Get Mystery Box with random crypto!

እጃችሁን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሱ 'ከሀገር የመከብለል ምስጢራዊ ዕቅድ እንዳላቸው ይፋ ሆነ' አ | 🇨🇬ደጉ ሳምራዊ የተገፊዎች ድምጽ ✟✟✟

እጃችሁን ከቤተክርስቲያን ላይ አንሱ
"ከሀገር የመከብለል ምስጢራዊ ዕቅድ እንዳላቸው ይፋ ሆነ"

አጀንዳ ለማስቀየር ቤተክርስቲያንን መጠቀማችሁን አቁሙ። የብልፅግና መንግስት አንድ ነገር ሲያስብ ቀድሞ በእነማን እንደሚያስወራ እናውቃለን። ከዚህም በፊት ቅዱስ ፓትርያርኩ ያልተባሉት ነገር አልነበረም። የብፁዕ አቡነ መርቆሬዎስን ታሪክ ለመድገም የሚተጉ የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች በቤተክህነቱና በቤተ መንግስቱ አካባቢ እንዳሉ እናውቃለን። ቅዱስ ፓትርያርኩን ከውጭ ህወሃት ይጎትታቸዋል ከውስጥ የብልፅግና ካድሬ ይገፋቸዋል። ይህንን ሁሉ ችለው ቤተክርስቲያንን ለጅብ አልሰጥም ብለው ሁሉን ችለው ቆመው ያሉ አባታ ናቸው።

ብልፅግና በቤተክህነቱ አክቲቪስቶች አማካኝነት ሊሰራ ያሰበው መሠሪ ተንኮል እንዳለ መረዳት ተገቢ ነው ስለዚህ ሁላችንም በንቃት ከቅዱስ ፓትርያርኩና ከቤተክርስቲያን ጎን በመቆም እንደ እስከዛሬው ቤተክርስቲያንን የመከፋፈል ሲራ ልናመክን ይገባል። ይህ መቅሰፍት የሆነ መንግስት እጁን ከቤተክርስቲያን ላይ እንዲያነሳም ሊነገረው ይገባል።

ብፁዕ አባታችን ቡራኬዎ ይድረሰን
ይፍቱኝ ይባርኩኝ

@ETHIOPIA_Hagerie