥ መናፍቅነት፥

21 ምቀኝነት፥ መግደል፥ ስካር፥ ዘፋኝነት፥ ይህንም የሚመስል ነው። አስቀድሜም እንዳልሁ፥ እንደዚህ ያሉትን የሚያደርጉ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።

22 የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።

23 እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።

24 የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
@ethiopianorthodoxs
1.7K views04:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 07:48:30 ሴት:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ ሃያ ሰባት በዚህች ቀን የአዳም ልጅም ሴት ያረፈበት ነው::

ሴትም 205 ዓመት ኖረ ሔኖስንም ወለደው:: ሔኖስንም ከወለደ በኋላ 709 ዓመት ኖረ ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ወለደ:: መላ ዕድሜው 912 ዓመት ሆነ በሰላምም አረፈ::

እግዚአብሔር አምላክ የእኛንም የንስሐ ዕድሜ እንዲያረዝምልን በጊዜውም ያለ ጊዜውም በሃይማኖት እንዲያጸናን ከእግዚአብሔር ጋር መኖር አለብን::

አጥተንም አግኝተንም: ታመንም በጤና ሁነን:.በወጣትነታችንም በሽምግልና ወራትም ከእርሱ ጋር በመኖር እርሱን በመፍራት ሕጉን በመጠበቅ በቸርነቱ እቅፍ ውስጥ በረድኤት እንዲያኖረን ያለፈ ኃጢአታችንን ተናዘን ለመጪው ከክፋ ሥራ እንዲጠብቀን የበደልነውን ክሰን የቀማነውን መልሰን ቀሪ ዘመናችንን እንዲባርክልን መጸለይ አለብን::

በተለይ መጪውንም የፍልሰታን ጾም አበው እንደተጠቀሙባት ከፈቃደ ሥጋ ርቀን: ጾመን: ጸልየን: ሰግደን: መጽውተን መልካምና በጎ ነገራችን በቀሪው የዕድሜ ዘመናችን እንዲከተለን በዚህች ጾም እንድንጠቀምበት ፈጣሪ ይርዳን ያበርታን::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳኑ አባቶች ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
1.7K views04:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 08:58:16 ተክለ አዶናይ:-
አንድ አማልክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬ ሐምሌ 24 በዚህች ቀን የደብረ ሊባኖሱ አባ ተክለ አዶናይ መታሰቢያቸው ነው::

የብፁዕ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት ስማቸው በዝቶ የሚጠራበት ገድላቸው የሚነበብበት የሚዘከርበት ዕለት ነው። በረከታቸው ይደርብን።

እኚም ተክለ አዶናይ የጻድቁ ልጅ ናቸው።

ትውልዳቸው ጎጃም ጎንጅ ጽላሎ ነው:: በዜና ማርቆስ ገዳም ምንኵስናን የተቀበሉ ሲሆን ጻድቁ አባታችን አባ ተክለ ሃይማኖት ከሾሙአቸው 33 አበው አንዱ ናቸው::

እስከ ዕድሜአቸው ፍጻሜ ድረስ በጸሎት የኖሩ አባት ሲሆኑ፤ ነብር ምግብ ያቀብላቸው፣ ሚዳቆ ውኃ ትቀዳላቸው የነበሩ ታላቅ ባሕታዊ ናቸው::

የተክለ ሃይማኖት ልጅ የተክለ ሃይማኖትን ሥራ ነውና የሚሠራው ክብር ይግባውና ፈጣሪ፤ ዙረው አስተምረዋል፣ በአጋንንት አሽክላ የተተበተበውን ሕዝብ አላቀው በቀናች ሃይማኖት አጽንተዋል::

ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅማትን ሥርዓት ሁሉ አስከብረው ከብረውበታል።

የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆነ ተገልጋዩ ንጽሕናና ቅድስናን ቢከተል ራሱን ሌሎችንም ያድናል እያሉ ይሰብካሉ ያስተምራሉ።

ለቤተ ክርስቲያን ምእመናን መልካም ቸር ጠባቂ በመሆን አገልግለዋል፤ በጾምና በጸሎት የበረቱ፣ በገድል በትሩፋት የተቀጠቀጡ፣ ዲንጋይ ተንተርሰው፣ ጤዛ ልሰው ለቤተ ክርስቲያን አምዳ ድዳ በመሆን አገልግለዋል::

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
1.8K views05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-29 08:04:50 አቡነ ጴጥሮስ:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ዛሬ ሐምሌ 22 በዚህች ቀን ኢቲዮጲያዊው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት አረፉ::

የ20ኛው ክፍለ ዘመን ታላቅ ሰማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሰላሌ አውራጃ ፍቼ ከተማ ተወለዱ::

አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት እንደሚሞቱ አስቀድመው መምህራቸው በትንቢት ነግረዋቸው ነበር።

