Get Mystery Box with random crypto!

ከስነ-ፅሁፍ ዓለም

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiobooks — ከስነ-ፅሁፍ ዓለም
የሰርጥ አድራሻ: @ethiobooks
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.34K
የሰርጥ መግለጫ

✍ አዝናኝ፣ አስተማሪና ቁም ነገር የሚያስጨብጡ የብዕር ውጤቶች የሚቀርቡበት የናንተው ቻናል!
የቻናላችን https://t.me/Ethiobooks ቤተሰብ ሁኑ፣ ለወዳጅ ጓደኞቻችሁም 'share' አድርጉ።
ለአስተያየት፣ ስነ-ፅሁፋዊ ጥቆማና ማስታወቂያ
@firaolbm እና
@tekletsadikK ተጠቀሙ።

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-02-18 11:30:20 መቃሪዮስ ሳልሳዊ - 2
174 viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:00:31 መቃሪዮስ ሳልሳዊ - 1
216 viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 11:00:16
መ ቃ ሪ ዮ ስ ሳ ል ሳ ዊ
━━━━━━━
«መስቀልና ፖለቲካ»
@ethiobooks
220 viewsተስፋዬ መብራቱ, 08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 10:59:54
205 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 08:55:39 ጉ ስ ቁ ል ና
══✦══
ወንድወሰን በየነ
'
እዩት፤ እዩት - እማ!
እዩት ጉዱን! ጉስቁልና
በለሆሳስ ሲያንሾካሹክ፤
ሲያጫውተን! ዋዛ - ዋዛ
ሲያሽ - ሲያላፋን
ሲተሻሸን! መና - መና
ሲጓተት - ሲጎናተል
ሲያጓጉለን - በየፊና።
ላመሉ፤ ደርሶ ያፍቅሮቱን
ወዶልን!
የኛ - እኛይቱን፤
ቁርበት ብጤ ወና
ሙጥኝ - ቁርኝት! ዝምድና።
ከአች አምና፤
አቻም የለውና - እንዳምና!
ከድሮ - ኑሮ - ንሮ!!
ወደር የለውምና - የዘንድሮ!!
════════
የቁራ ጩኸት!
"ትንሽ ግጥም...!"
ጥቅምት 2007 ዓ.ም.

https://t.me/Ethiobooks
36 viewsተስፋዬ መብራቱ, 05:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 10:13:04
ስ ን ዴ



ስንዴ በማዶ፣ ይመስላል በረዶ።


ስንዴ በጭንቅ፣ ባለጌ በጥብቅ።


የስንዴ ዛላ፣ እፍኝ ይሞላ።


ስንዴ ካ'ለ፣ ፈታጊ አይጠፋም።


ደሞዙ ስንዴ፣ ሥራው የምን ግዴ።


የስንዴ አራራ፣ የቆንጆ መራራ።


ስንዴ፣ ምን አልኩህ ዘመዴ።


ብቅ ብቅ፣ እንደ ስንዴ ምርቅ።


ስንዴ ለመቁረብ፣ ዋስ ለማቅረብ።


የስንዴ ንፍሮ ያተር ድብልቅ፣
ከዚያችው ወጥተው እዚያችው ጥልቅ።


ስንዴ ካልሸተ፣ ሽማግሌ ካልሞተ።


ስንዴ ራቱ፣ ወይራ እሳቱ፣ ማለፊያ ሚስቱ፤
ለምን ሠርግ ይሄዳል ሠርግ አ'ለ ቤቱ።

       
   ነገር በምሳሌ
@ethiobooks
414 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-14 14:09:38
መድረሻህን ሳታልም ጉዞ አትጀምር፤
መኖርህን ሳታውቅ አትሙት።

እኛ፤ ሰዎችና የፈጣሪ ልጅ ፍጡሮች ነን፣ በዘመን መካከል የተገኘን፤ ዘር ሲያራርቀን፣ ሃይማኖት ሲለያየን፣ ሀብት ሲመዳድበን፣ ፖለቲካ ሲከፋፍለን፥ ሕይወትም ስንፈልጋት ስትጠፋ፣ ሳንፈልጋት ስትበዛ፣ ስንከተላት ስታመልጠን፣ ስንተዋት ስትከተለን እየባከንን የምንኖር።

ሕይወት፤ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች። የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው።

ሰው የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቆየት፤ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ለማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ...።

... የተሸከሙትን ለሕይወት የሚረባ ፍሬ፣ ዱር እንደበቀለና ሰው እንደማያገኘው መልካም ፍሬ የሚነካው ቀርቶ የሚያየው ሳይኖር ያፈራውን ተሸክሞ የሚኖር ዛፍ ዓይነት ሰዎች ምንኛ ያሳዝናሉ! ...
>>>
━━━━━━━━
ሜሎሪና - ስውር ጥበብ
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ

https://t.me/Ethiobooks
439 viewsተስፋዬ መብራቱ, 11:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 09:27:45
➦ በ1799 ዓ.ም. ተወልደው በ1850 ዓ.ም. የሞቱት ፈረንሳዊ ደራሲ ሆነር ደ ባልዛክ በመጨረሻው ጊዜ መጽሐፎቻቸውን የሚደርሱት በየቀኑ 18 ሰዓት ያለማረፍ ነበር። መጽሐፎቻቸውን በሚጽፉበት ጊዜ ነጭ የመነኮሳት ቀሚስ ለብሰውና ጠረጴዛቸው አጠገብ ቆመው ነበር። በዚህ ሁኔታ 21 ዓመት ጽፈዋል።


