Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተቋሙን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ካነሱት ሃሳቦች መካከል፤ | Ethio techs Link

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የተቋሙን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ካነሱት ሃሳቦች መካከል፤

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በ2024 በጀት ዓመት የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 10 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱን ገለጸ።

የሳፋሪኮም ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ዛሬ የቀረበ ሲሆን በኢትዮጵያ ስላለው እንቅስቃሴም በሪፖርቱ ተካቷል። በዚህም ወቅት በኢትዮጵያ የደንበኞቹን ቁጥር ወደ 3 ሚሊዮን ማሳደጉን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ሪፖርቱን ሲያቀርቡ በኢትዮጵያ ካላቸው ደንበኞች ውስጥ 2.1 ሚሊዮን የሚሆነው ንቁ ደንበኛ መሆኑን ጠቁመዋል።

በዚህም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ካሉት 3 ሚሊዮን ደንበኞች ውስጥ 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑት በተከታታይ ባሉ 90 ቀናት ውስጥ የሳፋሪኮምን ኔትወርክ መጠቀማቸውን ያመለክታል። ይህ ማለት ሳይጠቀሙ 90 ቀን ያለፋቸው ደንበኞች ንቁ ተጠቃሚ በሚለው ውስጥ አይካተቱም።

ይህ የንቁ ደንበኞች ቁጥር በሚጠቀሙት አገልግሎት ሲቀመጥ 2 ሚሊዮን የድምጽ፤ 1.4 የዳታ፤ 0.7 ሚሊዮን የጹሑፍ መልዕክት ተጠቃሚዎች ናቸው።

በሳፋሪኮም ኔትወርክ የሚጠቀሙ ደንበኞች በአማካይ በወር 55.4 ደቂቃ የድምጽ የስልክ ልውውጥ የሚያደርጉ ሲሆን 1.5 GB የሞባይል ዳታ ይጠቀማሉ።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞቹን ቁጥር በ2024 የበጀት ዓመት ወደ 10 ሚሊዮን ለማድረስ ማቀዱንና አሁን ካለው 1500 የኔትወርክ ሳይት ወደ 3000 የኔትወርክ ሳይት ለማሳደግ አቅዷል።

በአሁኑ ወቅት በ22 ከተሞች ላይ ኔትወርክ መዘርጋቱን ያስታወቀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ይህም 25% የህዝብ ሽፋንን እንደሚወክል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አንዋር ሶሳ ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።

ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድ እንዳገኘ ዛሬ የተገለጸው የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት አገልግሎቱን በኢትዮጵያ ለማስጀመር ለኢትዮጵያ መንግስት 150 ሚሊዮን ዶላር መክፈሉንም ገልጿል።

የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ አገልግሎቱን ለመጀመር የቴክኖሎጂ እንዲሁም ሌሎች ዝግጅቶችን አጠናቀው ፈቃዱን ሲጠባበቁ እንደነበር አስታውሰው በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ወደ አገልግሎት እንደሚገባ አረጋግጠዋል።

#MPesaEthiopia
#FurtherAheadTogether
#SafaricomET
Safaricom Ethiopia Facebook page
TikvahEth Magazine

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs