Get Mystery Box with random crypto!

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ፈቃድ አገኘ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሳፋሪኮም | Ethio techs Link

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ፈቃድ አገኘ።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሳፋሪኮም ኤም-ፔሳ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

የሳፋሪኮም ኬንያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ፒተር ንዴግዋ ዛሬ ንጋት ላይ የተቋማቸውን ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ሲያቀርቡም ይህንኑ አረጋግጠዋል።

በኢትዮጵያ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንድ ዓመት የሞላው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎቱ በሚቀጥሉት ሳምንታት አገልግሎት መስጠት ይጀምራልም ተብሏል።

ከቀናት በፊት የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ "ኤም ፔሳ" የመጀመሪያው የውጪ የሞባይል ገንዘብ አገልግሎት ሰጪ እንደሚሆን በመግለጽ በሁለት ሳምንት ውስጥ ፈቃድ እንደሚያገኝ ተናግረው ነበር።

#MPesaEthiopia
#FurtherAheadTogether
#SafaricomET
Safaricom Ethiopia Facebook page
TikvahEth Magazine

                   #Share
@ethio_techs @ethio_techs