Get Mystery Box with random crypto!

የፍቅር ደብዳቤ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiop_books — የፍቅር ደብዳቤ
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiop_books — የፍቅር ደብዳቤ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiop_books
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 591
የሰርጥ መግለጫ

ፍቅር💚Loveፍቅር💙Love
ፍቅር❤️Loveፍቅር💜Love
ፍቅር💛Loveፍቅር❤️Love
ፍቅር💚Loveፍቅር❤️Love
የፍቅር_ደብዳቤ💌 የፍቅር_ደብዳቤ💌

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2022-07-13 21:33:01 ​​ መልካሙ ዶክተር

ክፍል አንድ ➊

አዘጋጅ ብሩክ

ስሜ ሀረግ ነው፣ ሀረግ የሚለውን ስም ማን እንዳወጣልኝ እንኳን አላውቅም ሀረግ የሚለው ስም ለኔ ብዙ ትርጉም ይሰጠኛል አንድ አንድ ጊዜ የሆነ ሰው ጥሎኝ ልሄድ ተክሎኝ የሄደ ዛፍ እንደሆንኩ ይሰማኛል ፍሬ የሌላ ዛፍ! የብቸኝነት ህይወት እንደዚህ ከባድ ነው ብሎ ለሌላ ሰው ለማስረዳት እንደዚህ ነው ብሎ ምሳሌ የሚሰጡት ነገር እንኳን ሊኖር አይችልም። ሁሉ ሰው ወደዚህች አለም ሲመጣ ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚመጣው ከዚህ አለም ሲሄድም ተመሳሳይ ነገር ነው ይዞ የሚሄደው ነገር ግን በዚህች አለም ላይ ሁሉም ሰው የተለየያ ህይወት ይኖራል አንዱ የአንዱን ህይወት መኖር በፍጹም አይችልም ምክንያቱም የዚህች አለም ኑሮ መሪዋ እድል በምንለው ነገር የተያዘች ናትና፣ እሱ ወደፈለገበት እንጂ እኛ መሄድ የምንፈልግበትን ቦታ መሄድ አንችልም። ማንም ሰው ከእናቱ/ከአባቱ ተለይቶ መኖር አይፈልግም ግን ብቸኛ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው አካለ ስንኩል ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን በግድ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው ድሃ ሆኖ መኖር አይፈልግም ግን ድሃ ሆኖ ይኖራል፣ ማንም ሰው በህመም እየተሰቃየ መኖርን አይፈልግም ግን ብዙ ሰዎች በህመም እየተሰቃዩ ይኖራሉ ፣ ለዚህም ነው ህይወት የምርጫ ጉዳይ ሳትሆን እድል ላይ የተሰራች ቤት ነው ያልኩት በዚህ አለም ላይ አብዛኛው ነገር ለሰዎች በተናጥል ተሰጥቷል ለሁሉም ሰው እኩል የተሰጠ ነገር ቢኖር " #ፍቅር " ብቻ ነው! በዚህ ምድር ላይ ለሁሉም እኩል የተሰጠ ስጦታ ፍቅር ብቻ ነው ህጻን ይሁን ሽማግሌ፥ ሴት ይሁን ወንድ፥ ቆንጆ ይሁን አስጠሊታ ፥ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታውን ተቀብሏል፣ ምንም እንኳን ስጦታውን በአግበቡ የሚጠቀሙ ሰዎች በጣም ጥቂቶች ቢሆኑም ቅድም እንዳልኩት ሁሉም ሰው የፍቅር ስጦታን ከፈጣሪ ዘንድ ተቀብሏል።
የኔ የፍቅር ታሪክ የሚጀምረው በአንድ መጥፎ አጋጣሚ ቢሆንም አጋጣሚው ግን በድንገት ህይወቴን ቀይሮ አየሁት
ፈጣሪ ህይወትህን ለመቀየር ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ አይመጣም ሰይጣንም ቢሆን ህይወትህን ለማበላሸት ሲፈልግ ሰው ይልካል እንጂ እሱ በተግባር አይመጣም ልዩነቱ ፈጣሪ መልካም ሰው ይልካል ሰይጣን ደግሞ ክፉ ሰው ይልካል እንደ አጋጣሚ ሆኖ ለኔ የተላከው ሰው መልካም ሰው ነበረ #እዩኤል እኔ እንደዚህ ነው ብዬ ከምነግራችው በላይ መልካም ልጅ ነው ከምንም በላይ ለኔ ለብቸኛዋ ምስኪን ልጅ ወንድም እናት አባትም ጭምር ነው እዩኤልን የተዋወኩት ድሮ ድሮ የጎዳና ልጅ እያለሁ ነበረ አንድ ቀን መንገድ ላይ መሬት ላይ ወድቆ ሰው ሁሉ ዝም ብሎት እያለፈ አይቼ ኪሴ ውስጥ ለምሳ ሰርቄ በያዝኩት ብር ሃኪም ቤት ወሰድኩት ሃኪም ቤት ውስጥ የካርድ ብር አጥቼ ወዲህ ወዲያ ስል............

