Get Mystery Box with random crypto!

ፀረ-ታንክ ሚሳኤል የማይመታው አዲሱ የቱርክ ታንክ #Ethiopia | የኤርዶጋኗ ቱርክ በወታደራ | Ethio News Media

ፀረ-ታንክ ሚሳኤል የማይመታው አዲሱ የቱርክ ታንክ

#Ethiopia | የኤርዶጋኗ ቱርክ በወታደራዊ ቴክኖሎጂ እየተራቀቀች ትገኛለች ። በአየር በምድርና በባህር ሀይል ቴክኖሎጂዎቿ ከመሪዎቹ ተርታ ከመሰለፍም አልፋ በአንዳንድ የጦር ዘርፎች መሪዎቹን መምራትም ጀምራለች ። በተለይም በሰው አልባ የጦር ጄት ወይንም ድሮን ቱርክ ከአለም ቀዳሚ መሆኗን ከአዘርባጃን እስከ ዩክሬን አስመስክራለች ።

አሁን ደግሞ ፊቷን ወደ ምድር ጦር በማዞር ከዘመኑ የቀደሙ ታንኮችን በማምረት ተጠምዳለች ። እናም ቱርክ የትኛውም ፀረታንክ መሳሪያ ሊመታው የማይችልን ታንክ ሰርታ ጨርሳለች ። ስሙንም አልታይ #Altay ብላዋለች ። ስያሜውም የቱርክ ነፃነት ለማስከበር በተደረገው ፍልሚያ የቱርክን ጦር እየመራ በግሪክ ወራሪ ላይ ከፍተኛ ድል የተቀጃጄውን የቁርጥ ቀን ልጅ ፈህረዲን አልታይን ለማሰብ የተሰየመ ነው ።

አልታይ ታንክ ጃቫሊንን ከመሰሉ የተራቀቁ ፀረታንኮች ራሱን መጠበቅ የሚያስችለው 360 ድግሪ የተገጠመለት ፀረታንክ መከላከያ አለው ። በዚህም መሰረት ይህ የቱርክ ታንክ ፀረታንክ ሚሳኤል ሲተኮስበት በተገጠመለት ሴንሰር መሰረት በፍጥነት በመለየት ራሱን ራሱን ሙሉ በሙሉ ከጥቃት ይሸፍናል ። ከመሸፈን በተጨማሪም በተገጠመለት ሚሳኤል ማውደሚያ የሚተኮሱበትን ሚሳኤሎች መትቶ ማክሸፍም ይችላል ። ከዚያም አልፎ ፀረታንኮቹ የተወነጨፉበትን አቅጣጫ በቅፅበት መለየት ስለሚችል ከቦታው ማፅዳትም የሚችል የተራቀቀ ታንክ ነው ።

ይህ አዲሱ የቱርክ ኩራት አልታይ 65 ቶን ክብደት ያለው ሲሆን በሰአት 60 ኪሎሜትር መክነፍም ይችላል ። እናም አዲሱ የቱርክ ታንክ ዩክሬይን ውስጥ እንደረገፉት የሩሲያ ታንኮች ለጥቃት ተጋላጭ አይሆንም ።

ቱርክ በቅርብ ጊዜ 1,000 የአልታይ ታንኮችን ለማምረት እየሰራች ትገኛለች ።

Seid Mohammed