Get Mystery Box with random crypto!

✧ ነቢያችን (ሷለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በ « #ኢስራእ_እና_ሚእራጅ» ጉዞ ላይ ካዩዋቸው አስገራሚ | Ethiomewlid ኢትዮ መውሊድ

✧ ነቢያችን (ሷለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) በ
« #ኢስራእ_እና_ሚእራጅ» ጉዞ ላይ ካዩዋቸው አስገራሚ ነገሮች ↶
------------ ★ ------------
ሙጃሂዶችን (ፊ-ሰቢሊላህ/ለ አሏህ ብለው የሚታገሉት)ን ተመለከቱ በሁለት ቀናት ውስጥ በአንደኛው ቀን የዘሩትን በሚቀጥለው ቀን
በሚያጭዱ ሰዎች ምስል አዩዋቸው። ፈጣን በሆነ መልኩ ይዘራሉ፣ ያጨዳሉ። ጂብሪል እነዚህ በአላህ መንገድ «ፊ ሰቢሊላህ» የሚታገሉ ሰዎች ናቸው አሏቸው ። በአላህ መንገድ የሚደረገው ትግል ሁለት አይነት ነው::

➳ አንደኛው በመሳሪያ የሚሆን ጂሃድ ሲሆን
➳ ሁለተኛው ደሞ ማስረጃ በማቅረብ በዒልም የሚሆን ነው ።
➳ ይህ በማስረጃ የሚታገል ሰው ያ በመሳሪያ ጂሃድ ያደርገ ሰው ምንዳ ያክል አለው ።
➳ ዛሬ ባለንበት ጊዜ ጨለማ በበዛበት ጊዜ በጥሩ የሚያዝና በመጥፎ የሚከለክል ሰው፤ በተነሳሽነትና በጥንካሬ፤ በብርታት የሚሰራ ሰው በአላህ መንገድ ላይ የሚታገል ሙጃሂድ የሆነ ሰው ነው።
➳ ሙጃሂዶች በአኺራ ላይ ከፍ ያለ ደረጃ አላቸው ረሱላችን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ) እንዲህ አሉ፦
➳ [ሱናዬ በሞተበትና በጠፋበት ጊዜ ሱናዬን ህያው የሚያደርገ ሰው የሸሂድ አጅር አለው] ብለዋል [በዚህ ሐዲስ ላይ ሱና የተፈለገበት ሸሪዓ ነው] ረሱላችን የመጡበት መንገድ ማለት
ነው ፣ ማለትም አቂዳቸውን ያሰራጨ ያስተማረ ሰው ይህንን አጅር ያገኛል ።

--ኢስራእ እና ሚዕራጅ ብርሃናዊ ጉዞ---