Get Mystery Box with random crypto!

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመረቀች ቻይና በአማርኛ ቋን | Ethiopian Digital Library

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን አስመረቀች

ቻይና በአማርኛ ቋንቋ ያስተማረቻቻውን የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን በትናትናው እለት አስመርቃለች።

በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) በትናናው እለት ተማሪዎቹን ያመረቀ ሲሆን፤ ከተመራቂዎቹ መካከልም በአማርኛ ቋንቋ በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን ተማሪዎቹ ይገኙበታል።

በቻይና የኢትዮጵያ ኤማባሲ ተወካዮች ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) የአማርኛ ቋንቋ ተማሪዎች ምርቃት ላይ መሳተፋቸውንም ኤምባሲው አስታውቋል።

“በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU በቻይና ውስጥ ብቸኛው የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ክፍል የሚሰጥ ዩኒቨርሲቲ ሲሆን፤ ትናንት ከተመረቁት መካከል የመጀመሪያው ዙር የአማርኛ ተማሪዎች ይገኙበታል ብሏል ኤምባሲው ባወጣው መረጃ።

ኤምባሲው ቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት መስጠቱን አመስግኖ ፤ “ይህ የሁለቱን ሀገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያጠናክራል” ብሏል።

የቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርሲቲ ለቻይናውያን ተማሪዎች የተዘጋጁ የአማርኛ መማሪያ መጽሃፍትን ባሳለፍነው ዓመት ግንቦት ወር ላይ ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በቤጂንግ የውጭ ጥናት ዩኒቨርስቲ (BFSU) አማርኛ ቋንቋን በመጀመሪያ ዲግሪ ማስተማር መጀመሩን ይፋ ያደረገው በፈረንጆቹ 2022 ላይ ነበር። #ዳጉ_ጆርናል

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library