የ ኢትዮጵያ ቡና የማሊያ ርክክብ ! ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀ እስከ ፐ ከተሰኘ የትጥቅ አምራች ኩባንያ ጋር ዛሬ የትጥቅ ርክክብ ስነ-ስርዓቱን በ ሳፋሪ ሆቴል አከናውኗል ። ከ ሀ እስከ ፐ ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ላለፉት አምስት አመታት በጋራ የሰራ ሲሆን ኢትዮጵያ ቡና አዲሱን ማሊያ በሁለተኛው ዙር የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ እንደሚጠቀምበት ተገልጿል ። ኢትዮጵያ ቡና ከ ሀ እስከ ፐ ጋር በጋራ በመሆን አራት ኪሎ አምባሳደር ህንፃ ላይ አዲስ የትጥቅ መሸጫ ሱቅ ከአንድ ወር በኋላ እንደሚከፍት ገልጿል ። በትጥቅ መሸጫ ሱቁ ላይ ከክለቡ ማሊያዎች በተጨማሪ የክለቡ አርማን የያዘ የተለያዩ ኮቶች እና ልዩ ልዩ አልባሳት እንደሚሸጡ ተገልጿል ። ከ ሀ እስከ ፐ ለ ኢትዮጵያ ቡና ዋናው ቡድን ፣ ከ 20 አመት በታች ፣ ከ 17 አመት በታች እና ለ ሴቶች ቡድን በአጠቃላይ 500 ማሊያ እንደሚያቀርብ ተገልጿል ። ከ ሀ እስከ ፐ ለ አሰልጣኞች ከ መቶ በላይ እና ለአሰልጣኝ አባላት 50 የክለቡ አርማን የያዙ ማሊያዎችን እንደሚያቀርብ ተገልጿል ። በ አጠቃላይ ከ ሀ እስከ ፐ ለ ኢትዮጵያ ቡና ያቀረባቸው ትጥቆች ዋጋ ሶሰት ሚሊየን 25 ሺህ ብር እንደሆነ ተገልጿል ። ከ ሀ እስከ ፐ ከዚህ ቀደም የሀበሻ ቢራን የብራንድ የትጥቅ መሸጫ ሱቅን የከፈተ እና በዘርፉ ላይ የስምንት አመት ልምድ ያለው ሲሆን በ ኢትዮጵያ ቡና ማሊያ እጅጌ ላይ የድርጅቱ አርማ እንደሚቀመጥ ገልጿል ። @ethiopiabuna12t @ethiopiabunasportteam 143 viewsKᴀʟᴇᴀʙ የየካው, edited 13:51