Get Mystery Box with random crypto!

ኢስራእ እና ሚእራጅ አሁን ያለንበት ወር የተከበረ በሂጅራ አቆጣጣር ረጀብ ይባላል። ይህ ወር | Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

ኢስራእ እና ሚእራጅ

አሁን ያለንበት ወር የተከበረ በሂጅራ አቆጣጣር ረጀብ ይባላል። ይህ ወር ትልቅ ወር ነዉ፡፡ምንነቱ ነዉ ትልቅ ቀን ያሰኘዉ??ኢንሻ አሏህ ከደርሱ እንማራለን,,,,,

አል- ቁድስ☞ቤተልሔም☞ጡሩ ሲናእ☞ ቁዱሱ (በመካና ሰማይ መኃል)
የኢስራእ መድረሻ(አል-መድነቱ ሙነወራህ፤መከቱል ሙከረማህ)

ኢስራእ እና ሚእራጅ አሏህ ለነቢያችን صلى الله عليه وسلم ላይ ከስጣቸው
ሙዕጂዛዎች(ተኣምራቶች) አንዱ ነው::

ይህም የተከሰተው በረጀብ ወር በ27ኛው ለሊት ነው

قال تعالى {{سبحان الذي أسرى بعبده ليلا من المسجد الحرام إلى المسجد أقصا الذي باركنا حوله لنريه من آياتنا إنه هو السميع البصير}}
አሏህ በተከበረ የቁረአን አንቀፁ ላይ
« ጥራት(ለአሏህ) ይገባው ባሪያውን የለሊት ጉዞ ከመስጊደ አል―ሀራም እስክ መስጊደ አል―አቅሷ እንዲጓዝ ላደረገው ይህ(መስጊደ አል―አቅሷ) ዙሪያው በበረካ የተሞላ እንዲሆን አደረግነው ይህንን ጉዞ እንዲያደርግ የተደረገው ተዐምራት ልናሳየው ዘንድ ነው እሱ(አሏህ) ሰሚና ተመልካች(የሆነ ጌታ) ነው።ይለናል

ኢስራእ ፦ማለት የሌሊት ጉዞ ሲሆን

ሚዕራጅ ፦ማለት ወደ ሰማይ ያረጉበት(የወጡበት) ሁኔታ ነው።

ما القصود من المعراج؟

ሚዕራጅ በማድረጋቸው ምንድን ነበር የተፈለገበት?

ما المقصود من المعراج هو تشريف الرّسولﷺ بإطلاعه على عجائب في العالم العلوي

መልእክተኛው ﷺሚዕራጅ (ወደ ላይኛው ዓለም ማረግን
(መውጣትን))
በማድረጋቸው የተፈለገበት መልእክተኛውንﷺ ማላቅ እና በላይኛው ዓለም ያሉ አስገራሚ ነገራቶችን ማሳየት ነበር።

ከተመለከቷቸው አስደናቂ ነገራቶች መካከል፦
①) በ 7ተኛው ሰማይ በይተ አል―መዕሙርን የተከበረ የሆነውን ቦታ አይተዋል፤ ይህ (በይተ አል―መዕሙር) የምድር ነዋሪዎች(የሰው ልጅ እና አጋንንት)ቂብላቸው ከዐባ እንደሆነው ሁሉ ለሰማይ ነዋሪዎችም(ለመላኢኮች) ቂብላቸው ይህ በይተለ አል―መዕሙር ነው ።

ታዲያ በዚህ በይተል መዕሙር 70,000 (ሰባ ሺህ)መላኢኮች በየቀኑ ይገቡና ይሰግዳሉ ከዛም ይወጣሉ ሰግደው የወጡት ሁለተኛ አይመለሱበትም ነበር
②) አሁንም በ 7 ተኛው ሰማይ ላይ ሲድረተ― አል ሙንተሀን ተመልክተው ነበር።
ይቺ ሲድረተ አል―ሙንተሀ ትልቅ ግዝፈት ያላት ዛፍ ስትሆን አሏህ ከፈጠረው ፍጥረት አንድም ውበቷን ለመግለፅ አይችልም(ቃላት ያጥረዋል)።
ስሪታቸው ከ ወርቅ የሆነ በሆኑ ቢራ ቢሮዎች ያሽቆጠቆጠች ናት ። የዛፋ መሰረት ከ 6 ተኛው ሰማይ ሲነሳ መድረሻዋ 7 ተኛው ሰማይ ነው።

③) በግዝፈት አሏህ ከፈጠራቸው ትልቅ የሆነውን ዐርሺንም ተመልክተዋል

ሌሎችንም ጭምር ...

መልእክተኛውﷺከጅብሪል ዐለይሂ ሰላም ጋር ከሲድረተ አል ―ሙንተሀ ብሀላ ተለያይተው ነበረ።

ከዛም ብቻቸውን የሶሪፈ አል― አቅላምን ድምፅ ሰምተው ነበር የዚህን የሶሪፈ አል ― አቅላም ድምፅን የሰሙት መላኢኮች ከ ለውሀል አል መህፉዝ የተፃፈውን ወደ ራሳቸው መፅሀፍ ሲገለብጡ ነበር።

እዚሁ ቦታ ላይ ሁነው ነበር በፍጡራን ባህሪ የማይገለፅ የሆነውን የአሏህን ንግግር የሰሙት

ከንግግሩም የ50 ሶላቶች ግዴታነትን ተገነዘቡ ።

ይህ ቦታ ከ ሲድረተ አል―ሙንተሀ በላይ ያለ ሲሆን

አንዳንድ ሰዎች እንደሚሉት አላህ ይጠብቀን እና አሏህ የሚገኝበት የመጨረሻ መኖሪያው ላይ ነበር ይላሉ ይህ ግልፅ የሆነ ክህደት ሲሆን ፍጥረታትን የማይመስለው አሏህ ለመኖሩ ቦታና አቅጣጫ አያስፈልገውም።

አንዳንድ ማስጠንቀቂያዎች
ወደ 6ተኛው ሰማይ በተመለሱ ሰዐት ነቢዩ ሏህ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም መልእክተኛውን ﷺ ጠይቀው ነበር ጥያቄውም፦
አሏህ በኡመተዎ(በህዝቦቾ)ላይ ስንት ሶላትን ግዴታ አደረገ?
መልእክተኛውም ﷺ
50 ሶላቶችን አሉ።

ነቢዩ ሏህ ሙሳም
*«ارجع وسل ربك التخفيف»*

ማለትም፦ ተመለስ ጌታህንም እንዲቀንስልህ ጠይቅ ማለታቸው

የተፈለገበት አሏህ በቦታ ተገልፆ እሱ ወዳለበት ቦታ ሂድ *ማለት ሳይሆን*

በዚህ አገላለፅ የተፈለገበት *ወህይ ወርዶልህ የሶላት ግዴታነትን የተረዳህበት ወደ ሆነው ቦታ ተመለስ* የሚል ነበር የተፈለገበት

አንዳንድ ሰዎች ከሚናገሩት ንግግር አሁንም ማስጠንቀቅ ይገባናል እሱም፦

«መልእክተኛው ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እና ጅብሪል የሆነ ቦታ ላይ ሲደርሱ ጅብሪልም አለ ይላሉ«እኔ ከዚህ በላይ ከተጓዝኩኝ ተቃጠልኩኝ ነገር ግን አንተ ከተጓዝክ አለፍክ» ይሄ አባባል ውሸት የሆነና ተቀባይነት የሌለው ነው።

ሌላው መልእክተኛው ﷺ ጅብሪልን ዐለይሂ ሰላም አሏህ በፈጠረው ትክክለኛ ቅርፁ ለ2ተኛ ጊዜ ተመልክተውታል።
①ለመጀመሪያ ጊዜ የተመለከቱት በመካ ውስጥ አጅያድ በተባለች ቦታ ከነ 600 (ስድስት መቶ) ክንፎቹ ሲሆን እያንዳንዱ ክንፎቹ የሰማይን እና የምድርን አድማስ ሸፍኖ ይይዝ ነበር በዚህ ሰአት ነበር ልክረ ሲመለከቱት መልእክተኛው ﷺ ራሳቸውን የሳቱት

② በዚች በተባረከች ለሊትም ለ 2 ተኛ ጊዜ አሏህ በፈጠረው ትክክለኛ ቅርፁ ተመልክተውታል

ይህንን አስመልክቶም አሏህ በተከበረ የቁርአን አንቀፁ ላይ ይለናል
*{وَلَقَدْ رَءاهُ نَزْلَةً أُخْرَىٰ عِنْدَ سِدْرَةِ المُنْتَهَىٰ}*١٤ سورة النجم
ማለትም፦
*«በርግጥ ለ 2 ተኛ ግዜ በሲድረተ አል―ሙንተሀ ላይ ተመልክቶታል»*

ነገር ግን በ2 ተኛ ጊዜ ምልከታቸው እንደ መጀመሪያው ራሳቸውን አልሳቱም ነበር ልቦናቸው ብርታት እና ጥንካሬ ታክሎበት ስለ ነበረ

ጅብሪል ዐለይሂ ሰላም ወደ መልእክተኛው ሶለ አሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀርቦም ነበረ በመካከላቸው የሁለት ክንድ እና ከዛም ያነሰ እርቀት እስኪኖራቸው ድረስ

ይህንን በተመለከተ አሏህ እንዲህ ብሎናል
*{ثُمَّ دَنَا فَتَدَلَّىٰ【 ٨】فَكَانَ قَابَ قَوْسَيْنِ أَوْ أَدْنَىٰ【٩】* سورة النجم
ማለትም
ከዛም ቀረበ ያለው ርቀት 2 ክንድ እና ከዛም ያነሰ እስኪሆን ድረስ

የዚህን የቁርአን አንቀፅ ትርጉም በተመለከተ ዓኢሻ ረዲየ አሏሁ ዐንሃ እንደተናገረችው «እኔ ከዚህ ኡማ (ህዝብ) የመጀመሪያው ጠያቂ ነኝ በዚህ አንቀፅ ላይ ማን እንደተፈለገበት »ትላለች።

*فقال " إنما هو جبريل لم أره على صورته التي خلق عليها غير هاتين المرتين"*

መልእክተኛወምﷺበዚህ የተፈለገበትማ ጅብሪል ነበር አሏህ በፈጠረው ቅርፁ ከሁለቱ እይታ ውጭ ሌላ አላየሁትም ነበር ።ብለዋል

በዚህ የቁርአን አንቀፅ አንዳንድ ሰዎች እንደሚቃጥፉት አይደለም የተፈለገበት

ይላሉም በዚህ የቁርአን አንቀፅ አሏህ ነበር የተፈለገበት ይላሉ በነሱ አባባል ሲጠጋ፣ ሲቀርባቸው የነበረው እሱ (አሏህ)ነው ይላሉ በነሱ አባባል ይህ አባባላቸዉ የተሳሳተ መሆኑን ሁላችንም ልናዉቅ ይገባል

አሏህ ከጥመት ይጠብቀንና!