Get Mystery Box with random crypto!

ETHIO-CAMPUS

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_universitys — ETHIO-CAMPUS E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethio_universitys — ETHIO-CAMPUS
የሰርጥ አድራሻ: @ethio_universitys
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.63K
የሰርጥ መግለጫ

✓ ፈጣን እና ተዐማኒ መረጃ፣
✓ለተማሪዎች እና ለመምህራን አዲስ መረጃ
✓ ጥቅስ እና መዝናኛ ዘገባዎች፣
✓ የምሁራን እይታዎችና መጽሐፈቶች፣
✓ የአለም ሙሉ መረጃና የታሪክ መዛግብቶች ።
ለማንኛውም መረጃ ➥ @ethio_universitys

🎬 "ተመራጭ የዜና ምንጭ"
ሀሳብ አስተያየት ካላቺሁ
join:- @Bi_Default
https://t.me/joinchat/Tmro_CpxdgLAEdKu

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-04-29 09:25:53
956 viewsYaredo man, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 19:38:26 #ቅሬታ #AAU

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ሰሌዳ ሚያዝያ 24 እና 25 እንደሆነ ማሳወቁ ይታወቃል። ይህ የጊዜ ሰሌዳ ሚያዚያ 23 ወይም ሚያዚያ 24 የኢድ አልፈጥር በዓል የሚያከብሩ ሙስሊም ተማሪዎችን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን በመጥቀስ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታችንን አሰሙልን ብለዋል:: ከአድስ አበባ የሁለት ወይም የሶስት ቀን ርቀት ላይ የሚገኙ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ወደ ዩኒቨርሲቲው ጉዞ ሲያደርጉ የኢድ አል-ፈጥር በዓልን ከቤተሰብም ሆነ ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ሆኖው በጉዞ እንዲያከብሩ ይገደዳሉ:: በመሆኑም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጊዜ ሰሌዳውን ሙስሊም ተማሪዎችን ታሳቢ አድርጎ ማስተካከያ ያደርግበት ዘንድ ተማሪዎች እንዲሁም የተማሪዎች ወላጆች ጠይቀዋል።

፨ከዚህ በፊት በበዓል ቀናት ጥሪ አድርገው ከተማሪዎች በቀረበ ቅሬታ የጥሪ ቀን ማስተካከያ ያድርጉ ዩንቨርሲቲዎች መኖራቸው ይታወሳል።
1.2K viewsYaredo man, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 19:37:51 በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በማታና በእረፍት ቀናት በ2014 ዓ.ም የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር
----------------------------------
1. Business and Economics College

1.1 Main Campus (Weekend and Evening)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management
 Cooperatives Business Management
 Cooperatives Accounting and Auditing
 Tourism Management
 Hotel Management

1.2 Awada Campus (Weekend)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management
 Cooperatives Business Management
 Cooperatives Accounting and Auditing
1.3 Aleta Wondo Campus (Weekend)
 Marketing Management
 Management
 Accounting and Finance
 Economics
 Logistics and supply chain Management
 Cooperatives Business Management
 Cooperatives Accounting and Auditing

2. Social Science and Humanities College (Weekend and Evening)
 Psychology
 Sociology
 Anthropology
 Journalism and Communication (Weekend only)
 English Language and Literature
 Sidaamu Afoo and Literature
 Geography and Environmental Studies
3. Natural and Computational Science College (Weekend and Evening)
 Mathematics
 Statistics
 Chemistry
 Applied Physics
 Biology
 Aquaculture and Fisheries Technology
 Bio-Technology
 BSc in Sport Science
4. College of Education (Weekend and Evening)
 Educational Planing and Management
 Adult Education and Community Development
 Special Needs Education
5. Institute of Technology (Weekend and Evening)
 Computer Science
 Information Technology
 Information System
 Civil Engineering
 Construction Technology and Management
 Mechanical Engineering
 Electromechanical Engineering (Weekend only)
 Hydraulics and Water Resource Enginering
 Water Resource and Irrigation Enginnering
 Industrial Enginnering

6. Daye Campus (Weekend)
 Mathematics
 Biology
 Physics
 English Language and Literature
7. College of Agriculture (Weekend and Evening)
 Agribusiness and Value Chain Management (Weekend only)
 Human Nutrition
 Food Science and Postharvest Technology
 Rural Development and Agricultural Extension
 Agricultural Economics
8. Wondo Genet College of Forestry and Natural Resources-Shashemene Campus(Weekend)
 Urban Forestry and Greening
 General Forestry
 Agroforestry
 Forest Products Utilization and Management
 Enviromental Science
 Soil Resources and Watershed Management
 Natural Resource Management
 Natural Resource Economic and Policy
 Land Administration and Surveying
 Geographic Information Science
 Wildlife and Protected Area Management
 Ecotourism and Cultural Heritage Management


ምንጭ፡ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አሉሚኒ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት
948 viewsYaredo man, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-28 19:37:10 #ነጻ_የስልጠና_ዕድል

የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን ላጠናቀቃችሁ ተማሪዎች የተዘጋጀ ነጻ የስልጠና ፕሮግራም

ስልጠናው በ2013 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለምትገቡ የህይወት ክህሎታችሁን ለማዳበር የተዘጋጀ ነው።

ስልጠናው ልምድ እና ሙያዊ እውቀት ባላቸው አሰላጣኞች የሚሰጥ ነው፡፡

ክቡር ኮሌጅ ከደስታን ኮሚዩኒኬሽን እና ከአፍሪካ ቢዝነስ ሰኩልስ አሶሴሽን ጋር በመተባበር ስልጠናውን አዘጋጅተውታል።

ሰልጣኞች በመረጡት የኮርስ አይነት ከአንድ ሳምንት እስከ ሦሥት ሳምንት ድረስ በስልጠና ላይ የሚቆዩ ይሆናል።

ስልጠናውን ወስደው ለሚያጠናቅቁ ተማሪዎች ሰርተፍኬት የሚሰጥ ሲሆን ንቁ ተሳትፎ ላደረጉ የተመረጡ ተማሪዎች ነጻ የከፍተኛ ትምህርት ዕድል (Scholarship) ተመቻችቷል፡፡

እስከ ሚያዚያ 27/2014 ዓ.ም ድረስ የ2014 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት ኮፒ በመያዝ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል፡፡

የሚሰጡ ስልጠናዎች፦

በአመራር ክህሎት
ፕሮግራሚንግ
የስሜት ብልህነት (EQ)
ሮቦቲክስ
ፕረዘንቴሽን ክህሎት
የመግባባት ክህሎት
ፐርሰናል ብራንዲንግ
ግራፊክስ ዲዛይን
ጊዜ አጠቃቀም
መሰረታዊ ሊኑክስ እውቀት
ዌብ ዴቨሎፕመንት
የሥራ ፈጣሪነት አስተሳሰብ

0113698558
0904848586
880 viewsYaredo man, 16:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 17:03:00 በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ለተመረቁ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገር ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ከአራት ሺህ በላይ ተማሪዎች መደበኛ ዲግሪ ማግኘት ባለመቻላቸው ሥራ ለመቀጠር መቸገራቸውን ይገልጻሉ።

በተማሪዎቹ ቅሬታ ዙሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ የተጠየቁት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) "የተማሪዎቹ ሙሉ መረጃ ሳይገኝ መደበኛ ዲግሪ ለመስጠት እንደሚቸገሩ" ገልጸዋል።

"ሰላምና መረጋጋት በሰሜን ኢትዮጵያ በአስተማማኝ ሁኔታ ሲሰፍን ከመጡባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርት ያቆሙበት መረጃ ተሟልቶ ሲቀርብ ዲግሪው ይሰጣቸዋል" ሲሉ አክለዋል፡፡

እስከዚያው ግን በተሰጣቸው ጊዚያዊ ሰርተፊኬት ሥራ መፈለግ እንደሚችሉ ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።

በትግራይ ክልል ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተፈናቅለው በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት ተማሪዎች ግን "ትምህርት ሚኒስቴር በአንድ ሴሚስተር የውጤት መግለጫ ወረቀት/Grade Report አሰናብቶናል" ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ይህ ወረቀት ደግሞ በሥራ ዓለም ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠር እንደማያስችላቸው በመጥቀስ ሚኒስቴሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጠይቀዋል፡፡
970 viewsYaredo man, 14:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 17:02:37 #KotebeUniversityofEducation
#የጥሪ_ማስታወቂያ

በ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ምዝገባ ሚያዝያ 28 እና 29/2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ወደ ተቋሙ ስትሄዱ መያዝ የሚገባችሁ፦

• የ1ዐኛ እና የ12 ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰርተፊኬት
• ከ9-12 ክፍል ትራንስክሪፕት
• ፓስፖርት ሳይዝ ፎቶግራፍ (4)
• አንሶላ፣ ብርድልብስና የትራስ ልብስ
• የስፖርት ትጥቅ

ከተጠቀሱት ቀናት ውጪ የሚመጡ ተማሪዎችን እንደማያስተናግድ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።
842 viewsYaredo man, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 17:02:15 #WolaytaSodoUniversity

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ሚያዝያ 27 እና ሚያዚያ 28/2014 ሲሆን ተማሪዎች ግቢ በገቡ በማግስቱ Orientatin ወስደው ግንቦት 01/2014 ክላስ እንደሚጀምሩና ሰኔ 29/2014 የመጀመሪያ ሴሚስቴር እንደሚጠናቀቅ የዩንቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አፅድቋል።
798 viewsYaredo man, 14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 17:01:32 #AAU

የአዲስ ተማሪዎች ጥሪ ፦

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2014 የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ ሚያዚያ 24 ቀን እና ሚያዚያ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓስ ሪፖርት እንድታደርጉ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ የሚያስፈልጋችሁ ነገሮች ከላይ ተዘርዝረዋል አንብቧቸው።

ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት ሚያዚያ 26 ቀን 2014 ዓ.ም መሆኑን ተገልጿል።

ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም ከ https://portal.aau.edu.et ማግኘት ትችላላችሁ።

በሌሌላ በኩንል ፤ ተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2014 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከሚያዚያ 27 እና 28 2014 ዓ.ም እንዲያመለክቱ ዩኒቨርሲቲው ጥሪ አቅርቧል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ነው የደረሰን።
879 viewsYaredo man, edited  14:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 19:43:44 የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ከምደባ ውጪ ባሉ መርሃግብሮች የሚቀበሏቸውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን ጠየቀ!!

