Get Mystery Box with random crypto!

47 ዓመታትን የዘለቀ አብሮነት!! የንጋት አብሪዋ ኮከብ ተመስሎ የተወለደው ቡና እነሆ የሀገር | ቡናችን👆

47 ዓመታትን የዘለቀ አብሮነት!!

የንጋት አብሪዋ ኮከብ ተመስሎ የተወለደው ቡና እነሆ የሀገር ኩራት የብዙሃን መሰባሰቢያ እና የደስታቸው ምስጢር ሆኖ 47ኛ ዓመቱ ላይ ደርሷል።

እግር ኳስ ውበቱ.....  ደጋፊው የክለብ መቆሚያ ካስማ.... ታማኝ ደጋፊ የታማኝ ደጋፊዎች መገለጫ ያላቸውን ሳይሰስቱ ለሚወዱት መስጠት መሆኑን ያየነዉ በታላቁ የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊ ነው

....የ47 ዓመቱ ጎልማሣ የሚሊዮኖች መሰባሰቢያ ዋርካ የሸገር አርማዉ የኢትዮጵያዊነት ተምሣሌት ........ የኢትዮጵያ ቡና ስፖርት ክለብ

ለቡና መወለድ ምክንያት የሆናችሁ መከራዉን በድፍረት ተጋፍጣችሁ ለወግ ማዕረግ ያበቃችሁ የብዙ ሚሊዮኖች መሰብሰቢያ ያደረጋችሁ ባለዉለታዎች እንኳን አደረሳችሁ!! ስምና ሥራችሁ ቡና ባለበት ሁሉ ሁሌም በበጎ ይነሳል። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን መታደል አለ? እናንተ ታድላችኋል እኛ ደግሞ እጅ ነስተን በክብር እንኳን አደረሳችሁ እንላችኋለን።

በነዚህ 47 ዓመታት ዉስጥ ሚሊየኖች ለቡና ተደብድበው ታስረዉ የአካል መጉደል እንዲሁም የህይወት መስዋዕትነት ከፍለውለታል...

እናንተ በቃላት የማይገለፅ ፍቅር የለገሣችሁት ..... በዉጤት ምክንያት ያልራቃችሁ ...... ከግል ጉዳይና ኑሮ በላይ ለቡና የሚትጨነቁ በሄደበት ሁሉ ድምቀቱ እና መከታው የሆናችሁ..... በጎነትን ካለዉ ማካፈልን አብዝታችሁ ያስተማራችሁ ...... ሮጣችሁ ላባችሁ አፍስሳችሁ ለቡና መቆም ምክንያት የሆናችሁ...... የሜዳዉ ድምቀት የጥበብና የፈጠራ ባለቤቶች የኢትዮጵያ ቡናቤ ተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ!!

እግር ኳስ ዋጋ ባልተሰጠው ዘመን ጀምሮ ገንዘባችሁ በድፍረት አውጥታችሁ ስፖርታዊ አጋርነትን ፈር የቀደዳችሁ ተቋማትና ግለሰቦች አጋሮቻችን እንኳን አደረሳችሁ!! ...... ነግዳችሁ አትርፉ ..... ፍቅር ተወዳጅነት ስኬትና ከፍታ ሁሌም እንመኝላችኋለን!! ..... የምንወደውን ስለደገፋችሁ ምርጫችን ምርትና አገልግሎታችሁ ነዉ!! ...... አምባሳደራችሁ ሆነን በየሄድንበት መልካም ስማችሁ ከማስተዋወቅ አንቦዝንም!! ......ምክንያቱም ማደግ በመደጋገፍ ዉስጥ መሆኑ አብረን በቆየንባቸዉ አመታት ዉስጥ እኛም እናንተም ተገንዝበናል።

በሀገሪቱ ዘመናዊ አደረጃጀት ያለዉ በህግና በዕውቀት የሚመራ ብቁ የሠዉ ኃይል ያለዉ የራሱ ሜዳና ካምፕ ባለቤት ...... ከመጀመሪዋ ዕለት ጀምሮ ክለቡን በመምራት በትጋት በማገልገል የሚጠበቅባችሁን ብቻ ሳይሆን ያላችሁን በሙሉ በመስጠት ያገለገላችሁ አመራሮች እና ሠራተኞች የዚህ አኩሪ ታሪክ ባለቤት ናችሁና እንኳን ደስ ያላችሁ!! እንኳን አደረሳችሁ!!

በባዶ እግር በራስ ልብስ ጭምር ታላቁ ቡና እንዲታወቅ በብዙዎች እንዲወደድ ባለታሪክ እንዲሆን በታማኝነት ለክለባችን የተጫወታችሁ፣ ያስለጠናችሁ፣ ያማከራችሁ ዛሬ ልፋታችሁ መና አልቀረም...... የዘራችሁት በቅሎ በዝቷል  እንኳንም ደስ ያላችሁ!! እንኳን አደረሳችሁ!!

....በኢትዮጵያ እግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያው ህጋዊ ደጋፊ ማህበር ባለቤት ....የኢትዮጵያ ቡና እንደ አሸዋ በዝቶ እንደ ክዋክብት ደምቆ እንዲታይ ሀሳብ ያመነጫችሁ ያስተባበራችሁ የመራችሁ በገንዘብ የደገፋችሁ ቅን የኢትዮጵያ ቡና ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ!!

ገና እንበዛለን..... በዛሬ ድክመታችን ውስጥ ውጤታማ ነገን እናያለን ... ሁሌም እንተጋለን!! በዝማሬ ታጅበን የታላቁ ክለባችንን ፍልሚያ ባለበት ተገኝተን እናደምቃለን .... በፍቅርና በአክብሮት አጋሮቻችንን ይዘን እንበዛለን!! ታላላቆቻችንና ባለውለታዎቻችንን እያከበርን.... ሌሎች ባለታሪኮችን እናፈራለን!! እንደ ቤተሰብ እየተወቃቀስ እና እየተመካከርን በጠንካራ መሠረት ላይ ቆመን.... በህብረት ቡናችንን እያጣጣምን ገና ብዙ ዓመታትን እንዘልቃለን!!

#ከምናልመው_ከፍታ_እና_ከምንናፍቀው_ደስታና_መዳረሻችን_ቅርብ_ነው!!

ኢትዮጲያ ቡና የሚሊዮኖች የልብ ትርታ

@Ethiopian_Coffee_Sc
@Ethiopian_Coffee_Sc