"አለቃ ተጠምቀ" የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋራ አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው "ኃይለ ማርያም አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚህች ሀገር ይሰለጥናል። ታዲያ ያኔ አንተ ለነፍስህ ሳትሰቀቅ በሰማዕትነት እለፍ፤ ሰማዕትነት ክፍልህ ነው፣ አደራ" ብለዋቸው ነበር። ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሰማዕትነት ለማረፍ በቅተዋል።

ብፁዕ አባታችን የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መምህር ኃይለ ማርያም ይባላሉ ነበር።

በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረ ሊባኖስ በመውሰድ በሃይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርጎቸዋል።

የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔ አውድማ ጎጃም በመሔድ በዋሽራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈጽመው መምህር ሆነዋል።

የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር ሔደው ተምረዋል። ወሎ ቦሩ ሜዳ ከሊቁ አካለ ወልድ የብሉያትን፤ ሐዲሳትንና የሊቃውንት ትምህርት በሚገባ አሒዱ።

በ1900 ዓ.ም ወሎ አማራ ሳይንት ሔደው ምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለ9 ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ።

በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረ ሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስና ፈጸሙ። በመምህርነት ተሾመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ለ6ዓመታት፤ በ1916 ዓ.ም በዝዋይ ደብረ ጽዮን ቅድስት ገዳም ለ3ዓመታት፤ በ1919 ዓ.ም አ.አ ማርቆስ በመምህርነትና የዓፄ ኃይለ ሥላሴ መምህረ ንስሐ ሆኑ።

ኢትዮጵያ የራሷን ጳጳሳት ስትሾም በስነ ምግባር ከተመሰከረላቸውና ከተመረጡ ጳጳሳት አንዱ ሆነው ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ።

ብፁዕ አባታችን "አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምሥራቅ ኢትዮጵያዊ ተላዌ አሠሩ ለአቡነ ኢየሱስ ሞዐ" ተብለው መንዝና ወሎ አገረ ስብከት ተሾሙ።

ቅዱስ አባታችን ቅድስት ቤተክርስቲያናችንና ቅድስት ሀገራችንን በጸሎታቸው፣ ሕዝቡን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነትን አውጆ ሕዝቡን በግፍ ይገድል ቤተ ክርስቲያንን ያቃጥል ጀመር።

በየገዳማቱ በርካታ ካህናትና መነኮሳት ተገደሉ፣ ብርቅዬ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች ተዘረፉ።

አቡነ ጴጥሮስ ይህን ግፍ በማየታቸው ከሀገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በጸሎታቸው ሊዋጉት ተነሡ።

አባታችን ዓፄ ኃይለ ሥላሴ በመከተል ወደ ማይጨው ሔደዋል። በዚያም በመርዝ የተደገፈ ጦርነትን ፋሺስት እያደረገ ሕዝቡን ሲገል ሥራዊቱን ሲበትን ተመለከቱ።

ወደ አ.አ ከተመለሡ በኋላ ደብረ ሊባኖስ ሔደው ለሀገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሠላሌ በሚገባ አስተምረዋል።

በደብረ ሊባኖስ ገዳም በጾምና በጸሎት ተጠምደው እግዚአብሔር የኢትዮጲያን ሕዝብ በምሕረቱ እንዲታደጋት እየተማጠኑ ወደፊት ለሚመጣባቸው ተጋድሎ መዘጋጀት ጀመሩ::


ወደ አ.አ በመመለስም ይህን ተግባራቸውን ይፈጽሙ ነበር። ጠላት በመላዋ ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎችን አባታችንን ይቃወሟቸው ይፈለጉም ጀመረ።

አባታችን ግን "የሀገሬ ሕዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ ባልፍ ይሻለኛል" ብለው ወሰኑ።

በግዜው የፋሽስት ኢጣልያ እንደራሴ የሆነው ራስ ኃይሉ በጥብቅ ይፈልጋቸው ያድናቸው ነበር።

እሱም ብፁዕ አባታችንን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አሳልፎ ሰጣቸው። ግራዚያኒን አጥብቆ ሲፈልጋቸው ነበርና ተደሰተ።

በኋላ ተይዘው ታሰሩ ሕዝቡንም ለፋሽሽት ለጣሊያን መንግስት እንዲገዛ ስበክ ተናገር ተባሉ።

ለዚህም መደለያ የተቀናጣ ቤት፣ ዘመናዊ መኪና፣ ከሮም መንግስት ዕውቅና ይሰጧታል ቢላቸው አሻፈረኝ አሉ።

ነገር ግን ሊገደሉ ሲፈረድባቸው በአደባባይ የእሳቸውን ፍርድ ለሚጠባበቀው ሕዝብ መስቀላቸውን አንስተው በ4 አቅጣጫ ባረኩ።

በፍርድ ወንበር ላይ የተቀመጠው ዳኛም አቡነ ጴጥሮስን " ሕዝቡን ቀስቅሰዋል ራሶም አምፀዋል ሌሎችም እንዲያምጹ አድርጎዋል" አላቸው።

