Get Mystery Box with random crypto!

ልዩ መረጃ! ኤርትራ ከህወሓት ጥቃት እራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆ | Ethio News Media

ልዩ መረጃ!

ኤርትራ ከህወሓት ጥቃት እራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የኤርትራ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ዛሬ ግንቦት 09/2104 ዓ.ም. ባሰፈረው መልዕክት ህወሓት በኤርትራ ድንበር በኩል እና በምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ በሁለት ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ብሏል።

ጨምሮም በዚህ በህወሓት ሊሰነዘር ይችላል ላለው ጥቃት የመጀመሪያው ዒላማ "ኤርትራ እና የኤርትራ ሕዝብ ናቸው" ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ከወራት በፊት ከተደረገው ከባድ ውጊያ በኋላ ጋብ ብሎ የቆየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ጊዜ ነው የኤርትራ መንግሥት ይህንን ያለው።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ከህወሓት በኩል ሊሰነዘር ይችላል ላለው ሌላ ዙር ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው ገልጾ ነበር።

እያየለ ከመጣው የዳግም ጦርነት ስጋት በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለጥቂት ሰዓታት የቆየ ጥቃት ሰንዝረው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።

ዛሬ በኤርትራ መንግሥት ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሑፍ ላይ ግን ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ራማ እና ባድመ አካባቢ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት አጋጥሞ ነበር ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።

የኤርትራ መንግሥት ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም አቀፍ ሕግ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት እንደሆነ ያረጋገጠወን አካባቢ ህወሓት ዳግም ለመውረር በዝግጅት ይገኛል ሲል ከሷል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ህወሓት ሊከፍት ነው ላለው አዲስ ጥቃት በምዕራብ ወልቃይት፣ ጸገዴ እና ሑመራን መልሶ በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ለመክፈት አቅዷል ብሏል።

በመጨረሻም ከህወሓት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት የኤርትራ ሕዝብ እና መንግሥት እራሱን መከላከል ይችላል በማለት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ለዚህ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ ለቀረበው ወረራ ለመፈጸም የመዘጋጀት ክስ ከህወሓት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቦታል።