Get Mystery Box with random crypto!

#የወፏ__ምክር አንድ ሰው አንዲት በጣም ቆንጆ ወፍ በመዳፉ ውስጥ ይዞ ጨምቆ ሊገድላት ሲል ከመሞ | Ethio iselamic gerup

#የወፏ__ምክር

አንድ ሰው አንዲት በጣም ቆንጆ ወፍ በመዳፉ ውስጥ ይዞ ጨምቆ ሊገድላት ሲል
ከመሞቷ በፊት አንድ ወይም ሁለት ቃላት ትናገር ዘንድ እንዲፈቅድላት ጠየቀችው፡፡
እንዲህም አለች “እባክህ አትግደለኝ፡፡ ሶስት ጠቃሚ ምክሮችን እሰጥሃለሁ፡፡
የመጀመሪያው ምክር፤ በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ፡፡ ሁለተኛው ምክር፤ ስለሆነው ነገር
ሁሉ አትቆጭ፡፡” ካለችው በኋላ ዝም አለች፡፡
ሶስተኛውንም ምክር ትነግረው ዘንድ ሲጠይቃት “ሶስተኛው ምክር ለልጆችህና ለልጅ
ልጆችህ በጣም ጠቃሚ ስለሆነ ካለቀከኝ አልነግርህም፡፡” አለችው፡፡
በዚህ ጊዜ ሰውየው ሶስተኛውን ምክር ለመስማት በጣም ጓጉቶ ስለነበረ ወፏን ሲለቃት
ከአንድ ዛፍ ላይ በርራ ወጥታ “ምንድን ነበር ያልኩህ? ታስታውሳለህ?” ብላ ጠየቀችው፡፡
እርሱም “በእጅህ ያለውን ነገር አትልቀቅ ነው ያልሺኝ፡፡” አላት፡፡
“ሁለተኛውስ?”
“ስላለፈው ነገር ሁሉ አትቆጭ፡፡”
“አዎ፡፡ ነገር ግን የነገርኩህን ነገር አልተቀበልክም፡፡ ባትለቀኝ ኖሮ ከሆዴ ውስጥ ለልጅ
ልጆችህ የሚሆን ወርቅ ታገኝ ነበር፡፡ ይኸው ነው፡፡” አለችው፡፡
ሰውየው “ሶስተኛውስ ታዲያ?” አላት፡፡
እሷም “ሶስተኛው የሁለተኛው ምክር ድጋሚ ነው፡፡ ስላጣኸው ነገር አትቆጭ፡፡ ይኸው
ነው፡፡ ደህና ሁን፡፡ ምክሬንም ባለመቀበልህ በድህነት ትኖራለህ፡፡” አለችው፡
ethio iselamic geru
ኢስላማዊ ሀዲሶችን ትኩስ ትኩሱን ያገኛሉ አላማችን ኡማውን ማገልገል ነው ለጓደኛዎ ሼር ያድር አንዲትም ቃል ብትሆን ከኔ የሰማቹትን ለሌሎች አስተላልፋ ብለዋል ረሱል ሰ ዐ ወ
ለአስተያየት( @Mahmmedinhabot)
ሼር(@ethioiselamdawa)