➦ የታወቁት ደራሲ ቻርልስ ዲክንስ አንዲት ደንቆሮ ድመት ነበረቻቸው። ደራሲው በሚጽፉበት ጊዜ የመኝታ ሰዓት ሲደርስ ድመቲቱ ከጸሐፊው ጠረጴዛ ላይ ትወጣና የሚበራውን ሻማ ታጠፋባቸዋለች። ቻርልስ ዲክንስም ተነስተው ይተኛሉ።


➦ በ1803 ተወልደው በ1869 የሞቱት ፕሮፌሰር ከንት ሊብሪ በፈረንሳይ ባሉ መጽሐፍት ቤቶች በሙሉ የበላይ ተቆጣጣሪ ሆነው ተሾሙ። ከንት ሊብሪ ከየመጽሐፍት ቤቱ እውቅና ድንቅ የሆኑትን መጽሐፍት ሰርቀው ወደ እንግሊዝ አገር ጠፍተው ይዘው ገቡ። በዚያም የሰረቁትን መጽሐፍ እየሸጡ ዕድሜ ልካቸውን ሀብታም ሆነው ኖሩ። ሀብቱም ከእሳቸው ተርፎ እስከ ልጅ ልጆቻቸው ደረሰ።


➦ ቻይናዊው ፊሽ ሼንግ በዘጠና ዓመት ዕድሜያቸው አንድ መቶ ቮልዩም መጽሐፍ የቻይናን ታሪክ ጽፈዋል። ሼንግ እነኚህን መጽሐፍት የጻፉት ቀደም ብለው አንብበዋቸው የነበሩትን መጻሕፍት በቃላቸው በማስታወስ ነበር። የቻይናው ንጉሥ ሁዋንግቲ "የቻይና ታሪክ ከኔ ቀጥሎ መኖር አለበት እንጂ፣ ከኔ በፊት ያለው መኖር አይገባውም" በማለት የቻይናን የታሪክ መጻሕፍት በሙሉ አሰብስበው አቃጥለውት ስለነበር፤ የቻይናን ያለፈ ታሪክ ለማዳን በማለት ሼንግ ያለፈውን የቻይና ታሪክ በቃላቸው ጻፉ።


➦ በ1645 ተወልዳ በ1700 የሞተችው አርማንዴ ቤጃርት በሁለት ዓመት ዕድሜዋ ታላቁን ፈረንሳዊ ደራሲ ሞሊየርን አገኘችውና አንገቱ ላይ ተጠምጥማ "የምወድህ ባሌ" ብላ ሳመችው። በዚያን ጊዜ የሞሊየር ዕድሜ ሃያ አምስት ዓመት ነበር። አስራ አምስት ዓመት ካለፋቸው በኋላ ሞሊየር 17 ዓመት ዕድሜ ያላትን አርማንዴ ቤጃርትን አገባት።

━━━━━━━━
ጳውሎስ ኞኞ
ስድስተኛው አስደናቂ ታሪኮች

https://t.me/Ethiobooks
404 viewsተስፋዬ መብራቱ, edited  06:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 10:00:20 ምን ዋጋ አለው
══❁══
ግርማ ተፈራ
@ethiobooks

[ወደ ኋላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
የትናንቱ ትውልድ የዛሬን ቢወቅሰው
[ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው]2× ]2×

ለመራራም ይሁን ለጣፋጩ ፍሬ
የትናንቱ ችግኝ ምክንያት ነው ለዛሬ
ቅብብል ነውና የትውልድ ጉዞ
የዛሬውም ነገር ይወልዳል አርግዞ
ምርቃት ቢያሰማን
አይጠቅመንም እርግማን
ማመስገንን ማድነቅን
ዛሬም እስካላወቅን
[ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው] 2×
[ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ] 2×
ያደፈርሳል ንፁሕ ፍቅር
ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር

የፊተኛ አልፎ የኋላው ሲተካ
ሁሉም ባንድ ሚዛን አይችልም ሊለካ
ተግባሩ ሲመዘን ቢለይም መጠኑ
የራሱ ልክ አለው ሁሉም በዘመኑ
ያኛው መሠረት ጥሎ
ይኼኛው አስቀጥሎ
መጪው እንዲጨርሰው
ፍቅሩን ካላወረሰው
[ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው] 2×


ወደ ኋላ ሄዶ ያንን ላይመልሰው
የትናንቱ ትውልድ የዛሬን ቢወቅሰው
[ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው] 2×

ሰጪም ተቀባይም በየበኩላቸው
በቅደም ተከተል ድርሻ ድርሻ አላቸው
ሰጪም በሰጠው ልክ ከተመዘነበት
ያጎደለው ካለ እሱም ዕዳ አለበት
ሁሉም ራሱን መርምሮ
ከስሕተቱ ተምሮ
ዛሬን እየቀየረው
ነገን ካላሳመረው
[ምን ዋጋ አለው ምን ዋጋ አለው] 2×
[ታሪክ ሲወሳ ትውልድ ወቀሳ] 2×
ያቀዘቅዛል የሞቀን ፍቅር
ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር

[ዘመን ሲነሳ ሁሌም ወቀሳ] 2×
ያደፈርሳል ቀጣዩን ፍቅር
ይቅር ይቅር ወቀሳው ይቅር።||


@ethiobooks
438 viewsተስፋዬ መብራቱ, edited  07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 09:52:17
424 viewsተስፋዬ መብራቱ, 06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