Get Mystery Box with random crypto!

Ethio Construction

የሰርጥ አድራሻ: @ethioengineers1
ምድቦች: የውስጥ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 26.29K
የሰርጥ መግለጫ

በኮንስትራክሽን ዘርፍ ላይ ከዲዛይን ,ቅየሳ ጀምሮ እስከ ፊኒሺንግ ሁሉንም
👷‍♂እናማክራለን
🏢ዲዛይን እናደርጋለን
📚ሙያዊ ድጋፍ እና እገዛ እናደርጋለን
🏗በጥራት እና በጊዜ ፍጥነት እንገነባለን
📲 0953138434(eng sintayehu melese) ወይም
tiktok
https://www.tiktok.com/@ethiocons
ለሃሳብ እና ኣስተያየት
@Ethiocon143bot ይጠቀሙ

Ratings & Reviews

1.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-09 21:35:17
አሳዛኝ_ዜና

ኢዩኤል ታዬወርቅ ሸዋታጠቅ ይባላል ተወልዶ ያደገው አዲስአበባ ኬንያ ኢምባሲ ከፍ ብሎ ልደታ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው።

እዩኤል (አቢቲ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ የኪነህንፃ ኢንጅነሪንግ 5ኛ ዓመት ተማሪ ነበር።

የፋሲካ በዓልን አያቱ ጋር አክብሮና እዛው ሲጫወት አድሮ በማግስቱ ከሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከመጣ ታናሽ ወንድሙ ጋር ወደቤተሰቦቹ ቤት ሲመለስ ኬንያ ኢምባሲ አካባቢ እየተሰራ ከሚገኝና 14 ፎቅ እርዝመት ካለው ፎቅ ላይ ተወርውሮ የወረደ ብረት ጭንቅላቱ ላይ መቶት በአበባነት እድሜው በአሳዛኝ ሁኔታ ተቀጥፏል።

#FirstSafety

https://t.me/ethioengineers1
5.4K viewsENG Sintayehu Melese, 18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-08 12:12:41
ይህ ማሽን ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ባለሀብት ይጥፋ?

በዚህ ዘመን ኮንስትራክሽን ማለት ይበልጡኑ ቴክኖሎጂ እና ማሽነሪ ነው። ከዚያም አመራርም አለ። በመሆኑም፣ ጥራት ያለው ግንባታን በተያዘለት ጊዜና በጀት ጨርሶ ለማስረከብ ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች ወሳኝ ናቸው።

ከታች በፎቶ የተቀመጠው የእግረኛ መንገዶችና የሕዝብ መሰብሰቢያ ግልጽ ቦታዎች ላይ ግንባታ ለማከናወን ጠቃሚነቱ ወደር የለውም።

ይህ ማሽን ሀገር ውስጥ የሚያስገባ ባለሀብት ቢጠፋ እንኳ፣ ማሽኑን መንግሥት ቢያስመጣው በተለይ ለኮሪደር ልማትና ተያያዥ  የፕሮጀክቶች ሥራዎችን በፍጥነት ለመጨረስ ተኪ የሚገኝለት አይደለም።


https://t.me/ethioengineers1
5.1K viewsENG Sintayehu Melese, 09:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 15:10:45
L- connection of tie beam

1- Rebars must cross like the fingers of a hand.

2- Put an additional rebar around the outer corner.

3- Extend hooked bars from the inside to the outside.


https://t.me/ethioengineers1
7.3K viewsENG Sintayehu Melese, 12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-04 08:44:12 ክፍያ ምሥክር ወረቀት/payment certificate/ 1. ቅድመ ክፍያ(Advance Payment Certificate) • ከ 20% እስከ 30%  ባለው ወሰን ውስጥ እንደ አሠሪው ፍላጎት ለሥራ ማስጀመሪያ የሚከፈል ክፍያ ነው፡፡ • ለዚህ ክፍያ ተቋራጭ ተመጣጣኝ በሁኔታ ላይ ያልመሠረተ የባንክ ዋስትና ያስይዛል፡፡ • አንዳንድ አሠሪዎች ተቋራጫቸው የባንክ ዋስትናውን መስያዝ የሚሳነው ሆኖ ከተገኘ፤…
6.5K viewsENG Sintayehu Melese, 05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-03 17:55:47
ጥያቄ

ወስን ተጠግቶ ለሚገነባ ግንባታ አዋሳኙ ባለመብት በአዋሰኝ በኩል ያለዉን የህንፃ ገፅ ለመስራት የመከልከል መብት አለው ወይስ የለዉም ?

#መልሱን_ቀጠይ_እመለስበታለሁ

ሳይት ላይ ያጋጠማችሁን ማገራት ለምትፈልጉ @Ethiocon143bot


https://t.me/ethioengineers1
6.2K viewsENG Sintayehu Melese, 14:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-29 16:21:13
የዱባዮ ቡርጂ አል አረብ ጂሜይራህ፣ በአለማችን ውስጥ ከሚገኙ ቅንጡ ሆቴሎች መካከል አንዱ ነው።

ይህ ሆቴል ከአለማችን ሠማይ ጠቀስ ሆቴሎችም በሦስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

ይሁን እንጂ፣ ከዚህ ረጅም ሕንፃ ውስጥ 39 ከመቶ የሚሆነው የሕንፃው አናት ክፍል ጥቅም አልባ (non occupied) ሲሆን፣ ሕንፃውን ለመገንባት 7.6 ቢሊየን ዳላር ወጪ ተደርጓል።

ቡርጂ አል አረብ፣ ያረፈው በሰው ሰራሽ ደሴት ላይ ከመሆኑም በላይ፣ ሕንፃው ከመሬት ጋር የሚገናኘው በድልድይ ነው።

https://t.me/ethioengineers1
8.8K viewsENG Sintayehu Melese, 13:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 11:02:06 የአዲስ ኮንክሪት ጥሩ ባህርያት /Properties of Fresh Concrete/

ኮንክሪት ለመብላለት/ለመደባለቅ/Mix/፣ ከቦታ ቦታ ለማንቀሳቀስ/to transport/፣ለማስቀመጥ/deposit/ እና ለመጠቅጠቅ/Compact/Vibrate/ ቀላል ወይም ምቹ ሆኖ ሲገኝ ጥሩ ነው።

የእነዚህ ጥምር ውጤት ኮንክሪቱ ከስራ ምቹነቱ ባሻገር ኮንክሪቱ ላይ የመግጠጥ ችግር እንዳይከሰት /resistance to segrigation/ የሚረዳ ይሆናል።

ከላይ የገለፅናቸውን ባህርያት ያሟላ ኮንክሪት «ምቹ»/Workable/ ነው ብለን የምንጠራው ይሆናል።

እንዚህን ባህርያት የሚያሟላ መሆኑን የምናተጋግጥበት የስራ ምቹነት/ፅኑነት ምርመራ/ workability test/ Consistancy test ይባላል።

የኮንክሪት workability ላይ ተፅዕኖ ሊያደርሱ የሚችሉ ምክንያቶች ምን ሊሆኑ ይችላሉ?

1ኛ.የውህድ ምጣኔ ትክክል አለመሆን/Mix ratio/

2ኛ. የጠጠር ወይም የአሸዋ የግርድፍ መጠናቸው/Gradation/ ወይም ቅርፅ/Shape/ልክ ያለመሆን

የኮንክሪት workability እንዴት ማወቅ እንችላለን?

በሳይት እና በቤተ ሙከራ ይህን የምናረጋግጥባቸው 4 መንገዶች አሉ።

እነዚህም

1. Slump test
2.Compacting factor test
3.Veebee test እና
4.Vibro workability test ናቸው።

ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት /Slump test /Cone test/ or /Sand test/

የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በቀላሉ በሳይት የሚተገበር የፍተሻ አይነት
ሲሆን የኮንክሪትን ለስራ ያለውን ምቹነት (Workability) እና ፅኑእነት
(Consistency) ለመለካት ይጠቅማል።

ኮንክሪት ስላምፕ ቴስት በየእያንዳንዱ የኮንክሪት ሙሌት ስራ ወቅት መሰራት ያለበት ሲሆን በምን ዓይነት የጊዜ ልዩነት ወይም በየስንት መጠን መሰራት እንዳለበት በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል።

ስላምፕ ቴስት በቀላል ወጪ የሚሰራ በመሆኑ ተመራጭ የመፈተሻ መንገድ ነው በዚህ ምክንያት ከ1922 GC ጀምሮ እስካሁን አገልግሎት ላይ እየዋለ ይገኛል።

የኮንክሪት ስላምፕ ቴስት ውጤት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ሁኔታዎች
(Factors influencing slump test result)

1- ለኮንክሪቱ  የተጠቀምናቸው ግብአቶች ባህርይ።

ለምሳሌ:  ስነውህድ (ኬሚስትሪ) ቅጥነት ፣ የቁሱ መጠን እና ስርጭት (particle size and distribution) ፣ እርጥበት ፣ የሲሚንቶ ግብአት እና እርጥበት የመያዝ አቅም

2- የኬሚካል አድሚክስቸር መጠንና አይነት መስተጋብር.

3- የኮንክሪቱ አየር የመያዝ አቅም።

4- ኮንክሪት ማቀላቀያ ማጓጓዣ ቁስ እና ዘዴ

5- የኮንክሪቱ ሙቀት መጠን /temperature/

6- የተጠቀምነው የውሃ መጠን

7- ለፍተሻ የተወሰደበት ግዜ

Slump test ለማድረግ የምንጠቀማቸው እቃዎች ምን ምን ናቸው?

ጉርድ የኮን ቅርፅ/Truncated cone/ :-ይህ ቅርፅ ማውጫ 30 cm
ቁመት የታችኛው ዲያሜትር 20 cm
የላይኛው ዲያሜትር 10cm ዲያሜትር ነው

Plate/መደብ/ :- ከብረት የተሰራ 16 mm dia. እና 60 cm ርዝመት ያለው
መጠቅጠቂያ ብረት/Compaction rod/

የስራ ቅደም ተከተሉ እንዴት ነው?

1ኛ. መጀመርያ የቅርፅ ማውጫ ኮን (mold ) ንፁ መሆን አረጋግጥ ኮንክሪቱ በቀላሉ ከሞልድ እንዲላቀቅ ቅርፅ
ማውጫውን ዘይት መቀባት አለበት።

2ኛ. ቅርፅ ማውጫውን (mold ) ትልቅ ዲያሜትር ባለው ጫፍ በኩል ወንፊት ባልሆነ ስሃን/plate/ ላይ ማስቀመጥ።

3ኛ. የቅርፅ ማውጫ (mold) በእኩል 4 layer በኮንክሪት መሙላት።

4ኛ. እያንዳንዱን የኮንክሪት ሌየር 25 ግዜ በመጠቅጠቂያው ብረት መምታት የአጠቃጠቅ ጉልበታቱ እኩል መሆን አለበት።

5ኛ. ኮኑ (mold) ከሞላ በኋላ ትንሽ ስፋት ባለው ጫፍ ላይ ያለ ትርፍ ኮንክሪትን በቅርፅ ማስወገድና መለሰን።

6ኛ. በርጋታ  ቅርፅ ማውጫውን
(mold) ወደላይ በመሳብ ከኮንክሪቱ ማለያየት።

7ኛ. ቀጥሎም ኮንክሪቱ ከቅርፅ ማውጫ (mold) ያለውን የርዝመት ልዩነት መለካት።

ማስታወሻ

ሳምፕሉ ከተወሰደ በሁለት ደቂቃ ውስጥ ቴስቱን መከወን አለብን።

ከቴስት በኋላ የምናገኛቸው የውጤት አይነቶች /Results to be/

True Slump

ይህ ከፍተሻው ምናገኘው ትክክለኛው ልኬት ነው።

ቅርፅ ማውጫው ከኮንክሪቱ ከተለያየ በኋላ ያለው የኮንክሪቱ ቁመት ከቅርፅ ማውጫው አንፃር የምናገኘው ልዩነት ነው።

Zero Slump

ዜሮ ስላምፕ ኮንክሪቱ አነስተኛ የውሃና
ሲሚንቶ /water-cement ratio/ያለው መሆኑን ያሳያል።

Collapsed Slump:

ይህ ከዜሮ ስላምፕ በተለየ
የኮንክሪቱን የውሃና ሲሚንቶ/water-cement ratio/ ምጣኔ ትልቅ መሆን ያሳያል እንዲሁም የኮንክሪቱ የእርጥበት መጠኑ ከፍተኛ በመሆኑ እና High workability mix መሆኑን ያሳየናል።

Shear Slump

ይህ ደግሞ የፍተሻው ውጤቱ ሙሉ
እንዳልሆነ ይነግረናል።


https://t.me/ethioengineers1
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, edited  08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 09:10:26
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ፕሌት any Size & thickness
ጄ ቦልት (ጥርስ ማዉጣትና ማጠፍ)

የተለያዩ  [modefic] ስራዎችን እንሰራለን።

ማንኛዉንም ብረታ ብረት እንገዛለን።

ስልክ 0994941706 ወይም 0910379303 ደውለው ያግኙን
ቴሌግራም ላይ ፦https://t.me/heavenic1

አድራሻ፦  ቁ 1.መርካቶ
                ቁ.2 አየር ጤና  ኪዳነ ምህረት

ጥራትና ታማኝነት መለያችን ነው።
ታምራት ፕሌት እና ጄ ቦልት አቅራቢ
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 09:10:25 HOW TO CHECK SAND QUALITY IN FIELD?
.

There are some useful tests that can be done in the field for checking
the quality of sand utilized for construction. The
following tests may
be performed to determine the characteristics of
sand.
FIELD TEST OF SAND:


1. Take a glass and add some water in it.
2. Add a few amount of sand in the glass. At that
point, shake it vivaciously and permit it to settle. If there is clay present in the sand, an apparent layer will be formed at the top level of sand.
3. Mix the sand into sodium hydroxide or caustic soda solution to
distinguish the presence of organic impurities.
If organic impurities
are present in the sand, the color of the solution
will be turned into brown.
4. Now take a squeeze of sand and taste it. If it is
salty that means salt is present in the sand.
5. Take little amount of sand in the hand, and then
rub it against the
fingers. If the fingers are recolored it means sand
consists of some
earthy materials.
6. The color of sand describes the cleanness of
sand. The size and sharpness might be examined by touching and
watching visually.
7. The sand may be examined by mechanical
analysis to know its
fineness, durability, void ratio etc.


https://t.me/ethioengineers1
1.9K viewsENG Sintayehu Melese, edited  06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-24 07:50:11
ፀግሽ ፕሌት እና ጄቦልት ማምረቻ ጅምላ እና ችርቻሮ መሸጫ

በበቂ ሁኔታ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች እደ ምርጫቹ ታገኛላቹ ከበቂ ሀሳብ ጋር

1 ፕሌት በሚፈልጉት ሳይዝ ቆርጠን ቀዳዳ አበጅተን እንሰጦታለን

2 ጄቦልት በሚፈልጉት የጥርስ መጠን እናም የቁመት መጠን ጥርስ አውጥተን አጥፈን እሰጦታለን

3 እንዲሁም ላሜራ 1ሚሊም እስከ 12 ሚሊም ለማስቆረጥ ካሰቡ እኛው ቆርጠን እናስረክባለን

4 ማንኛውም ላሜራ እንዲሁም ሌላ ብረት ቀዳዳ ሚበሳ ካሎት እበሳለን

5 ያጡት እቃ እኛ በሚገርም ሁኔታ ሞደፊክ እናረጋለን


እደው ምን አለፋውት ላሜራ መቁረጫ ቶርኖ ምን ለሁሉም ይጠይቁን ከብቁ ባለሞያ ጋር ሁሉም አለ

ሌላው ብቻ ሚፈልጉት ይዘዙን በታማኝነት በተባለው ቀን ያገኛሉ

መልካም ስራ ለራስ ነው
በዚህ ይደውሉ 0913061530
0923764834 ፀግሽ ፕሌት
2.2K viewsENG Sintayehu Melese, 04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