Get Mystery Box with random crypto!

ሶሀቢዩ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?! T.me/ahmedin99 የአላህ መልእክተኛ (ሰዐ | Ethio iselamic gerup

ሶሀቢዩ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!

T.me/ahmedin99

የአላህ መልእክተኛ (ሰዐወ) አንዴ ከጂሃድ እየተመለሱ በምሽት መንገድ ላይ ማረፍ ፈልገው አንድ ሸለቆዋማ አካባቢ ላይ ሰፈሩ። መላው ሰራዊት እንዲተኛና እንዲያርፍ ፈልገውም:—

" እኛ ልንተኛ ነው ማነው የሸለቆውን መግቢያ በመጠበቅ ከድንገተኛ የጠላቶቻችን ወረራ ሊጠብቀን ፈቃደኛ የሚሆነው ?"ሲሉ ጠየቁ።

በዚህን ጊዜ ሁለት ሶሀባዎች ይህን ከባድ ኃላፊነት ለመወጣት ተስማምተው ስራ ጀመሩ ከዛም አንዱ ለሌላኛው "እኔ የሌሊቱን ግማሽ ልጠብቅ፣ አንተ ደግሞ ግማሹን ትጠብቃለህ ተራ በተራ እንተኛ"ተባባሉ።

በዚህም መሰረት አንደኛው ተኛ ሌላኛው እየጠበቀ ለይል ሰላት መስገድ ጀመረ። እየሰገደ ሳለ ቀን ላይ በተደረገው ጂሃድ ባለቤቱ የቆሰለችና ድንገት ከጉዞ ሲመለስ በዚህ ቆስላ ያገኛት ባሏ" ከነሱ መሀል አንድን ሰው ሳላቆስልና ደምም ሳላፈስ አልመለስም" ብሎ ዝቶ ከቤቱ የወጣው አይሁዲ ከነቢዩና ባልደረቦቻቸው ማረፊያ መግቢያ ላይ ሲደርስ እየሰገደና ጌታውን እያናገረ (ቁርኣን እየቀራ) የአላህን ባሮችን የሚጠብቀውን ሶሃቢይ ከቅርብ ርቀት ተመለከተው....በያዘው ቀስትም ወርውሮ ወጋው ሶሀቢዩም ቀስ አድርጎ አውጥቶት ሰላቱን
ቀጠለ፣ለሁለተኛ ጊዜም ደግሞ ወረወረ አሁንም ወጋው እንደመጀመሪያው ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሰላቱ ላይ ቀጠለ! በቀስት ሰውነቱን ቀጥታ እየተወጋ የማይወድቀውና የማይጮኸው ግለሰብ ሁኔታም እየገረመው ለሶስተኛ ጊዜ ወርውሮ ወጋው፣ ይህንም ቀስ አድርጎ አውጥቶ ጥሎት ሩኩዕ ከዛም ሱጁድ አድርጎ ከአጠገቡ የተኛውን አብሮት የሚጠብቀውን ሶሀቢይ ቀሰቀሰው እንቅስቃሴያቸውን ሲመለከትም አይሁዲው ቦታውን ጥሎ ጠፋ....

ሌላኛው ሶሀቢይ ልክ ሲባንን ዙሪያው በደም ተሞልቶ ሲመለከት ምን እንደገጠመው ጠየቀው የሆነውን በነገረው ጊዜም "ታድያ ምነው ልክ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደወጋህ አልቀሰቀስከኝም"? ሲልም ጠየቀው ይህ ልቡ በጌታው ቃል በቁርዓን ፍቅር የተሞላና ጥፍጥናውም ሁሉን ነገር ያስረሳው ውድ ሶሀቢይም "አንዲትን ሱራ ጀምሬ ነበር ሳልጨርሳት ማቆም አልፈለግኩም፣ ነቢዩ እርሳቸውንና ምዕምናንን የመጠበቁን ኃላፊነት ጥለውብኝ ባይሆን ኖሮ ነፍሴ እስካልወጣች ድረስ የሆነው ቢሆን ቁርዓኔን መቅራት አላቋርጥም ነበር" ብሎ መለሰለት!!!

ይህ ሶሀቢይ እኛን ቢመለከት ምን ይል ነበር?!
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)