ይቀጥላል .......
ቶሎ እንዲቀጥል


ከ 30 Like በኋላ ይቀጥላል

LIKE SHARE COMMENT
230 views18:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 21:59:14 ​​ . . . ሀያል ፍቅር . . .

ያሉትን ይበሉ ተዋቸው ይናገሩ
ሲያወሩ ውለው ሲያወሩ ይደሩ

ወረኛው ቢበዛ ስራ ፈት አሳባቂ
አምላክ አለን ለኛ የፍቅራችን ጠባቂ

"እንዲ ሆነ" ቢሉ ቢመሰክሩ በየተራ
ፍቅራችን ላይቆም ምንም ቢወራ

መሰረታችን ፍቅር ነው በምንም ማይለካ
ህይወት ነው እስትንፋስ በማንም ማይተካ



@ethiopbooks
@yelebemelekt
293 views18:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 13:54:00 ሁሉም ሰው የምትሰጠውን ያህል አይመልስልህም የምትጨነቅለት ያህል አያስብልህም ዓለም እንደዚ ናት አንተም ለመቀበል ከሆነ አትስጥ ከተቻለህ ለማይመልሱልህ ግን ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች መልካሙን ነገር ሁሉ አድርግ...
ፍቅርን ታተርፋለህ...
መልካም ቀን
303 views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-12 12:11:27
best profile pictures

Join &share
305 views09:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 21:03:43

ህይወት ከስህተት የጠራች አይደለችም. . .
መሳሳትት ማለት ግን ማጥፋት አይደለም፤
ስህተትን ችግር አድርጋችሁ አትመልከቱት፤
ከተሳሳትን በኃላ ለማስተካከል እንሞክር እንጂ . . .
አዋቂዎች ሆነን አልተፈጠርንም
. . . እየኖርን እናውቃለን!

@yelebemelekt
@yelebemelekt
283 views18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 15:55:53 እባካችሁ 2ተኛው ቻናሌ join በሉ

እንኳን ወደ ቻናላችን በደህና መጣችሁ
ጣፋጭ የፍቅር ታሪኳች
መሳጭ አባባሎች
እሪፍአሪፍ ግጥሞች
አፍቅረዋል ፍቅሮንስ
ለመግለፅ ተቸግረዋል
በቃ እኛ አለንሎት!!
ይቅርታ መጠየቅስ ፈልገዋል
ለፍቅረኛዎ መልክት ማስቀመጥ ከፈለጉ
በዚህ ሊንክ መላክ ትችላላችሁ @yodeha

@yelebemelekt
326 views12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:53:34 ​​​​ ♂የሰፈሬ ልጅ

እውነተኛየፍቅርታሪክ

የመጨረሻው ክፍል

... ጉዴን ይነግረኝ ጀመር ቢኒ ወደ ጢስ አባይ አጎቴ ጋ እሄዳለው ያለኝ አውቆ እንደሆነ እና
እናቴ ዘንድ ወደ አ/አ እንደ ሄደ እናቴ ደማነስ ስላለባት በጣም ታማ ስለነበረ እሷ ሊያያት እንደ ሄደ ነገረኝ ድብስ ብስ አድርጎ ተናግሮ ማለፍ ፈለገ እኔም በጣም ገረመኝ አንድ ጥያቄ የፈጠረብኝ ነገር አለ አልኩት ቢኒ ይሄን ታክል ለእናቴ መስዋትነትን የከፈለ ለም
ንድን ነው አልኩት ያን አላውቅም አለኝ ምን አልባት ሰለሚወድሽ ይሆናል አለኝ በዚህ ዘመን ምን አይነት ፍቅር ነው"" ይሄን ታክል መስዋትነት የሚያስከፍል አልኩኝ አቤል እውነቱን ልንገርህ አደለ ላለመናገር ስለፈለክ እንጂ የሆነ ሚስጥር እንዳለ ይገባኛል አልኩት እንደዛ ለምን ታስብያለሽ እያለ ብዙ ቀባጠረብኝ እንደ ማይነግረኝ ሳውቅ አመሰግናለሁ በቃ ቻወ አልኩት ለተወሰነ ሰከንድ ዝም አለኝ

ማውቅ የለለብሽን ባታውቂ ምን ይቀርብሻል አለኝ ሚጠቅመኝን አኔነኝ ማውቅ አልኩትኝ አሺ በቃ ሰረኬን ጠይቂያት አለኝ ሰርኬ ማለት ሰራተኛችን ናት አሁን የባሰ ደነገጥኩ እንነዚህ ሰዋች ቢኒ እንዴት አድርጎ ቢቆልፋቸው ነው ይሄን ታክል ለመናገር የከበዳቸው አልኩኝ እሺ ብዬ ተሰናብቼው ተለያየን ሰራተኛችን በሌላ ቀን ማታ ላይ ብዙ ስናወራ ቆየንና ከብዙ ጭቅ ጭቅና ንትርክ በኃላ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሊያደርግ የቻለው የቢኒ እናት ለእናትሽና ለአባትሽ መለያየት ዋና ምክንያት ናት አለችኝ ደነገጥኩኝ የቢኒ እናት በጣም ክፉና ወረኛ ሰለነበረች ለእናትሽ ሰለአባትሽ መጥፎ ነገር እየተናገረች እንዲፋቱ ያደረገች እሷ ናት አለች ከዚያን በኃላ አባትሽ ታሞ ስለ ነበረ ብዙም ሳይቆይ እንደ ሞተ እና እናቴም የአባቴን መሞት ስትሰማ ከዛን ቀን ወዲህ በሽተኛ እንደሆነች ብዙ ስቃይ እንዳሳለፈች በሰአቱ ገና ህፃን እንደ ሆንኩ ነገረችኝ ቢኒ ይሄን ሁሉ ሰለ ሚያውቅ እናቱ ጋር ተጣልቶ አባቱ ጋር እንደ ሚኖር እና እናቴ የሞት አፋፍ ላይ ሁና ታማ እንኩላሊቱን እንደ ሰጣት በተለያየ ግዜ ደግሞ ደማነስ ስላለባት ደሙን እንደ ሰጣት ነገረችኝ ይሄን ሁሉ ያደረገው እናቱ የበደለቻትን እሱ ሊክሳት እንደ ሆነ እኔንም ሰለሚወደኝ ይሄን ሁሉ እንዳደረገ ስትነግረኝ የሰማሁትን መቀበል አቃተኝ በእንባ ታጠብቁ ቢኒ የልጅ አዋቂ ነው እድሜውና አስተሳሰቡ አይገናኝም ብህይወት እስካለሁ ድረስ ቢኒን እንደ ምጠብቀው ለራሴ ቃል ገባሁ።

ከብዙ ልፋት በኃላ እኔም በጥሩ ውጤት ተመረኩኝ ወድሜ በጣም ደስ አለሁ ህይወት ቀጠለች ስለ ቢኒ ሳልስማ አመታት አለፈኝ እሁድ ቀንን አወደዋለሁ ጉዋደኞቼ ጋር ስንዝናና ውለን ወደ ቤት መጣሁ
ሰራተኛችን ሳያት ተኝታለች እኔም ልረፍ ብዬ ወደ ሩሜ ስሄድ
ለስለስ ያለ ሙዚቃ ተሰማኝ ወደ ክላሴ የምሄድበት ኮሪደር እንደ ጨፌ የተጎዘጎዘ ቀይ ፅገሬዳ አየሁ የልቤ ምት ሲጨምር ይታወቀኛል ቀስ ብዬ በሩን ከፈትኩት በህይወቴ ብዙ ሚያምሩ ክለሶችን አይቻለሁ እንደ ዛሬው ግን የሚያምር ክላስ አይቼ አላውቅም ወደ ወስጥ ገበሁ ሳለሰስበው ከኃላዬ አይኔን ከደነኝ ድምፁን ጎርነን አደርጎ እኔ ማነኝ አለ ቢኒ ነው ከደስታዬ ብዛት የተነሳ ጨውኩኝ ተጠመጠምኩበት
ብዙ ግዜ አልቅሻለሁ እንደ አሁን ግን የደስታ እንባ አላለቀስኩም
በቃ ቢኒ ማለት ለእኔ ወንሜ እህቴ እናቴ አባቴ ጓደኛዬ ፍቅረኛዬ ነው በህይወቴ አልሜው የማለውቀውን ነገር አደረገለኝ የእናቴን ቀለበት አሰረልኝ ከዚህ በላይ ፍቅር የት አለ ለቢኒ አረገዝኩለት ህይወት ትቀጥላለች ። አንድ የምወደው የመጽሀፍ ቅዱስ ቃል አለ

#በለሱንየጠበቀፍሬውንይበላልጌታውንየጠበቀይከብራል



//ተፈፀመ//


ምስጋና
ታሪኩን በመከታተል አስተያየታችሁን ላደረሳችሁኝ በሙሉ!

በታሪኩ ላይ ያላችሁን አስተያየት ከታች አስተያየት @etthiop_books የሚለውን በመንካት ያድርሱን፡፡
330 views09:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 12:49:32 ​​ላትጨርሰው ነገር ፍቅርን ጀምረክ
የመሀላ ቃሉን ሁሉንም እረስተክ
መለዬትን ወሰንክ መራቅን ፈልገክ

ሂድ ተመላለስ ድረስ ካሰብክበት
ድሮም መንገደኛ አይቆምም ባለበት
ወደድኩሽ ሞትኩልሽ ማለቱም ይቅርበት
የሰጠከኝ ፍቅር ይኑር እንደዘበት
አንተም ከእኔ እራቅ እኔም ልቻልበት
​​
...........
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
299 views09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 19:18:02 ​​​​ ‍ የሰፈሬ ልጅ

እውነተኛ የፍቅር ታሪክ

#ክፍል_14

... የወንድሜ ትክሻ ላይ የእናቴን ልብስ አየሁት እናቴ ሞተች ከዛን በኃላ የተፈጠረውን አላውቅም ከሁለተ ቀን በኃላ ራሴን ሆስፒታል አገኘውት
በቃ የተፈጠረውን ሳውቅ አበድኩ የእናቴ መቃብር ላይ እንዴት ልቁም ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣብኝ እናቴን ዳግም እንደ ማላገኛት ሳውቅ መኖር አስጠላኝ ወንድሜ ከእልቅሶ ብዛት ማውራት አይችልም ሀዘኔ በጣም በረታ ሁሉም ነገር እንዳያልፍ የለ አለፈ

በጣም የሚገርመው ቢኒ ወደ አጎቱ ከሄደበት ቀን ጀምሮ አላየሁትም እናቴ ከሞተች አንድ ወር አለፈው ወንድሜ ለእኔ የካናዳ ፓስፖርት አምጦ ሰጠኝ ደነገጥኩኝ ፕሮሰሱን ከጀመረ ቆይቷል ግን በዚህ ሰአት ያመጣዋል ብዬ አላሰብኩም ወንድሜ ቤታችንንም ሽጦታል ሰራተኛችን አሳዘነችኝ ከህፃንነቴ ጀምሮ አሷ ናት ያሳደገችኝ እናቴን አጥቻት ሰራተኛችንን አጥቻት ቢኒን አጥቼው መኖሬ አስጠላኝ በቃ ምርር ብዬ አለቀስኩኝ ወንደሜን አልሄድም አልኩኝ እንደዛ ስለው ከእኔ በላይ አበደ አውቃለሁ ካሁን በኃላ ያለኝ በቸኛ ተስፋዬ ወንድሜ ነው ይሄን ሀሳብ ደግመሽ እንዳታስቢው አለኝ ለመብረር ሁለት ሳምንት ሲቀረን ወደ አ/አ መሄድ አለብን አለኝ ልቤ በፍረሀት ተውጧል ሰፈረ ላይ አቤልን አገኘውት ቢኒን ስጠይቀው እንዳላየው ነገረኝ መናገር አልፈለገም በቃ ስለ ቢኒ ከአቤል ውጭ የሚያውቅ የለም ቢኒን የማግኘት ተስፋዬ መነመነ ሳቄ ሁሉ ሀዘን ዋጠው