ባለስልጣኑ ለሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ትምህርት ተቋማቱ ከመንግስት ምደባ ውጪ በማታ እና በርቀት ትምህርት በራሳቸው መልምለው እንዲሁም የተለያዩ መስሪያ ቤቶች በአቅም ግንባታ ሲባል የሚልኳቸውን ተማሪዎችን እንደሚቀበሉ አስታውሷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ በሁዋላ በሚኖር የተማሪዎች ቅበላ ወቅት ሶስት ጉዳዮችን ልዩትኩረት ሰጥቶ መመዝገብ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
በተጨማሪም ፡-
- በግሉ አልያም በመስሪያ ቤት ለድህረ ምረቃ ለመመዝገብ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ከባለስልጣኑ መስሪያ ቤቱ ህጋዊነት እና ትክክለኛነት የተረጋገጠ መሆኑን ማጣራት

- በማንኛውም ደረጃ ከውጭ የተገኙ የትምህርት ማስረጃዎች በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የአቻ ግመታ የተሰጣቸው መሆን እና
- የቴክኒክ እና ሙያ የትምህርት ማስረጃዎችም በሚመለከተው አካል ህጋዊነታቸው የተረጋገጠ መሆን እንደሚገባው አሳስቧል፡፡

አያይዞም የሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተበራክተዋል ተብሎ ስለሚታመን፤ በትምህርት ተቋማቱ የሚሰሩ ሰራተኞችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን እንዲያረጋግጡ ይሁን ሲል አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ የተሰጠውን ተልእኮ ያለ ትምህርት ተቋማቱ ማሳካት እንደማይችል ያስታወሰ ሲሆን ዩኒቨርስቲዎች እያበረከቱ ላለውም አስተዋፅኦ እውቅናን እንደሰጠ የላከልን መረጃ ያመለክታል፡፡
1.3K viewsYaredo man, 16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-19 10:06:32 " ከ4 ክልሎች ተጨማሪ 8,080 ተማሪዎች ምደባ ያገኛሉ "

የትምህርት ሚኒስቴር ከዚህ ቀደም ይፋ ካደረገው ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ይገባሉ ካላቸው 152,014 ተማሪዎች በተጨማሪ 8 ሺህ 80 የሚሆኑ ተማሪዎችን ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲ እንደሚመድብ አሳውቋል።

ምንም እንኳን ጦርነት ሁሉንም ክልሎች በተወሰነ ደረጃ ተፅእኖ ቢያሳድርባቸውም ነገር ግን በተለየ ሁኔታ በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ አፋር እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የነበረው ሁኔታ በልዩነት እንዲታይ ተደርጓል።

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጠቀሱት አራቱ ክልሎች ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያቸው ፥ " የጦርነት ስሜት የፈጠረው ነገር ተማሪዎችን ጎድቷቸው እንደሆነ አስተያየት የሚደረግበት መንገድ እንፈልግ በሚል የክልል ትምህርት ቢሮዎች ተስማምተው ለትምህርት ሚኒስቴር የሰጡት ስራ አስተያየት የሚደረግበት ሁኔታ ካለ እንዲፈለግ " የሚል እንደነበር አስረድተዋል።

በዚህም ፥ በፊት ወደ መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች እንዲገቡ ከተቆረጠው ቁጥር 152 ሺ ተጨማሪ የሚገኝ ቁጥር ካለ ታይቷል ሲሉ ገልፀዋል።

በተለይም ፥ ከትግራይ ክልል መጥተው አራተኛ ዓመት ጨርሰው የሚወጡ ተማሪዎች ስለሚኖሩ የቅበላ ቦታዎችን ማግኘት ይቻላል በሚል ስራ ላይ ያሉት 43 ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን አቅም አሟጠው ወደ 8,080 ተማሪዎች የቅበላ ቦታ እንዳሳወቁ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የተገኘውን የተማሪ ቅበላ አቅም በፍትሃዊነት ለ4ቱ ክልሎች በጦርነቱ ምክንያት በተጎዱ ተፈታኞች መጠን እንዲከፋፈል መወሰኑንም አሳውቀዋል።

ምንም እንኳን የተገኘው የቅበላ ቦታ ለ4ቱ ክልሎች ይከፋፈላል ቢባልም በምን አግባብ እና መንገድ ተማሪዎቹ እንደሚለዩ እስካሁን በግልፅ የተብራራ ሆነ የታወቀ ነገር የለም።
1.2K viewsYaredo man, edited  07:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