Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ASTROLOGY

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioastrology1 — ኢትዮ ASTROLOGY
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethioastrology1 — ኢትዮ ASTROLOGY
የሰርጥ አድራሻ: @ethioastrology1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.27K
የሰርጥ መግለጫ

<<ሰለ ኮከቦ ይወቁ>>
የተወለዳቹበት ወር ሰለናት እንደሚናገር ያውቃሉ?
Le cross ena ማስታወቂያ 👉 @unverseand

Ratings & Reviews

1.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-02-16 10:48:53 ከነሐሴ 18 እስከ መስከረም 13 ለተወለዱ በሙሉ።

»» ዞዳይካቹ ቪርጎ ይባላል
»» አብዛኞቹ ቪርጎዎች ድንግል ናቸው፣ እንደዛውም ቀበጦች አይጠፉም።

»» ጋብቻ ለቪርጎዎች ከበድ ይላል ፣ አንዴ ከገቡበት ግን ጋብቻን ያቁበታል።

»» ጩኸት እና ጫጫታ አያበዙም ፣ አልፎ አልፎ ካልሆነ ብቸኝነትን ያዘወትራሉ።

»» ለጥቃቅን ነገሮች ሁሉ ትኩረት ይሰጣሉ ፣ አስር ብር ከሃምሳ ሳንቲም ለሚያወጣ እቃ አስራ አንድ ብር ከፍለው አርባ አራት ሳንቲም ይጠብቃሉ፣ ግዜቸውንም ቢሆን እስከ ሰኮንዶች ወርደው ያሰላሉ።

»» ቪርጎዎች በየካፍቴሪያው ፣ በየሻይ ቤቱ ፣ በየመዝናኛው በየጭፈራ ቤቱ ማግኘት የሚከብድ ይሆናል፣ ይልቁንም በየቢሮ አምሽተው ይሰራሉ። ለፍፁማዊነት ያደላሉ፣ በከንቱ ህልም እና ለማይረባ ምኞት ግዜ የላቸውም፣ የተግባር ሰዎች ናቸው።

»» ሁሌም በሃሳብ እንደተዋጡ ነው፣ አይኖቻቸው ግልፅ ሆነው ፀጥ ያሉ ናቸው።

»» የቪርጎ ግዙፍ ብዙም አይተይም ፣ ብዙዋች ደቃቃ ናቸው ፣ ጥንካሪያቸው ግን ብረት ነው።
»» ስለመልካቸው ይጨነቃሉ ፣ ባገኙት እድል ና አጋጣሚ ሁሉ መስታዎትን ያያሉ ፣ በአለባበሳቸውም ቢሆን ሁሌም ሽክ እንዳሉ ነው።

በጣም ፅዱም ናቸው በገኙት አጋጣሚ ሁሉ ሻዋር ከመውሰድ አይተቀቡም »» ብርቱ ሰረታኞች ናቸው ፣ጭንቀት እና የስራ ብዛት ጤናቸውን ሊያዛባ ይችላል።
»» ቪርጎዎች ስድ የሆነ አነጋገር ፣ ብልግና እና ግዴለሽነት እብድ ያደርጋቸዋል።

»» ታመው ለተኙ ሰዎች ከሰማይ እንደተላኩ መላእክት የሚቆጠሩ ደጎች ናቸው።

»» ቪርጎዋች ሰለ አኗኗር ልማደቸውና ስለበህሪያቸው ሲነገራቸው ያንን ለመቀበል ይቸገራሉ፣ even አሁን የተፃፈውን ዞዳይክ ባህሪያቸውን እንኳን ምንም እኔን አይገልፅም እንደሚሉ እውን ነው።

»» የማንም ጥገኛ ተረጂ መሆንን አጥብቀው ይፈራሉ፣ ገንዘብን አለግባብ ቢሞቱ አይበትኑም፣ ቋጣሪ ነገር ናቸው ብክነትን ያወግዙታል ።

»» ቪርጎዋች እኔ ነኝ ያሉ ተቺዋች እና አቃቂር አዎጪዎች ናቸው፣ እነሱ ሲነኩ ግን ያማችዋል።
»» ቪርጎዋች ረጋና ቀዝቀዝ ያሉ ናቸው ፣ በምክንያት እንጂ በስሜት አይመሩም ፣ በቃላቸውም ይገኛሉ።
»» ቀጠሮ አክባሪ ናቸው ቀጠሮ ሚያረፍድ ስው አይወዱም።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
138 viewsedited  07:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:47:10 ከሐምሌ 17 እስከ ነሐሴ 17 ለተወለዳቹ በሙሉ።

»» ዞዳይካቹ ሊዮ ይባላል
»» ትምክታቸው ያስደነግጣል፣ ፈገግታቸው ደግሞ ያስደምማል። ለሊዮ ሰዎች ትእቢት የሞላበት ጉራ እና ፀሐይ ሞቅ ያለን ተጫዋችነት በአንዴ ይዞ መገኘት የተለመደ ነው።

»» ሊዮን ለማግኘት ከፈለክ በከተማው ውስጥ ብሩህና አንፀባራቂ ከሆኑ ቦታዎች አፈላልገው፣ ሊዮ ሰው ጨለማና ድባት ነገር አይወድም፣ ገዥ ብላኔቱ ፀሀይ ነች።
»» በቀላሉ የሚያፍር ሊዮ ማግኘት ይከብዳል፣ ፊቱ ከድካም እና ከጭፈራ ብዛት የተነሳ ቲማቲም ሊመስል ይችል ይሆናል እንጂ ወፍ።

»» ራሳቸውን በፍፁም ዝቅ አድርገው አይመለከቱም፣ ሆድ ይፍጀው የሚለው ነገርም የላቸውም፣ ዝምተኛ መስለው የሚታዩ ሊዮዋች አሉ ፣ በውስጣቸው ግን ጠንካሮችና ክብራቸውን የሚጠብቁ ናቸው።
»» ሴቷ ሊዮ ቀልጣፋ እና ደንጋጣ መስላ ትታያለች ፣ እንቅስቃሴዋ ግን በግርማ ሞገስ የተሞላ ነው። በሊዮ ገፅታ ላይ የአዛዥነትና የበላይነት መንፈስ ሁሌም እንደሰፈነ ነው፣ ንግግሩም የታሰበበትና በእርጋታ የተሞላ ነው።

»» ሊዮዎች ምክርን በነፃ መስጠት ያስደስታችዋል፣ ያፈቁሩታልም፣ ይህን ሲያደርጉ ካንተ በላይ አውቃለው በሚል መንፈስ ነው።
»» የሊዎዋች የበላይነት መንፈስ በቅንነት የተሞላ ነው። በብዙ ችሎታው ወደር የሌለው ነው ፣ የእኔነት ኩራቱ ግን ለጉዳት የተጋለጠ ነው።

»» አፍቅሬ ውዳሴም ናቸው፣ እጅግም ሲበዛም ብልጥ ናቸው። ፍቅር ምግባቸው ነው ፣ ፍቅርን ይወዳሉ፣ በሌሎች ትከሻ ላይ መደገፍን በፍፁም አይወዱም።

»» ሊዮዎች አባ ዝራው ናቸው ፣ ስስትና ቁጠባ ሊዮዎች በዞረበት አይዞሩም፣ ማእረግና ቅንጦትን ይፈልጋሉ፣ አንዲት ሊዮ ምን ቆጣቢ ብትሆንም በጣም ውድ የሆኑ ልብሶችን መግዛትዋ አይቀርም።
»» ሊዮ ታማኝ ጓደኛ፣ ኅይለኛም ወዳጅም ነው። ጠላትም ሲሆን እንደዛው ነው።

»» ስላክብርና ስላዝናቸውም ይጨነቃሉ ግን ደግ እና ሩህሩህ ናቸው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
132 viewsedited  07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:45:31 ከሰኔ 15 እስከ ሐምሌ 16 ለተወለዳቹ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ካንሰር ይባላል
»» ካንሰሮች በብዛት እና በግልፅ የሚታዩት ጨረቃ ሙሉ ስትሆን ነው፣ በጨረቃማ ምሽት አምረው እና ደመቀው ይወጣሉ፣ የጨረቃ ብርሃን ምግባቸው ነው ተፈጥሯቸው ከጭረቃ ብርሃን ገፅታ ጋ ይመሳሰላል።

»» የካንሰሮች ስሜት ይለዋወጣል ፣ ካንሰሮች ግን ሁሌም ያው ናቸው፣ የሚለዋወጠው ስሜታቸው ብቻ ነው።

»» ካንሰሮች ሁሉ የቀልድ ወዳጆች ናቸው፣ በሳቅ እና ጨዋታ ይፋፋሉ ግን ሁሌም አይገኝም እንደ ሙዳቸው ይጠፋል፣ ይመጣል።

»» ከብዙ ነገር መደበቅን ቢመርጡም አድናቆትን ግን አይጠሉም። የማስታዎስ ችሎታቸው ድንቅ የሚባልለት ነው። ኑሮ ያስተማረቻቸውን ትምህርት አይረሱትም።

»» የድሮ ነገር ሁሉ ያስደስታቸዋል፣ አሮጌ ጫማዎች እና ልብሳቸውን በፍፁም አይጥሉም፣ በክብር ይቀመጣል።

»» ካንሰሮች የሚስጥር ቋት ናቸው ትንሹም ትልቁም ሚስጥሩን ያካፍላቸዋል፣ የራሳቸውን ግን ወፍ የለም።

ለንብረታቸው አና ልጆቻቸው ማንንም አይሰሙም።
»» የሚፈልጉትን ነገር በቀጥታ አይናገሩም፣ ገደምዳሜ ናቸው
»» ጠንቃቆች ናቸው በጥንቃቄ ይጓዛሉ ስለነገው አጥብቀው ይሰጋሉ
»» እንደካንሰሮች ቤቱን የሚወድ የለም፣ ቤታቸውን እንደ መቅደስ ያዩታል።

»» ለምግብ ልዩ ፍቅር አላቸው ፣በነሱ ምግብን ማባከን ኅጢያት ነው፣ ገዝተውም ያስቀምጣሉ
»» የካንሰሮች ስሜት ጥልቅ ነው፣ የእናትነት ትእምርት ነው።

»» ካንሰሮች ገር፣ ደግ፣ ገራም፣ርጉና ትሁት ፍጥረት ናቸው፣ የጨረቃ እና የባህር ሞገድን ማያት ይወዳሉ።

»» አንድአንዴ በገሀድ የሌለን ጥቃት እና ነገር በምናበቸው ፈጥረው በፍርሀትና በስጋት ሲናጡ ሊታዩ ይችላሉ ።

»» ካንሰር ሴቶች ለእናትናት ምቹ እና ምርጥ ናቸው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
127 viewsedited  07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:43:33 ከግንቦት 14 እስከ ሰኔ 14 ለተወለዳቹ በሙሉ

»» ዞዳይካቹ ጄሚናይ ይባላል
»» አንዱ ጄሚናይ ሁለት ሆኖ ሊታይ ይችላል፣ ይህ ሚሆነው አይናችን ሰይሆን ጄሚናይ ሁለት ፍጥረት ስለሆነ ነው፣ ካንድ ቦታ ሰክነው አይገኙም።

»» ፈጣን አድማጭና ፈጣን ተናጋሪ ናቸው። አይነተኛዎቹ ጄሚኒዎች ቀጠንና ረዘም ይላሉ፣ ብዙዎቹ ደልደልና ከበድ ያሉ አይደሉም።
»» ከአንድ ነገር ላይ ሰክነው አይቆዩም እንቅስቃሴያቸው ፈጣን ነው ፣ቢሆንም ግን ግርማ ሞገስን የተላበሰ ነው።

»» ጓደኝነትን በፍጥነት ይመሰርታሉ፣ ትንግርታዊ የሆነ ተግባቦት ብቃት አለቻው።

»» በአንደበት ስልጠት ወደር አልባ ናቸው ፣ የአግቦ ንግግርም ያቁበታል፣ በብልህነትም ሆነ በብልጠት የሚስተካከላቸው የለም፣ አእምሯቸው በመብረቃዊ ፍጥነት ይሰራል

»» ምንም የማይጨበጡን ጄሚናዮች በአኳሪያሶች እቅፍ ውስጥ ሲገቡ ይረጋገሉ
»» ሴቷ ጄሚናይ ውብ መልክ ይኖራታል፣ በአንድ ግዜ በጣም ብዙ ነገር መስራት ትችላለች።

»» ጄሚናዮች ቀጠሮ አክባሪዎችም አይደሉም፣ ሁሌም ያረፍዳሉ። ከየትኛውም ዞዳይክ በተለየ እንቅልፍ ያስፈልጋችዋል ፣ ይህም እረፍት አልባውን አእምሮኣቸውን እረፍት ለመስጠት ይረዳል።

»» ሁሌም በፍለጋ ላይ ናቸው ፣ ይባዝናሉ። አንድአንዴም ምን እየፈለጉ እንደሆነም አያቁትም፣ ምናባቸው ድንበር አልባ ነው።

»» ጨዋታ አዋቂ፣ አበ መላ፣ ቀልጣፋ፣ ዲፕሎማት ቢሆኑም የያዙትን ከዳር ለማድረስ ግን ትግስት ያጥራቸዋል እውቀታቸውም ጥልቀት አይኖረውም

»» ጄሚናዮች ንግግር ላይ ብቻ ሳይሆን በጽህፈትም ላይ ጎበዞች ናቸው።

»» በመጀመሪያ እይታ ፍቅር ከሚይዛቸው ሴቶች ውስጥ 90% የጄሚናይ ሴቶች ናቸው። ፍቅርንም ቶሎ ነው ሚጀምሩት።

»» ጄሚናዮች በጣም በዙ አመት ይኖራሉ ፣ቶሎም አያረጁም፣ ከሌሎች ዞዳይኮችም በበለጠም ሞትን በጣም ይፈራሉ ።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
120 viewsedited  07:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:41:59 ከሚያዝያ 13 እስከ ግንቦት 13 ለተወለዱ ሁሉም

»» ዞዳይካቹ ቶረስ ይባላል
»» የቶረሶች አቋም ቀጥ እና ፀጥ ያለ ነው ፣ በደንብ ቀርበዋቸው እስኪያውቋቸው ድረስ መልሳቸው ሁሉ አዎ፣ አይደለም፣ ነው፣ አመሰግናለው ብቻ ይሆናል።

»» የእነሱ ፍላጎት አትንኩኝ፣ ተውኝ ነው፣ እንዲሁም በጠም ትግስተኛ ናቸው »» ወንዱ ቶረስ አንገቱ ወፍራም ወይም ጡንቻማ ሆኖ ጫንቃው ሰፊ እና ጠንካራ ይሆናሉ።

»» ብዙ ግዜ ወደ ተቃራኒ ፆታ አብዝተው ይሳባሉ፣ ቢሆንም ግን እናሱ ከሚሄዱ ይልቅ ሰዎችን ወደ ራሳቸው መሳብን ይፈልጋሉ።
»» ቶረሶች የቤት ሰዎች ናቸው ፣ ድሎትና ምቾትን ይወዳሉ፣ የመብል እና መጠጥ ያለቅጥ ወዳጅነታቸው ጤናቸውን ያውከዋል »» በጠም ግትር ናቸው።

ቶረስ ለገንዘብ እና ንብረታቸው እንደቤተሰቡ ሁሉ አክብሮት አላቸው »» ሰማያዊ፣ ሮዝ እና ሓምራዊ ቀለም ይወዳሉ ፣ ቀይ ግን በፍፁም አይስማማቸውም።

