Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioenku — ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioenku — ኢትዮጵያዊነት የኪነ-ጥበብ ሥራዎች በትረ ጊዮን ካስት ኤጀንት
የሰርጥ አድራሻ: @ethioenku
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 584
የሰርጥ መግለጫ

#ማንኛውንም አይነት #የቪዲዮ ሥራ በጥራትና በፍጥነት እንሰራለን::
#We do all kinds of #Video work efficiently and quickly
#በታማኝነት ልናገለግሎት ዝግጁ ነን
#We are ready to serve you faithfully
#ይደውሉ:-09-42-55-6130 / 09-24-54-83-65
#በውስጥ ማናገር ከፈለጉ
#If you want to talk inside
@Babilove12

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-26 21:18:27 #ምትኬ

ክፍል-16

#ደራሲ_HiLA

ዛሬ ሰናይትን ወደ ቤት አመጣታለሁ
ብሩኬ አስፈላጊውን ሁሉ ከከፈለ በኋላ መውጫ አፅፎ ተያይዘን ወደ መኪና ገባን እንደው ድንገት ዞር ስል ሰናይትን በደንብ አስተዋልኳት የዋህ መሳይ ፊት አላት ዝም ያለች ናት መልሶቿ ቁጥብና ቀዝቃዛ ናት በብዙ መከራ ውስጥ ማለፏን ገፇ ይመሰክራል እሷ ግን እንደው ጥንካሬውን አድሏታል መልኳ በዚ ሁሉ ውስጥ አልፋ እንኳን ቆንጆ ናት ያውም ጠይም አይኗ ከንጣቱ ትልቅነቱ ገና ሲያዩት ያስደነብራል ፀጉሯ ረጅም ባይሆንም ልክ እንደኑግ የጠቆረ ነው ሰውነቷ ደንደን ብሎ ሞላ ያለ ነው በአጠቃላይ የደስደስ ያላት ወጣት ናት ትንሿ ልጇ ከመዳፍም እምታልፍ አትመስልም እንደው ግን ባልተገለጡት አይኖቿ ባልተዘረጉት ጣቶቿ ፍቅር ታሲዛለች ሲያይዋት ውለው ቢያድሩ አሰለችም ትንሽዬ መልአክ ትመስላለች የሆነ የአምላክ አገልጋይ አይነት ምትሀት አላት በቃ አቅፌ ስይዛት ጠረኗ መአዛዋ ልክ የመቅደሱን እጣን አለኝ ንፁህ ያልጎደፈ እንዳው እሚያውድ የሆነ ሀይልማ ተሰጥቷታል ፈዝዤ እያየኀት እጇን እየሳምኩ ቤት ደረስን በቃ እናቴ እልል ብላ ተቀበለችን ሁሌም እሚገርመኝ ብሩኬ ቀና ብሎ አይኗን ማየት ይፈራል እማዬም ስለምታቅ እስኩ እስኪሄድ ዞር ትላለች፡፡
በቃ በደንብ ተቀበለችን ከሰናይት ጋር አስተዋወኳት ሁሉን አሟልታ ነበር የጠበቀችን ወይኔ እናቴ ፍቅር እኮ ናት እንደ በሀላችን አናቷን በቂቤ አንጀቷን በአጥሚት ትጠግነው ገባች ትንሽ አውርቻት ለእረፍት ገባሁ እማዬ የልጅቷን ስም ስጠይቃት ሴና መሆኑን ነገረቻት በጣም ስለገረመኝ ተመልሼ ለምን እንዳለቻት እና ትርጉሙን ጠየኳት
"ሴና ማለት በኤሮምኛ ታሪክ ማለት ነው ልጄ ታሪኬ በሷላይ ብዙ ታሪኮቼን መዝግቤ ይዣለሁ አይናን ሳየው ማንነቴን አስታውሳለሁ የትላንት ታሪኬን በሷ ገፅ ላይ ማንም ሊያነበው ይችላል እኔን ለማወቅ ሴናዬን ማየት በቂ ነው፡"
እውነቷን ነው የሁሉም እናቶች ታሪክ በልጆቻቸው ገፅ ይመሰከራል የነሱ መራብ ለኛ የጥጋብ መንስኤ ነው የነሱ መጎሳቆል የነሱ ሀዘን የነሱ የተመሰቃቀለ ህይወት ለኛ ነው ታሪካቸውን በኛ ለመፃፍ እኛን ለማኖር እናትነት ያልተገለጠ ገና ያልገባን ታሪክ ነው ሁላችንም የነሱ ሴና ነን፡፡
* * *
ቀኖች እርስ በእርስ እየተዋለዱ ወራትን ተኩ እነሆ ሰናይት ከወለደች ሁለት ከአስራአምስት ቀን ሆናት ልጇ ሴናም ክርስትና ልትነሳ አምስት ቀናት ብቻ ቀርተዋታል፡፡ እማዬም ሽርጉዱን ተያይዛዋለች የሰፈር ሰው ሁሉ የኛ ዘመድ እንደሆነች ነው ሚያቀው ፡፡ ብሩክና እማዬም ጥሩ ወዳጆች ሆነዋል ቤት ሲመላለስ እንደበፊቱ አይፈራም፡፡ እኔም ስራዬን በሚገባ ሁኔታ ወድጄውም ለምጄውም ነው እየሰራሁ ያለሁት የብሩኬ እናት ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ላይ ትገኛለች አንዳዴ እማዬ ጋር ትመጣ እና አምሽታ ተጫውታ ትሄዳለች፡፡ ብቻ ፈጣሪ ይመስገን ጥሩ ቤተሰባዊ ቅርበት አለን፡፡
የሴናዬ የኔ ልዕልት ክርስትናዋ ነገ ነው አጥቢያችን ከሆነው ቅዱስ ገብርኤል ቤተከርስቲያን ነው የምናስነሳት ብለናል ሰናይትም እኔ ክርስትና እናቷ እንድሆን ስጠይቀኝ እኔም ብሩኬም እማም ሁላችንም ነበር ደስተኛ የሆነው ሴና ፍቅር የሆነች ትንሽዬ ልዕልት ናት፡፡ በለሊት ሄደን የቤተክርስቲያኑን ስነስርዓት ካጠናቀቅን በኋላ ወደቤት ተመለሰን እናቴ ሁሉን አዘጋጅታ ስለነበር ጥሩ ድግስ አርጋ ጠበቀችን ሁላችንም በደስታ ነበር ያሳለፍነው ሲበላ ሲጠጣ አመሸን ብሩኬና እናቱ አምሽተው ሄዱ ቤትዬም ከእኔ ጋር አደረች፡፡
ነገሮች በመልካም መሄድ ቀጥለዋል ሰናይትም እናቴን እያገዘች ልጇን እያሳደገች ነው ሴናዬም እምታሳሳ እንቁ እየሆነች ነው፡፡ ብሩኬ እና ቤቲ ከኔ በላይ ከሴና ፍቅርም ሱስም ይዟቸዋል በየቀኑ ሳያዩአት አያድሩም፡፡ ሴናዬ እያደገች ሰናይትም እየተላመደች በመጣችበት ወቅት አንድ ቀን ጠዋት ሴና አምርራ ማልቀስ ጀመረች እኔ እና እማዬ ተሯሩጠን ወደ ክፍሉ ስንገባ ግን ባየነው ነገር ደነገጥን በህልሜም መሰለኝ አልተኛሁም ብቻ ደነዝኩ ከድንዛዜዬ ያነቃኝ የልጄ ሴና ለቅሶ ነበር፡፡

