Get Mystery Box with random crypto!

#Update ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለ | ኢትዮ ASTROLOGY

#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በነነዌ ጾም የሚከናወነውን ሥርዓተ ጸሎት አስመልክቶ ዛሬ በሰጠው መግለጫ የምዕመናን ድርሻ ምን መሆን እንደሆነ ገልጿል።

ሁሉም ምእመናን እና ምእመናት በጾመ ነነዌ በሦስቱም ቀናት ጥቁር ልብስ መልበስ፣ በጸሎት መርሐ ግብሩ ተገኝቶ ጸሎት መጸለይ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እና የአባቶችን መልእክት ሰምቶ መተግበር እንደሚገባው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል፡፡

የጸሎት መርሐ ግብሩም ጠዋት ኪዳን እና ምሕላ፣ ቅዳሴ፣ የሰርክ የዐውደ ምሕረት መርሐ ግብር እንዲሁም ማታ የቤተሰብ ጸሎት ናቸው ብሏል።

በመጨረሻም ምእመናን ለጸሎት ወደ ቤተ ክርስቲያን በሚሄዱበት ጊዜ ለጸሎት ከሚያስፈልጉ መጽሐፍት ውጪ ሌላም ምንም ዓይነት መፈክር ይዞ መምጣት የማይቻል መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ፤ የቤተክርስቲያኗ መገናኛ ብዙሃን ዛሬ ቤተክርስቲያን ሕገ ወጥ ስትል ያወገዘቻቸው አካላት ወደ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፤ ቦንጋ ለመግባት ሞክረው በሕዝበ ክርስቲያን እና በጸጥታ ኃይሎች ቅንጅት ዕቅዱ ከሽፏል ስትል አሳውቃለች።

በተጨማሪ መረጃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በኦሮምያ ክልል በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔና አካባቢው፣  በጅማ በምሥራቅ አርሲ አሰላ ፤ በምዕራብ ሐረርጌ ጭሮ ፤ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ አዲስ አበባ አዋሳኝ ከተሞች በሃይማኖታቸው ምክንያት በእሥር ላይ የሚገኙ ምእመናን መኖራቸውን ገልፃለች።

በርካቶች እየታደኑ በፀጥታ ኃይሎች ተይዘው ታስረዋል ፤ አሁንም እየታሰሩ ነው ብላለች።

እነዚህ በእስር ላይ የሚገኙ ምዕመናን ምግብና ውሃ እንዳያገኙ ተደርገዋል ስትል ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

Share Share

@ethiozenanews1 @ethiozenanews1