Get Mystery Box with random crypto!

ዶክተሩ ያወሩት ነገር አንድም ቀን ተግባራዊ ሲሆን ባናይም ዛሬም በህ/ተ/ም/ ቤት ተገኝተዉ እንዲ | ኢትዮ ዩኒቨርስቲ መረጃ

ዶክተሩ ያወሩት ነገር አንድም ቀን ተግባራዊ ሲሆን ባናይም
ዛሬም በህ/ተ/ም/ ቤት ተገኝተዉ እንዲህ ብለዋሌ:-

የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተናን ዲጂታላይዝ ለማድረግ/በኦንላይን ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የፈተና አሰጣጡን ሙሉ ለሙሉ አውቶሜት ለማድረግ ከቻይና መንግስት ጋር እየተሠራ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመዋል።

ለፈተናው የሚቀመጡ ተማሪዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በርካታ ታብሌት ኮምፒዩተሮች እንደሚያስፈልጉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በኮቪድ-19 ምክንያት አምራች ድርጅቱ ኮምፒዩተሮቹን በተያዘለት ጊዜ ማምረት አለመቻሉን ገልጸዋል።

ኮምፒዩተሮቹ በተያዘላቸው ጊዜ ከደረሱ በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የቀጣይ ዓመት ፈተና ኦንላይን እንደሚሰጥ አረጋግጠዋል።

ታብሌቶቹ በሚጠበቀው ጊዜ ካልደረሱ፥ መንግስት የፈተና ስርቆት የሚቀነስበት የተሻለ አሰራር በመከተል ፈተናው ይሰጣል ብለዋል።
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Join &
|||_Support us
@ethio_university_info
@ethio_university_info