ክፍል 17 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
117 views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 15:53:10
ይፍጠኑ ይመዝገቡ
109 views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 21:13:16 #ምትኬ

ክፍል-15

#ደራሲ_HiLA

ሻወር ወስጄ ስወጣ እናቴ የኔን ክፍል ለሰናይት እያስተካከለች አገኘኋት አገዝኳት ለኔ ደሞ ከማዬ ጋር ልተኛ ተስማማን መጀመሪያ ሳሎን ተኛለሁስል እምቢ አለች እማ እምቢ ካለች አለች ነው በዛውም ምን እንደሚያስፈልግ ስጠይቃት ሁሉንም ነገረችኝ ድንገት ስለሆነ ወደ ቤተሰባችን የተቀላቀለችው ለአራስ የሚያስፈልጉ ነገሮች አልተሟሉም እነሱን ከገበያ ገዝቶ ማምጣት ሀላፊነት ተጣለብኝ ከታዘዝኩት መሀል ያው እናንተም እንደምገምቱት የገንፎ ፣ የአጥሚት እህሎች ዋነኞቹ ናቸው በተጨማሪም ልብስ ቂቤ ዳቦቆሎ የልጅ መታጠቢያ ዛንዚራ ብዙ ነገር ከእማዬ ጋር ቁጭ ብለን ፃፍን በመሀል
እማ" አልኳት እየተሽኮረመምኩ
"ወዬ ምትኬ ደሞ ምን ፈለግሽ አስተያየትሽን አቀዋለሁ"
"ምንም ግን የሆነ ነገር ልጠይቅሽ ነበር እማ"
" ምንድነው እሱ ?"
" እኔ ስወልድ እንዴት ነው ምታርሺኝ እማ"
" አይ የኔ ምትክ እኔ እናትሽ ወገቤን ታጥቄ ነዋ ማርስሽ አይደለም ለልጄ መተኪያ ለሌላት ቀርቶ ማንንም የማርያም አራስ አይደል የማርሰው አቤት ለሰርግሽስ ብትይ እንደው ድል አርጌ ነው ምድርሽ ደሞ ክብርና ማዕረግ ይዘሽልኝ ቀርቶ ለማንም አለሌስ ይደገስ የሌ እንኳን አንቺ ለወግ ማዕረግ በቅተሽልኝ አለሜን አሳይተሽኝ ሆሆሆሆ እንደው ፈጣሪ ለዛ ያድርሰን ፈቃዱን ይስጠን እንጂ እኔ እናትሽ አላሳፍርሽም ማርያምን ልጄ "
"አይ እማዬ ስወድሽ እኮ " እቅፍ አርጌ ጉንጯን ሳምኳት
"ኧረ አንቺ ልጅ አነቅሽኝ ሆሆሆሆ ልገይኝ ነው ወድያ ዞርበይ ምን ትላለች "
"እማ ግን ብሩክ ምን አይነነት ልጅ ይመስልሻል? ሳትዋሺ ይመጥነኛል? አይበዛብኝም እማ?"
"ማ እሱ ነው እንከን የለሽ ልጄ ላይ ሚበዛው እንደው ስለወደድሽው ነው እንጂ አይመጥንሽም እኔ እንደውም ምትክ ልሙትልሽ ሀገራችን ንጉስ ቢኖራት ለንጉስ በዳርኩሽ......" አይ እናት በሳቅ ፍርስ አልኩኝ አነጋገሯ በጣም ያስቅ ነበር
"እና ብሩክ አንግዲ እንደነገርሽኝ መልካም ሰው ይመስላል ፈጣሪ አመሉን አይቀይር እንደው እመቤቴ ከክፉ መንፈስ ትጋርደው ያው ጉድና ጅራት ከበስተኋላ አይደል ሚባለው ብቻ አንቺ ራስሽን ጠብቂ "
"ደግሞ አደራ በአንድ ሳትጣመሩ ወደ አልጋ እንዳትሄጂ ሴት ከነክብሯ ነውና ውበቷ አልያ ይንቅሻል ሙሉ ከሆንሽ አክባሪሽ ነው ልጄ ራሷን የማታከብር ማንም አያከብራትምና"
"እሺ እናቴ ቃል ገባለሁ በክብር ነው ምትድሪኝ"
"ምትክ ፈጣሪ የተባረከ ትዳር እንዲሰጥሽ አብዝተሽ ፀልይ ቤቱን ልጆቹን ሚስቱን አክባሪ እንዲያደርገው ለምኝ አየሽ የኔ ልዕልት ፀሎት ሀይለኛ መሳሪያ ነው ከፈጣሪ መገናኛ ድልድይ ነው እሺ ልጄ"
"እሺ እማ ውድድድነው ማረግሸ ያንቺ ልጅ በመሆኔ ክብር እና ምስጋና ለአምላክ"
" ታድያ መቼ ነው ምታስተዋውቂኝ?"
"እኔጃ ብቻ በቅርብ"
"ዛሬ ሀሙስ ነዋ?"
"አዎ እማ"
" በቃ እሁድ አምጪዋ ዝም ብለሽ አስተዋውቂኝ"
"እሁድ እእእእእ ልንገረው እሺ ቀጠሮ ከሌለው" ከዛም ብዙ አወራን ስለብሩክ ተወያየን ምሳ በላን ትንሽ አረፍ ልል ወደ መኝታ ቤት ገባሁ ራሴ መኝታ ቤት ምን አልባት ዛሬ የመጨረሻ ቀኔ ይሆናል እምተኛው ገብቼ የደከመ ሰውነቴን አሳረፍኩ እንቅልፍ ወሰደኝ፡፡
* * *
ስልኬ ደጋግሞ ሲጮህ ነቃው ብሩክ ነበር አናገርኩት እየመጣ መሆኑን ነገረኝ ተነስቼ መለባበስ ጀመርኩ ወጣሁ ብዙም ሳይቆይ ብሩኬ መጣ፡፡ ከብሩኬ ጋር ሄደን ሁሉንም ነገር ነገርናት ደስታ ሲያስለቅሳት እኔም አብሪያት አለቀስኩ ቀጥለን ከብሩኬ ጋር ተያይዘን ገበያ ወጣን ያስፈልጋል ያልነውን ሁሉ ገዛን ከዛም ቤቲ ጋር ደውዬ ያለችበት ሄደን ወሰድናት ሁለታችንን ቤት አድርሶን ወደ ቤቱ ሄደ፡፡
ከቤቲ ጋር እቃውን አስገባብተን እማዬ መልክ መልክ ካስያዘችው በኋላ ከቤቲ ጋር ብዙ አወራን እኔና እሷ በተገናኘን ቁጥር ወሬያችን ማብቂያ የለውም እማ ራት ብሉ ብላ ስጠራን ነበር መምሸቱ የታወቀን ነገም ስራ እንድታስፈቅድልኝ ነገርኳት በዛው ራት ከበላን በኋላ ገብተን ተኛን::

ክፍል 16 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
116 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 16:52:48 #ምትኬ

ክፍል-14

#ደራሲ_HiLA

አሁን ላይ እኔም በትንሹ ተረጋግቻለሁ ቢያንስ ድካሟን እንደቀነስኩ አስባለሁ እናቴ አለሜ ናት በስስት ስታየኝ አንዳች ስሜት ይፈጥርብኛል በተለይ ትንሽ የተጎሳቆልኩ ከመሰላትና ፊቴ ግርጥት ካለባት እንስፍስፍ ማንነቷ የተለየ ነው ሁሉም እናቶች ቃላት ባይገልፃቸውም የኔ እናት ግን ሁሉ ነገሬ ናት ሲከፋኝ አፅናኜ አማካሪዬ፤ስደሰት ፈገግታዬ ሀሴቴ፤ ሳጠፋ መምህሬ መንገድ መሪዬ ኩራዜ ገፃሼ እናቴ ለኔ እኔ ነች ሂወቴ ነች እስትንፋሴ ነች ስጦታዬም ጭምር ድካሟን ማንነቷን መመለስ ባልችልም ቢያንስ እሞክራለሁ የሷን ሀቅ ጥቂቷን መክፈል ባልችልም እጥራለሁ እናቴ አባትም እናትም ሆና ስላሳደገችኝ የእሷን ደስታ እንጂ ሀዘኗን ማየት አልሻም ፊቷ ከቶ እንዲከፋ አልፈልግም ስለናቴ ማውራት ከጀመርኩ ማቆሚያም ማብቂያም የለኝም፡፡ መቼም አሁን ከስራ መውጫ ቀደም ብዬ ስለመጣሁ ትጨነቃለች ሳታስብ ቀድሜ ካላስረዳኀት ለነገሩ እስካወራ አጠብቀኝም ቀድማኝ ነው ምታወራው የራሷን ሀሳብ ከጭንቀትና ከፍቅር አንፃር እምታወራው አይ እማ ትለያለች እኮ
"እማ እማ "
"ምትክ ምን ሆንሽብኝ በዚህ ሰአት አመመሸሽ ወይስ ምንድነው?" ይኸው እማ እንዲ ናት ለኔ ያላት ፍቅር
"ኧረ እናቴ ምንም አልሆንኩም ዛሬ ስራም አልገባሁ የሆነ ነገር ላማክርሽም ላስፈቅድሽም ነበር እንቀመጥ እማ"
"እሺ ግን ለምን ስራ አልገባሽም የትስ ነበርሽ ምትክ"
"እማ ልነግርሽ ነው አትቆጪኛ እማ ሙች መጥፎ ነገር አልተፈጠረም እውነት"
ከዛም ከመጀመርያው ጀምሬ ነገርኳት ከዛ እናቴ ፊቷ እየተቀየረ ማንበብ አቃተኝ ትስማማ ትናደድ አላቅም እኔም ግራ ገባኝ እማ አውርቼ እስክጨርስ ዝም ብላ አደመጠችኝ ልክ ስጨርስ የተወሰነ ደቂቃ ዝም ካለች በኋላ
"ልጄ አየሽ አባትሽ ስምሽን ሲያወጣ ሁሉን ማያዬ ብሎ ነው አንቺ ልጄ በመሆንሽ እጅግ ኮራለሁ አምላክ ባርኮ የሰጠኝ የመጀመሪያዬም የመጨረሻዬም ነሽ አንቺን ወደ መንገድ መርቼ መስመር ሰጥቼሻለሁ ቀራው ያንቺ ነው አንቺን ሳሳድግ አባትሽ በሚመኘው መንገድ በራስ መተማመን ያላት ጠንካራ በራሷ የምትመራ መልካምና ሰው አክባሪ ደግሞም ደፋርና ሽንፈት እማትወድ አርጌ ነው እና ልጄ ውሳኔሽን አስቢበትና እርግጠኛ ከሆንሽ አምጫት እኔ እናትሽ አላሳፍርሽም የማርያም አራስ ነች ፈጣሪ እስከፈቀደው ከኛጋር ትኖራለች "
አመሰግናለሁ እናቴ ወድሻለሁ በቃ ለብሩክ ልደውልለት እሱ ደስተኛ አልነበረም ግን እመኑኝ አታፍሩም በኔ ውሳኔ እሺ የኔ ልጅ እኔም የጀመርኩትን ልጨርስ ደግሞ ምትክ መቼ ነው እምታስተዋውቂኝ
በቅርብ እማ
ለብሩኬ ደውዬ ነገርኩት ከዛም ከምሳ በኋላ እንደሚመጣ እና አብረን እንደምንሄድ ተስማማን ለሰናይትም ምግብ እና ጁስ እንዲወስድላት ነገርኩት ተስማማን ከዛም ወደ ሻወር ገባሁ........

ክፍል 15 ይቀጥላል.....ከተመቻችሁ

#አስተያየት ካላችሁ...

@Babilove12

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
117 views13:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:42:05
130 views06:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 22:14:58 #ምትኬ

ክፍል-13

#ደራሲ_HiLa

"እኔ ደሞ አንተ የሆነ ነገር የሆንክ ነበር የመሰለኝ ከዛ አንዱን ስጠይቀው ምን እንዳለኝ ....." ያለኘኝን ሳላወራ ሳቅ ቀደመኝ በዚህ መሀል ብሩኬ የአንገት ሀብሉን አየው
"እናቴ ብሌኔ ፍቅሬን ተቀበልሽኝ? የኔ ሆንሽ? ነገሽ የኔ ሊሆን ገዬ ያንቺ ሊሆን ቤቴ አካሌ ልቶኚ ክብርሽ ኩራትሽ ልሆን ፈቀድሽ?"
"አዎ ብሩኬ ለኔ ካንተ የተሻለ ወንድ አላገኝም ሰው መሆን ገብቶሀል በመንገዴ የከተተህ ፈጣሪ እንጂ እኔ አይደለሁም እሱ የሰጠኝኝ ፍቅር ደግሞ መግፋት አልችልም፡፡ ብሩኬ ልቤም አይምሮዬም አንተን እያሰበ ነው አዎ ባሌ የልጆቼ አባት እንድትሆን ሙሉ ሰው እንድታደርገኝ መርጬሀለሁ"
ብሩክ ከአይኑ እምባ ሲፈስ ተመለከትኩ ግንባሬን ሳመኝ፡፡ በመሀል ስራ እንዳላስፈቀድኩ ትዝ ሲለኝ "ወይኔ ብሩኬ ስልክ መደወል አለብኝ ስራ አላስፈቀድኩም እኮ አንዴ ደውዬ ልምጣ?"
"እሺ እማ ሂጂ"
እኔ ስልክ እያወራሁ ስሄድ ብሩክ ደግሞ ወደ አራሷ ክፍል ገባ፡፡ ደውዬ ስራ አስፈቅጄ ተመልሼ ወደ ውስጥ ገባሁ ብሩክ ህፃኗ አልጋ አጠገብ ቆሞ በጉጉት ሲያያት አየሁት በዛው ቅፅበት የልጁ እናት መሆን ተመኘው ለሱ ማርገዝ ፈለኩ አንድ ቀን ጊዜው ሲደርስ እንደሚሆን ተስፋ አርጌ ወደ እናትየው አመራው
"እንዴት ነሽ ታድያ አሁን ሰናይት?" ስሟን ቅድም ካርድ ስንቆርጥ ነበር የሰማሁት
"ፈጣሪ ይመስገን እናንተን ባይጥልልኝ ምን እሆን ነበር ጌታ ይባርካቹ"
"አሜን ግን እኮ ትልቅ ነገር አይደለም ማንም የሚይረገው ነው....... ይልቅ ዛሬ እዚው ነው ምታድሪው የሚያስፈልግሽ ነገር ካለ ላምጣልሽ" በዚህ ሰአት ብሩክ ከኋላዬ ቆሞ ነበር፡፡
"አይ ምንም የለም አመሰግናለሁ"
"እሺ ነገ ወደ ቤትሽ ትሄጃለሽ አንዳድ መዘጋጀት ያለበት ነገር ካለ እኔና ብሌን ሄደን እንድናስተካክል ወይም እዛ ላለ ሰው እንድንናገር አድራሻሽን ስጪን አላት ብሩክ በዛ ሰአት ፊቷ በአንዴ ዳመነ አይኖቿ በእንባ ተሞሉ በሲቃ ድምፅ
" እኔ እኮ ቤት የለኝም ማለቴ የምኖረው ሸራ ወጥሬ ነው እና የኔ የምለውም ሰው የለኝም ለእግዜር ያለ ነው የሚያጎርሰኝ እናንተም ከዚህ በላይ አላስቸግራቹ ፈጣሪ መቼም የከፈተውን ጉሮሮ ሳይዘጋ አያድርም....." ብላ በሀሳብ እና በትካዜ አቀረቀረች ፊቷን ሳየው አንዳች ነገር እንባዬን ፈንቅሎ ከውስጤ አወጣው አሳዘነችኝ አንጀቴን ተላወሰላት ብቸኝነት ተስፋ ማጣት ድህነት መገፋት እነዚህ ሁሉ የሷን ማንነት ወርሰው ሌላ ሰናይትን ፈጥረዋል ልላት እምችለው ነገር አልነበረም እሷን እሚያፅናና ቃልም የለኝም ብቻ አንድ ነገር ትዝ አለኝ ቢያንስ እኛ ቤት ከእኔ እና ከእናቴ ጋር አብራ መቆየት ትችላለች ፈጠን ብዬ ብሩኬን ይዤው ወጣሁና "ብሩኬ እቤት ይዣት ልሄድ አስቤያለሁ እኛ ቤት እዛ ቢያንስ እስክትጠነክር ከኛ ጋር ትቆይ ከዛ ባይሆን እናስብበታለን"
"ማለት ብሌን አናቃትም እኮ በርግጥ ታሳዝናለች ግን ሌላ አማራጭ እንፈልግ ወይ ዘመድ እናፈላልግ ወይ የሆነ ነገር እናድርግ እንጂ ማዘርስ ምን ይላሉ?"
"ብሩኬ ሴት እኮ ነኝ እኔ በሷ ቦታ ብሆን ምን አደርግ ነበር ቅድም አላየሀትም ምንም መጠጊያ እንደሌላት ትንሽ ጊዜ ነው እባክህ?"
"እኔ ደስ አላለኝም ግን እሺ አማራጭ ከሌለን" በሀሳቤ ስለተስማማ በጣም ደስ አለኝ ተመልሼ ያለውን ነገር ነገርኳት ከደስታ ብዛት እንባዋን መቆጣጠር ተሳናት አነባች፡፡
ወደቤት ከብሩኬ ጋር ተመለስን በር ላይ አድርሶኝ ወደ ስራው ሄደ እኔ እናቴን ለማናገር ገባሁ፡፡
ብሩኬ ባይደሰትም ለኔ ሲል ተስማምቷል እማም ብትሆን እምቢ አትለኝም እኔ ደግሞ መንፈሰኔን አስደስታታለሁ፡፡
እናቴን እየተጣራሁ ወደውስጥ ገባሁ አረፍ ብላለች ስራ ስላቆመች አሁን ላይ እኔም በትንሹ ተረጋግቻለሁ ቢያንስ ድካሟን እንደቀነስኩ አስባለሁ......

#ክፍል 14 ይቀጥላል....ከተመቻችሁ

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
134 views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 20:10:13 #ምትኬ

ክፍል-12

#ደራሲ_Hila

ብሩክ ላበላብ ሆኖ ከተኛበት ደንግጦ ተነሳ፡፡ ሰአቱን ሲመለከት ከለሊቱ 9:45 ሆኑዋል ወርዶ ውሀ ጠጥቶ ተመልሶ ተኛ አንዳች ነገር ልቡን ደስ አለው፡፡
* * *
ጠዋት ከእንቅልፌ ስነቃ አንዳች የተለየ ቀለል ያለ ስሜት ነበር ሲሰማኝ የነበረው ብሩኬን መናፈቄ እጅግ በረታ ቢሆንም እንደማገኘው አውቃለሁ ስወጣ በር ላይ እንደሚጠብቀኝ አቅፎ እንደሚስመኝ ከምንም በላይ ሀብሉን በአንገቴ ሲያየው የተሰበረ ልቡን እንደምጠግንለት አቃለው፡፡ ቁርስ ከእናቴ ጋር ተመግቤ እናቴን ተሰናብቼ ስወጣ ብሩኬን በአይኔ ፈለኩት ከበሬ ባሻገር ከሚቆምበት ስፍራ መኪናውን በአየኔ ፈለኩ ግን አልነበረም ልቤ ተጨነቀ ለምን አልመጣም? ማታ አስከፍቼው ይሆን ወይስ ምንድነው የተፈጠረው? በር ላይ የተወሰነ ደቂቃ በሀሳብ እየባከንኩ ቆምኩ ግን የለም በዝግታ መንገዴን ቀጠልኩ የሰፈራችንን መታጠፊያ ጨርሼ ወደ አስፓልት ስወጣ ልቤ በድን ሆነ አይምሮዬ ማሰብ አቃተው የሆነ የሰው ብዛት ብቻ ይታየኛል ቀስ እያልኩ ስጠጋ የብሩኬ መኪና ነበረች ከዛ መላ አካላቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ ላብ በጀርባዬ ኮለል ብሎ መፍሰስ ጀመረ
* * *
"የኔ ልጅ ብሩክ እስቲ ና ተቀመጥ"
"ወዬ እማዬ ቁርስ በልቼ ወጣለሁ ብሌን ላይ መድረስ አለብኝ በጠዋት ላገኛት ፈልጋለሁ"
"እሺ ልጄ እሱን እረዳለሁ ግን ይቺን ልጅ አደራ ፍቅርህ እንደ ጉም እንዳይሆን በነፋስ የሚበተን አደራ ልጄ ከጅህ እንዳታመልጥህ ጠበቅ አርጋት ፍቅርህን በልቧ ላይ በእምነት ስራው ዙፋንህ እንዲሆን እምነትን ሰላምን ፍቅርን አፅንተህ ኑር አደራ"
"እሺ እማዬ በጣም አስፈራራሽኝ ደሞ አንቺ ከጎኔ ካለሽ ሁሉም ይስተካከላል...... በይ እማ ልሂድ እንዳታመልጠኝ ደና ዋይ"
* * *
እያዘገምኩ ሰው አጠገብ ስደርስ ሁሉም ያወራል ግማሹ የራሱን ግምት ይሰጣል አንዱን ጠጋ ብዬ "ይቅርታ አባት ምን ተፈጥሮ ነው ?" አልኩት በልቤ ክፋ እንዳያሰማኝ እየተማፀንኩ
" ምን አውቄ ሚስቱ ናት መሰለኝ መንገድ ምጧ መቶ ነው አሉ? ወይ የዘንድሮ ወንድ በቃ መላ ቅጡ የጠፋበት......." ከዛ በኋላ ሰውየው ያለውን አልሰማሁም በሰው ውስጥ እየተጋፋው ወደ ብሩክ መኪና ተጠጋሁ በዚሁ መሀል አንዱ ከመሀል " እስቲ ገለል በሉ መኪናውን አሳልፉት ነፍሰጡሯን ሆስፒታል ያድርስበት ሆሆሆሆ ዞር በሉ" ሲል ለመኪናው መንገድ ከፈቱለት አጠገቡ ደርሼ መስታወቱን አንኳኳው ቀና ሲል እኔ ነኝ
"ምንድነው?"
"ውይ እናቴ በነብሴ ደረሽ የሆነውን በኋላ ላስረዳሽ አሁን ጊቢና ይቺን ሴት ሆስፒታል እናድርስ"
"እሺ" አልኩት አንዴ እሱን አንዴ እሷን እያየሁ ወደ መኪናው ገባሁ አንድ ሌላ ሰው ጨምረን በአቅራቢያ ወዳለ የግል ሆስፒታል ገባን፡፡
ሆስፒታል ደርሰን አስፈላጊውን ሁሉ አሟላ፡፡ ግራ ቢገባኝም ለመጠየቅ ጊዜ አላገኘሁም ነበር እሷን ማዋለጃ ሲያስገቧት አብራን የነበረችውን ልጅ ዞር ብሎ " ብቻዋን ነው እንዴ የምትኖረው? ማለቴ የልጇ አባት የለም?"
" አለ ለማለት አያስደፍርም ለነገሩ በቁሙ የሞተ ነው እሷን ያሰቃያል እንጂ"
"ማለት አልገባኝም በሽተኛ ነው ወይስ በሀገር የለም"
"ኧረ ሙሉ ጤነኛ ነው በሀገርም አለ ግን ምን መሰለህ ሚስትና ልጆች አሉት በፍቅር አበድኩ ካለና ቅምጡ ካረጋት በኋላ ስታረግዝ ውሻ አረጋት ለምን እንደጠላት ስታጣራ ጉዱን ሰማች ያኔ አለም ጨለመችባት ስራም የላት ብቻ ታሳዝናለች"
አሁን ነገሩ ገባኝ ብሩኬ አያቃትም ግን እንዴት እሱ መኪና ገባች፡፡ እሱን እያሰብኩ ከውስጥ የህፃን ድምፅ ተሰማ ዶክተሩ ወደኛ በመምጣት
እንኳን ደስ አለህ የሴት ልጅ አባት ሆነሀል " አለው ቅናት ተሰማኝ ዞሬ ብሩክን ሳየው "ይቅርታ አባቱ አይደለውም እሷግን ደህናት ?"
"በጣም ይቅርታ አባቷ መስለከኝ ነው....."
"ምንም አይደል ያጋጥማል ዶ/ር"
"አሁን እሷ እና ልጇ ሙሉ ጤነኛ ናቸው ግን ድካም እና የአቅም ማነስ እናትየው ላይ ይታያል በእርግዝና ወቅት ጉዳት ነበረባት ለዛሬ እዚህ አድራ ነገ ትወጣለች መልካም ቀን"
"በጣም እናመሰግና"
በዚህ መሀል አብራን የመጣችው ልጅ ልታያት ወደ ውስጥ ስትገባ ትንሽ የማወራበት ጊዜ አገኘሁ
"ብሩኬ ምንድነው የተፈጠረው ?"
"ይኸውልሽ እናት ወደአንቺ እየመጣሁ መሀል አስፓልት ላይ ሲጯጯሁ አየሁ ለማረጋገጥ ስጠጋ እርዳታ ፈላጊ ሴት ናት በሂወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ልቤ አዘነ መርዳት እንዳለብኝ አሰብኩ ከዛ አንቺ መጣሽ በቃ ይሄነው የተፈጠረው"
"እኔ ደሞ አንተ የሆነ ነገር የሆንክ ነበር የመሰለኝ ከዛ አንዱን ስጠይቀው ምን እንዳለኝ ....." ያለኘኝን ሳላወራ ሳቅ ቀደመኝ በዚህ መሀል ብሩኬ የአንገት ሀብሉን አየው.....

