Get Mystery Box with random crypto!

ነባራዊ መረጃዎች !! * ወልደያ ➢ ወልደያና አካባቢው ሰላም ነው ➢ ከወልደያ ወደ ደሴ፣ኮምቦ | Ethiomedia

ነባራዊ መረጃዎች !!
*
ወልደያ
➢ ወልደያና አካባቢው ሰላም ነው
➢ ከወልደያ ወደ ደሴ፣ኮምቦልቻና ሀይቅ የሸሹት ወገኖችም ተመልሰው ወደ ከተማዋ ገብተዋል, እየገቡም ነው
➢ በደሴና በኮምቦልቻ ባሉት ኬላዎች ላይ የሚሰሩት የፀጥታ ስራና ህዝብን የማረጋጋት ስራ ጥሩ ነው
➢ የወልደያ ህዝብ ለጥምር ጦሩ በሚገባ መልኩ እያገዙ ነው ደግፏቸው
➢ ጥምር ጦሩም ጠላትን ወደ ኃላ አዙሮ እየለበለበው  ነው ትናንት ማታ ተራራ ላይ ሰፍሮ የነበረው ሀይል ጧት ላይ ሲታይ የለም
➢ አሁንም ጥምር ጦሩ በወርቄል ፤ ዶሮ ግብርና ቃሊም ተጋድሎ እያደረገ ነው
➢ የጉራ ወርቄ ተጋድሎ ታሪክ አይረሰውም በአንድ ሰዓት 2 ሲኖ ሬሳ ረፍርፈዋል (ትናንት)
➢ በሮቢት ላይ የአየር ሀይል ጥቃት ተፈፅሟል ይህ ወራሪ ሀይልም ወደ ሀራና ኤሊውኃ ተበታትኗል
➢ በግዳን ወረዳ የሙጃ ከተማን ተቆጣጥሮ የላሊበላን መስመር ለመያዝ እና ሀራ ከተማን ለመያዝ ያደረገው ሙከራ አልተሳካለትም

በሰቆጣ
➢ አበርገሌ ገና ነፃ አልወጣም
➢ የአበርገሌ ወረዳን ነጻ ለማውጣት ጥምር ሀይሉ  አሁን የሞት ሽረት እያደረገ ይገኛል
➢  ትናንት ማታ የተወሰኑ የወራ*ው ታጣቂዎች  ወደ ዝቋላ ገብተው የነበረ ቢሆንም ንጋት ላይ ወጥተዋል ( በስልክ የተገኘ)
➢ በዝቋላ ወረዳ ስር የሚገኘው የቀዳሚት ቀበሌ ምሽግም ትናንት ተሰብሯል
➢ በዋግ ክፍል ፅፅሩ ላይም ጥምር ጦሩ እርምጃ እየወሰደ ነው

ወልቃይት
➢  በወልቃይት በኩል ጦርነቱ በሁለትጸ ግንባር ነው
   1ኛ :- በሁመራ በበረከት  እና
   2ኛ :- በሽሬ አቅጣጫ ነው።
➢ በሽሬ እስካሁን አንድ የህወሓት ምሽግ ተሰብሯል
➢ በበረከት ደግሞ ሱዳን የሚገኙ የህወሓት ታጣቂዎች የጀመሩት ነው

ኤርትራ
➢ ህዋ*ህት ትናንት ከሰዓት ጀምሮ እስከዛሬ ጥዋት ወደ ኤርትራ አዲ ፀፀር፣ አዲ ጎሹና ራማ  የማጥቃት ሙከራ አድርጓል       
➢ በዚህም የኤርትራ ሰራዊት በትግራይ የሰሜኑ ክፍል አዲያቦ ላይ ተገቢ እርምጃ ወስዷል እየወሰደም ይገኛል (ቻለው)

ማሳሰቢያ
1ኛ:- ሁሉም አካል ለጥምር ጦሩ የሚችለውን ያግዝ፣ ይርዳ ፣ ይዘጋጅ
2ኛ:- ህዝባችን ከሽብር እንታደገው ሽብር የሚነዙትንም ጥቆማ እንስጥ።
=============

ለቪድዮ ይህንን http://bit.ly/ethiomedia1

ለቴሌግራም  ይህንን https://t.me/ethiomedia2