Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ ምስል አትገረም። የደኸየ ኪስ እንጅ የደኸየ ስነልቦና የለንም። የቆሸሸ ልብስ እንጅ የቆሸሸ | PAPIO BELETE 💚💛❤️

በዚህ ምስል አትገረም። የደኸየ ኪስ እንጅ የደኸየ ስነልቦና የለንም። የቆሸሸ ልብስ እንጅ የቆሸሸ አዕምሮ የለንም። የቀጠነ ሰውነት እንጅ መከራ የማይችል አጥንት አልተሸከምንም። ህዝብን እንደ ህዝብ አገርን እንደ አገር የሚያከብር አስተሳሰብ እንጅ በሀያል ናቸው ተራ ፕሮፓጋንዳ የሚሸነፍ ወንድነት አልሰራብንም። ሰዎቹ ኩሩ ነን። በማንም ጎረቤቶቻችን ላይ የማንንም ክብር እና ሉአላዊነት ደፍረን እምነቱን ለይተን፣ ቋንቋውን መርጠን ጥቃትና ወረራ ፈፀመን አናቅም። አክብረን የተከበርን ህዝቦች ነን።

ማንም ይሁን የትም ሰው በመሆኑ ብቻ እናከብራለን። ለዚች አለም ስግብግብ የሆነ አመለካከት የለንም። ሆዳችን አሸንፎን ችግራችንን በክብራችን ተደራድረንበት አናቅም። ጥቁር አድርጎ ሲሰራን በመፅሀፍ ቅዱስ ክብር ያላት አገር ተብሎ ስማችንን
ከትቦ ሲያስቀምጥልን ፣ በታላቁ ነብየ (መሀመድ ) ሰአወ ..ሀበሾችን ካልነኳችሁ አትንኩ ብለው የተናገሩልን ሚስጠረኛ ህዝቦች ነን። በታሪካችን እማንም ላይ ዘለን ገብተን የማንም ክብር አልነካንም። ክብራችንን ገፍተው የነኩንን ወራሪና ተላላኪ ባንዳና ቅኝ ገዢዎችን ግን አዋርደን መመለስ እንችልበታለን።