#ክፍል 13 ይቀጥላል ከተመቻችሁ

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
131 views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-22 05:45:25 #ምትኬ
ክፍል11

#ደራሲ_Hila

"ብሌን አፈቅርሻለሁ "
ሲለኝ ደነግጬ በሩን ዘግቼ ገባሁ። መምጣቴን የተመለከተችው እናቴ
"ምትኬ መጣሽ የኔ ልጅ ቀንሽ እንዴት ነበር?"
"ደና እማ ጥሩ ነበር ደክሞኛል ልተኛ ነው እናቴ ደና እደሪ"
ብያት ቶሎ ወደ ክፍሌ ገባሁ፡፡ እናቴ ምንም አላለችኝም አልተከተለችኝም
ክፍሌ ገብቼ የሰጠኝን ስጦታ መክፈት ጀመርኩ ምን ይሆን ብዬ እየጓጓሁ ነበር
ስጦታውን ስከፍት ግን ያየሁትን ማመን አቃተኝ AFEKRSHALHU የሚል የወርቅ አንገት ሀብል ነበር በጣም ያምራል እንባዬ በጉንጮቼ ኮለል ብሎ ሲፈስ ታወቀኝ በዛው ቅፅበት የመኝታ ቤቴ በር ተከፍቶ እናቴ ገባች በእጄ የያዝኩትን ሀብል እያየች
"ምትክ ምንድነው የያሽው እስቲ አምጪ ?"
"እማ ብሩክ ነው የሰጠኝ እናቴ ምክርሽን ፈልጋለሁ ያሳለፍኩት ቀን ከባድ ነው እማ" እናቴን እያወራሁ እምባዬን መቆጣጠር አቃተኝ፡፡ አጠገቤ ቁጭ ስትል ጭኗ ላይ ጭንቅላቴን አስደግፌ ከመጀሪያው ጀምሮ ሁሉንም ነገርኳት፡፡ ታቀዋለች ግን እንዲቀለኝ ነበር ደግሜ የነገርኳት እስክጨርስ ምንም አላለችም ነበር፡፡ ጨርሼ ዝም ስል
"ምትክዬ"
"ወዬ እናቴ "
"አየሽ ፍቅር አስበነው ፈልገነው አይመጣም ደግሞም ገፍተነው አይሄድም አንቺ ለብሩክ የጎደለ ማንነቱን የጠፋ እሱነቱን ሰጠችው በሀብት በዝና የማይገኝ ጎዶሎነቱን ሞላሽለት፡፡ እናቱ ያጣችው የመሰላትን ልጇን የተነጠቀችውን ደሟን በፍቅር አስመለሽላት በመዘናጋት ለነሱ የሰጠሻቸውን ደስታ አንቺ እንዳታጪው ውለታና ፍቅር ለየ ቅል ናቸው አይገናኙም ኧረ እንደውም አንዱ አንዱን ያጠፋዋል ብቻ ግን ልጄ ቆም ብለሽ አስቢ ከራስሽ ተማከሪ ያንቺ ህይወት ነው"
ብላኝ ከተኛሁበት ቀና አርጋ ግንባሬን ሳመችኝ
"ምትክ የኔ ልጅ ጠንካራ ናት በራሷ የምትተማመን ጭምር"
ብላኝ ጥላኝ ወጣች
ትራሴን ታቅፌ ጋደም አልኩ አይምሮዬም ልቤም አንድ መስመር ላይ ተገናኙ ሁለቱም ብሩክን ያስባሉ ያፈቅራሉ ያለምንም ማመንታት ያንገት ሀብሉን ለበስኩት ፍቅሩን ተቀበልኩት

***
"እናቴ በጣም አፈቅርሻለሁ መቼም አልተውሽም አላስከፋሽም ሁሌም ባርያሽ ሆናለሁ"
"ብሩኬ እኔም አፈቅርሀለሁ ይሄ ቦታ ያምራል አይደል"
"በጣም እናቴ አረንጓዴ እኮ ነው በዛላይ የወፎቹ ዜሜ "
" ብሩኬ ፏፏቴዎቹ ድምፃቸው የልጅነት ህልሜ ይህ ቦታ ነበር "
"ብሌን ብሌን ወዴት ሄድሽ እናቴ የትነሽ እባክሽ ነይ ብሌ........ን" ብሩክ ብሌን ከአጠገቡ ምን እንደወሰደበት አጣት ቢጣራ ቢጮህ ቢሮጥ ብሌን ጠፋች "ብሌ.....ን ፍቅሬ ብሌ......ን" ከብዙ ሩጫና ጥሪ በኋላ ራቅ ያለ ቦታ ላይ ከአንድ እድሜያቸው ከገፋ ነጭ በነጭ ከለበሱ የመልአክ አይነት መልክ ካላቸው እናት ጋር በደስታ እየተፍለቀለቀች ታወራለች አጠገብዋ ሲደርስ
"ቆይ ብሌን የት ሄድሽ ይህን ገነት የመሰለ ስፍራ ብቻዬን አስጠላኝ አስደነገጭሺኝ የማጣሽ መሰለኝ እኮ"
"እንዴ ብሩክዬ ስጠራኝ ሰምቼሀለሁ እኮ ደሞ እያወራውህ ስለሆነ ነው"
በዚ መሀል አብረዋት የነበሩት እናት ደስ በሚል አንደበት በሚገርም ቅላፄ በሚጣፍጥ ንግግር
"ልጄ አይዞህ እናቷ ጋር መታ ነው አደንግጥ ደግሞ አትለይህም ተንከባከባት ይቺን እንቡጥ አበባ ሳትፈነዳ እንዳታደርቃት ወፏ በነፃነት እንድትበር ተዋት ያንተ ልብ ጎጆዋ ነው ብትበርም ጎጆዋን ትታ አትሄድም ካላፈረስከው በስተቀር ልጄ እጅህን ስጠኝ.... አንቺም የኔ ልጅ እጅሽን ስጪኝ"
ከዛ የሁለታችንንም እጅ ይዘው አንድላይ አጨባበጡን
"ልጆቼ አትለያዩም በአንድ ታስራችኀል በሉ ሂዱ ብረሩ ሂዱ"
የነበሩበት ቦታ ገደል ሆነ ወደታች ተምዘግዝገው መውረድ ጀመሩ፡፡
ብሩክ ላበላብ ሆኖ ከተኛበት ደንግጦ ተነሳ፡፡ ሰአቱን ሲመለከት ከለሊቱ 9:45 ሆኑዋል ወርዶ ውሀ ጠጥቶ ተመልሶ ተኛ አንዳች ነገር ልቡን ደስ አለው

#ክፍል_12_ይቀጥላል ከተመቻችሁ

#joine #share

https://t.me/Ethioenku
121 views02:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 10:11:46 Watch "የሕፃን ዲያቆን ሲሳይ የህይወት ታሪክ ። subscribe. " on YouTube


119 views07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-21 07:12:26 https://t.me/Ethiolove16?videochat=4561f34365e5e4c89a
108 views04:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