»» የማታ ማታ ስኬት ቤታቸው ትከትማለች፣ ቅንጦት ነገር ይወዳሉ
»» የቶረሶች ፍቅር ጥልቅ እና ዘላቂ ነው። ነፃነትን የማይሰጥና አስጨናቂ የመሆን እድላቸው ግን ሰፋ ያለ ነው።

»» የተረጋጉ እና የተደላደሉ ናቸው፣ አይዋከቡም፣ ለውበት የሚሰጡት ዋጋ ከፍ ይላል፣ በተለይ ቶራስ ሴቶች በዛ ባሉ ጌጣ ጌጦች የሚዋቡ ናቸው ።

»» አብዛኞቹ ቶረሶች መልክመልካሞች እና ቆንጆዎች ናቸው።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
120 viewsedited  07:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:38:30 ኮከቦን ይወቁ

ከመጋቢት 12 እስከ ሚያዝያ 12 ለተወለዱ ሁሉ

»» ዞዳይካቸው ኤሪስ ይባላል
»» ተግባቢነታቸው ልዩ ፣ ጉልበታቸው የትየለሌ ፣ ብርቱ ፣ ሀይለኛ ሰላም ብለው ሲጨብጥዎ እንኳን እጃቸው እንደብረት ሲሆን ፈገግታቸው ደግሞ ቅፅበታዊ ነው።

»» ኢ ፍታዊ ነው የሚሉትን ነገር ሳይውሉ ይቃወማሉ፣ የሚመስለቸውንም ከመናገር ወደኀላ አይሉም
»» የዋህ ናቸው ፣ መዋሸት አይቻለቸውም፣ ሁሉንም ፊት ለፊት ነው፣ ቢዋሹም ይታወቅባችዋል።

»» ከህይወት ዘመናቸው ውስጥ በአንደኛው በጭንቅላታቸው ወይም በፊታቸው ላይ ጠባሳ ጥሎባቸው በሚያልፍ አደጋ ውስጥ ዘለው ይገባሉ።

»» ኤሪሶች ጊዜ እና ሰው አይመርጡም፣ በአደገኛ መንገድ ያሰቡትን ለመፈፀም ይጓዛሉ። ብልሃት የላቸውም።

»» ኤሪሶች ሃሳባዊ ናቸው።
»» ሳያምኑት ቢቀሩ በታለቅ ድንጋጤ ይመለከትዎታል፣ መታመን ይፈልጋሉ።

»» ሴቷም ሆነች ወንዱ ትከሻማ ሲሆኑ በሚራመዱበት ጊዜ ሰውነታቸው ወደፊት ዘንበል ይላል።

Share Share

@ethiokokeb @ethiokokeb
@ethiokokeb @ethiokokeb
130 viewsedited  07:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 18:30:41 Good News #ሰበር_ዜና!!

በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው የተለዩት በቀድሞ ስማቸው እነ አባ ሳዊሮስ በዛሬው ዕለት በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው የይቅርታ ደብዳቤ ማስገባታቸው ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል ዘግቧል።

ዝርዝር መረጃ እንደደረሰን እናቀርባለን!!

 Share Share

@ethiozenanews1 @ethiozenanews1
131 viewsedited  15:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-06 11:00:14 በዛሬዉ እለት በጉራጌ ዞን የስራ ማቆም አድማ ተደረገ

በዛሬዉ እለት በ ጉራጌ ዞን መዲና በሆነችዉ ወልቂጤ ከተማ እና ሌሎች አካባቢዎች ላይ የስራ ማቆም አድማ መመታቱን ብስራት ራዲዮ ከነዋሪዎች አረጋግጧል። አድማዉ ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ጣቢያችን ሰምቷል።