ወደ አ/አ ልንሄድ ሰንል ዕቃችንን ስናወጣ ሰራተኛችንም ቦርሳዋን አወጣች ደነገጥኩ አንቺ ወንዴት ልትሄጂ ነው አልኳት እየሳቀች የእጅ ቦርሳዋን ከፍታ ፓስፖርቷን አሳየችኝ ዘልዬ ተጠመጠምኩባት
እናቴ እኔ ጋር የምትሄድ ያህል ነው የተሰማኝ ደስ አለኝ ወንድሜን ሂጄ አቀፍኩት በጣም አመሰገንኩት ለእሷም የካናዳ ፕሮሰስ ጨረሰላት
በቃ ሰፈሬን ስለቅ ውስጤ ተረበሸ ቢኒን ሳስበው እንባዬን አልቻልኩም

ያለፈው ሁሉ አልፎ ካናዳ ቶሮንቶ ገባን ወንድሜ ከናዳን ይወዳታል ለብዙ አመታት ኑሮባታል እኔ ግን ሀሳቤ ቢኒ ጋ ነው ቢኒ ከህይወቴ ለአንድ ሰከንድ መጥፋት አልቻለም እሱን የማላስበብት ግዜ የለኝም
ከብዙ ግዜ በኃላ አቤልን ዋትሳፕ ላይ አገኘሁት በጣም ደስ አለኝ በቃ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ነው የማገኘህ እውነቱን ምትነግረኝ ከሆነ ምንም ሳትደብቀኝ ንገረኝ አልኩት እኔ እንደዛ ስለው እንደ መደናገጥ ቢልም
ጉዴን ይነግረኝ ጀመር ቢኒ ወደ ጢስ አባይ አጎቴ ጋ እሄዳለው ያለኝ አውቆ እንደሆነ እና
እናቴ ዘንድ ወደ አ/አ እንደ ሄደ…



. ꧁༺༒༻꧂
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
@ethiop_books
••●◉Join us share ◉●••

┄┄┉┉✽‌»‌ ✿ »‌✽‌┉┉┄┄
342 views16:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 11:31:23 መለየትን የማይፈራ መውደድ የማይችል ብቻ ነው.......


ፍቅር ደካማም ያደረግናል። በጥልቅ ስታፈቅሩ ያፈቀራችሁት ሰው ዓለማችን ይሆናል። ጎዶሎአችን በብቸኛነት የሚሞላ ሰው ያ ሰው ብቻ መስሎ ይሰማናል። ስለሆነም ያ ሰው ማጣት ወደ ጎዶሎነታችን የሚመልሰን የብቸኝነት ዜማ አድርገን እቆጥረዋለን። ጥልቅ ፍቅር ታላቅ የማጣት ፍርሀትን ይወልዳል። ለኔ እንዲያውም እንደ ፍቅር ፈሪ የሚያደርገን የለም። ታላቁ ፍርሀት የሚፀነሰው እጅግ አብልጠን የምንወደውን ነገር ላለማጣት ነው። ፍቅር ልክ እንደ ስልጣን ነው። ባለስልጣን ስለወንበሩ ላይፈራና ላይጨነቅ ይችላልን? ፍቅር ውስጥ እምነትና ተስፋ ቢኖሩም ፍፁም እርግጠኛ መሆን የምንችለው በራሳችን እምነትና ተስፋ ላይ እንጂ ባፈቀርነው ሰው ስለእኛ ስላለው እምነትና ተስፋ እርግጠኛ መሆን ስለማትችል እሱን የማጣት ስጋት ልባችንን ውስጥ መንቆርቆሩ አይቀሬ ነው። እኛ ባለን እውቀት፣ እምነትና ተስፋ ብቻ ፍቅሩ አይቆምምና!

ለመቀላቀል
@yelebemelekt

መልካም ቀን
384 views08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