ቀጥሎም "ካህናቱም ሆነ የቤተ ክህነት ባለስልጣናት ሊቀ ጳጳሱም አቡነ ቄርሎስ የጣሊያን ገዢነት አምነው አሜን ብለው ሲቀበሉ እርሶ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዋን አፈንጋጭ ሆኑ?" ሲል ጠየቃቸው።

ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ በቆራጥነት የሚከተለውን መለሱ፦

"አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው፤ ስለ ኢትዮጵያና ስለ ኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም፤ እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ ሕዝቤም ጭምር፤ ሓላፊነትም ያለብኝ የቤተ ክርስቲያን አባት ነኝ፤ እኛ ኢትዮጵያዊያን ስንሞትም ስንኖርም ኢትዮጵያዊ ነን" ብለው በቁርጠኝነት ተናገሩ።

ቀጠል አድርገውም "ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ ዐውቃለሁ።ስለዚህ በኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ።" አሉ።

ወደ ሕዝቡ ዞር ብለውም "አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግስት ቤተ ክርስቲያን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያን ለመግደል፣ ሃይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው፤ እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ግፈኛ አትገዙ። ስለ ውድ አገራችሁ፣ ስለ ቀናች ሃይማኖታችሁ ተከላከሉ። ነጻነታችሁ ከሚረክስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዎጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጣላት እንዳይገዛ አውጋዣለሁ፤ የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን።" በለው አወገዙ።

ችሎት ላይ ያለውን ሕዝብ በሙሉ ስለ እርሳቸው ሲያለቅስ አሳቸው ግን መስቀላቸውን አውጥተው እየጸለዩ ሕዝቡን ባረኩ።

ወደ መግደያ ቦታም ወሰዷቸው በዚህ ጊዜ በዛሬዋ ዕለት ከአራዳ ጊዮርጊስ ዝቅ ብሎ ባለው ቦታ በአደባባይ በጥይት ሩምታ ዘንቦባቸው በሰማዕትነት አረፋ::

ቤተ ክርስቲያንም ጥቅምት 12 ቀን 1998 ዓ.ም "አቡነ ጴጥሮስ ሰማዕተ ጽድቅ ዘኢትዮጵያ" ተብለው እንዲጠሩ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ጻድቁ በተወለዱበት ሥፍራም በፍቼ ከተማ ግንቦት 1 ቀን 2001 ዓ.ም ጽላት ተቀርጾላቸው ቤተ ክርስቲያን በስማቸው ታንጾላቸው መታሰቢያ ሐውልትም ቆሞላቸዋል።

ያልተነገረላቸው ሰማዕታት ያልተዘመረላቸው ጀግና የደብረ ሊባኖስ ኮከብ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ በረከቶ ይድረሰን።

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት የአባታችን በረከት ይድረሰን ይደርብን ለዘላለሙ አሜን!
@ethiopianorthodoxs
2.1K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 09:53:55 ሐምሌ ገብርኤል:-
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሐምሌ 19 በዚህች ቀን ሕፃኑ ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ መከራ ተቀበሉ::

ይህም ሕፃን ዕድሜው 3 ዓመት ሲሆነው ከሮም ወደ ሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች::

በዚያም የሸሹትን መኰንን በዚያ አገኙት ወደ መኰንኑም ቀረቡ አምልኮቷን ጠየቋት እርሷም 3 ዓመት የሆነ ልጅ አለኝ እርሱን ጠይቅ አለችው::

ሕፃኑንም ከፊቱ አቁመውት አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው::

ሕፃኑም ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ለአንተ ግን ኅዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው::

መጽሐፍ ለዝንጉ ተድላ ደስታ የለውም አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታትን በኮልታፋ አንደበቱ ረገማቸው ብርታቱንም አይተው አደነቁ::

ከዚህ በኋላ መኰንኑ በትልቅ የናስ ጋን ውኃ ጨምረው እሳት ያነዱ ዘንድ አዘዘ የእሳቱ ድምፅና ውኃው ፈልቶ ሲፍለቀለቅ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ሆነ።

ቅድስት ኢየሉጣ ያን ጊዜ ፍርሃትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሳባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ::

ጌታም ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳኑ የተዘጋጀውን የብርሃን ማደሪያዋችን አሳያት ከዚያ በኃላ በእምነቷ ጸንታ እግዚአብሔርን አመሰገነች::

ወደ ጋኑም በገቡ ሰዓት የውኃው መፍለቅለቅ እንፋሎቱ እንደ ንጋት ውርጭ ሆናቸው::

ከእግዚአብሔር የተላከ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል በዛሬው ዕለት አቀዘዝቅዞታልና::

ያን ግዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው።

እግዚአብሔር አምላክ መልአኩን ልኮ በአገራችን ላይ የተቃጣውን የዘረኝነትና የመከፋፈል እስት ያርቅልን ያብርድልን።

ለእግዚአብሔርምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና ኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸው ይድረሰን ለዘላለሙ አሜን::
@ethiopianorthodoxs
2.4K views06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