2023-03-06 10:00:11
አበራ ለማ የተወለደው በ1943 ዓ.ም. ፍቼ
ሰላሌ ውስጥ ነው። እድገቱ ወሊሶንና አዲስ አበባን ያካትታል። ካገራችን ገጣሚያንና አጫጭር ልቦለድ ጸሓፊዎች አንዱ ነው። በኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነ ጽሑፍ ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የማዕርግ ተመራቂ ነው። ሙያው ጋዜጠኝነት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ሬዲዮና ፕሬስ መምሪያዎች ሠርቷል። ከጦር
ግምባር ጋዜጠኝነት እስከ ኪነጥበባት ዘርፎች ሃያሲነት ዘልቋል።
እስከ ሰማኒያዎቹ አሠርት አጋማሽ ድረስ፥
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ዋና ጸሃፊ ሆኖ አገልግሏል። ዛሬ የኖርዌይ ነዋሪ ነው።
በኖርዌይ ደራስያን ማኅበር ብቸኛውና
የመጀመሪያው ጥቁርና በአፍ መፍቻ ቋንቋው የሚጽፍ አባል ደራሲ ነው።
በዚህ ማኅበር ውስጥ የዓለም አቀፍ ኮሚቴው የረዥም ዘመን አባል በመሆንም ይታወቃል። ባለቅኔ ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድህንን በ1997 እ.ኤ.አ.፣ ስዊድናዊ/ኤርትራዊ የሆነውን የአስመራውን እስረኛ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ዳዊት ይስሐቅን በ2009 እ.ኤ.አ. ሃሳብን በነጻ የመግለጽ ሽልማት እንዲሸለሙ በእጩነት አቅርቦ ማሸለሙም ይታወሳል።
ከአበራ ለማ የታተሙ ሥራዎች፦
➦ ኩል ወይስ ጥላሸት፣ የግጥም መድብል 1967
➦ ሽበት፣ የግጥም መድብል 1974
➦ ሕይወትና ሞት፣ የአጫጭር ልብ ወለዶች መድብል 1975
➦ ሞገደኛው ነውጤ፣ 1976 ኖቭሌት
➦ አባደፋር፣ ከሌሎች ደራስያን ጋር ስብስብ 1978
➦ ጽጌረዳ ብዕር፣ ከሌሎች ገጣሚያን ጋር ስብስብ 1978
➦ የማለዳ ስንቅ፣ ያጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞች መድብል 1980
➦ መቆያ፣ ያጫጭር ልቦለዶችና ግጥሞች መድብል 1980
➦ ትዝታን በጸጸት፣ ያጫጭር ልቦለዶች ትርጉም (በጋራ) 1981
➦ አውጫጭኝ፣ የግጥም መድብል 1994
➦ ሙያዊ ሙዳዬ ቃላት፣ ኢልቦለድ 1994
➦ የእውቀት ማኅደር፣ ኢልቦለድ 1998
➦ እውነትም እኛ፣ የግጥሞች ስብስብ ቪዲዮ በዲቪዲ፣ ታህሳስ 2003
➦ ጥሎ ማለፍ፣ ታሪካዊ ልቦለድ
➦ ሽፈራው ሞሪንጋ ጥር 2003
➦ ቅንጣት - የኔዎቹ ኖቭሌቶች 2008
➦ ኩርፊያና ፈገግታ፣ የግጥም መድብል 2013
➦ የኢትዮጵያውያን ገጣሚያን ሥራዎች ወደ ራሽያ ቋንቋ የተተረጎመ በጋራ 1981 G.C.
➦ ULIKE HORISONTER - (ኖርዌጂያንኛ ግጥሞች) በጋራ 2003 G.C.
➦ ENKETRØSTREN (በኖርዌጂያን ኖቭሌቶች) 2017 G.C.
➦ TIME TO SAY NO፣ (የእንግሊዝኛ ግጥሞች) በጋራ 2014 G.C.
➦ ትውስብ - ያጫጭር ልቦለዶችና ኖቭሌቶች ስብስብ 2014 ፤ ይጠቀሳሉ።
ደራሲ አበራ ለማ በ2013 ዓ.ም. ሁለት ከፍተኛ ሽልማቶችን በኢትዮጵያ አግኝቷል፡፡ እነርሱም፦
1. ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን፣ በ2013 ዓ.ም. የሕይወት ዘመን ተሸላሚ ምርጥ ጋዜጠኛ
2. የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር የክብር ሜዳይ ሽልማት፣ በሥነ ጽሑፍ አስተዋጽኦ፣ 2013 ዓ.ም. ናቸው።
━━━━━━━
ዊኪፒዲያ
https://t.me/Ethiobooks
450 viewsተስፋዬ መብራቱ, 07:00