2022-01-28 19:32:54
ፌስቡክ እና ቢዝነስ
ስድስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ፌስቡክን ይጠቀማሉ። ፌስቡክን በቀላሉ ቢዝነስን ለማሳደግ መጠቀም ስለሚቻል የተጠቃሚው ኢትዮጵያ ውስጥ መብዛት ለቢዝነሶች ጥሩ ዕድል ነው።
ፌስቡክን ለቢዝነስ መጠቀም የሚቻልባቸው መንገዶች፦
የድርጅታችንን ወይንም የፌስቡክ ገጽ መፍጠር
ጓደኞቻችን እና የእነሱ ጓደኞች፣ የጓደኞቻቸው ጓደኞች፣ ወዘተ ገጻችንን እንዲከተሉ መጋበዝ
የድርጅታችንን ምርቶች፣ ዜናዎች፣ አዳዲስ ዕድሎች፣ ወዘተ በየጊዜው መለጠፍ
ለሚመጡ አስተያየቶች፣ መልዕክቶች፣ ወዘተ አስፈላጊ የሆነ መልስ መስጠት
ከድርጅታችን ቀጥታ ከተገናኙ ነገሮች በተጨማሪ ከቢዝነሳችን ጋር በቀጥታ ያልተገናኙ ግን የተያያዙ ነገሮችን (ዜናዎች፣ ፎቶዎች፣ ቪዲዮዎች) መለጠፍ፣ ማጋራት
ገጻችን ላይ ከቢዝነስ ውጭ የሆኑ እና አጨቃጫቂ ነገሮችን፣ ያልተረጋገጡ ዜናዎችን፣ ወዘተ አለመለጠፍ
ያልሆኑ ነገሮችን ኮመንት ላይ የሚጽፍ ሰውን ብሎክ ማድረግ
ሴኪዩሪቲውን በደንብ የተጠናከረ ማድረግ፣ ያለ አድሚን ፈቃድ ገጽ ላይ እንዳይለጠፍ ማድረግ
የግል ህይወታችንን ተሳስተን እንኳን የቢዝነስ ገጻችን ላይ አለማጋራት
በአንጻሩ ግን በቢዝነስ ገጻችን ላይ የምንለጥፈውን ነገር የግል ገጻችን ላይ ማጋራት
የቢዝነስ ስልክ ቁጥራችንን ገጻችን ላይ ማስቀመጥ
ባይ ሴል (Buy Sell) ግሩፕስን መቀላቀል እና ምርታችንን ወይንም አገልግሎታችንን ማጋራት
ለፌስቡክ ገጻችን የምንሰጠው የቢዝነሳችንን ወይንም የምርታችንን ስም መሆን አለበት
ስንጽፍ ፊደል አለመግደፍ፣ ግልጽ በሆነ ቋንቋ መጻፍ
የምንለጥፋቸው ጽሑፎች ምስል ቢኖራቸው የበለጠ ተመራጭ ይሆናል፣ ስለዚህ ሁሌም ትክክለኛ እና ከሌላ ያልተወሰደ ምስል ማጋራት
የግድ አስፈልጎን ያልተከለከለ (copy righted ያልሆነ) ምስል ወይም ጽሑፍ ከሌላ ቦታ ብንወስድ፣ ምንጭ መጥቀስ
የምርታችንን ወይንም የአገልግሎታችንን ቪዲዮ በየጊዜው መለጠፍ፣ ማጋራት
ከወደዱት ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉልን!
54 viewsEsrome, 16:32