ከትናንት በስቲያ የክልሉ መንግስት ህብረተሰቡ የስራ ማቆም እድማ ቅስቀሳ የሚያደርጉ አካላትን ጥቆማ እንዲሰጡት ጠይቆ ነበር።

የጉራጌ ዞንን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሚል በአዲስ መልኩ ለማደራጀት ዉሳኔ መሰጠቱ የሚታወስ ሲሆን የዞኑ መንግስትም ይህንን ተግባራዊ ወደ ማድረጉ ገብቻለሁ ብሏል።

ሆኖም የዞኑ ነዋሪዎች አሁንም ጥያቄዎች እንዳሏቸዉ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እያንጸባረቁ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እየተደረገ ያለዉ የስራ ማቆም አድማ ለአራተኛ ዙር መሆኑም ታውቋል።

Share Share

@ethiozenanews1 @ethiozenanews1
187 viewsedited  08:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 22:24:49 #Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የምዕመናን ድርሻ ምን መሆን እንደሆነ ገልጿል።

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው ብሏል።

በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ቤተክርስቲያን ሕገ ወጥ ስትል ያወገዘቻቸው አካላት ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ቦንጋ ለመግባት ሞክረው በሕዝበ ክርስቲያን እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ ከሽፏል ስትል አሳውቃለች።

በተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በኦሮምያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔና አካባቢው፣  በጅማ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ፤ በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ ፤ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አዲስ አበባ አዋሳኝ ከተሞች በሃይማኖታቸው ምክንያት በእሥር ላይ የሚገኙ ምእመናን መኖራቸውን ገልፃለች።

በርካቶች እየታደኑ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል ፤ አሁንም እየታሰሩ ነው ብላለች።

እነዚህ በእስር ላይ የሚገኙ ምዕመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል ስትል ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

Share Share

@ethiozenanews1 @ethiozenanews1
177 viewsedited  19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-05 22:06:35
#ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መዲና ቦንጋ ለመግባት ቢሞክርም በሕዝበ ክርስቲያን እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ ከሽፏል!!!

@በከፋ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙት 12 ወረዳ ቤተ ክህነቶች የቅዱስ ሲኖዶስን ውሳኔ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ላይ ሳሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥያቄያችን ካልተመለሰ የካቲት 5 ቀን ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል ብሎ መናገሩን ተከትሎ ለዛሬ የታሰበው ሰልፍ እንዲቀር ነገር ግን ሁሉም በተጠንቀቅ እንዲጠብቅ ይነገረዋል።

@በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ከቀኑ 9:00 ሰዓት አካባቢ ሕገ ወጡ ቡድን እየመጣ ነው መባሉን ተከትሎ የቦንጋ ከተማ አሥሩ አድባራት የሚገኙ ካህናትና ምእመናን በነቂስ ወጥተው የኦሮሚያ እና ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አዋሳኝ ወደ ሆነችው ጎጀብ ወደ ተባለችው ኬላ ደርሰው ከክልሉ የጸጥታ ኃይሎች ጋር በመሆን ኬላውን ዘግተው በመጠበቅ ላይ ሳሉ ሕገ ወጡ ቡድን ይደርሳል።

@ሕገ ወጡ ቡድን በኦሮሚያ ፖሊስ ታጅቦ ይደርስና እንገባለን አትገቡም ግብ ግብ ይጀመራል በዚህ ሁኔታ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የፖሊስ፣ ልዩ ኃይልና የሚሊሻ አባላት ከምእመኑ ጋር ሆነው በመከላከላቸው ወደ ጅማ መመለሳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

@በዚህ ሰዓትም ወደ ቦንጋ የሚያስገቡ መንገዶች ሁሉ ተዘግተው የመኪና እንቅስቃሴ ቆሟል። ሕዝበ ክርስቲያኑም በከፋ በሚገኙት በአሥሩም አድባራት ሆኖ ቤተ ክርስቲያንን በመጠበቅ ላይ ይገኛል።

@ከከፋ የደረሰን መረጃ)

@ምንጭ፦ ተዋሕዶ ሚዲያ

Share Share

@ethiozenanews1 @ethiozenanews1
146 viewsedited  19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