Get Mystery Box with random crypto!

#EthioTechs_News ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ስለሚያስጀምረው 5G ኔትዎርክ ጥቂት መረጃዎች! | Ethio techs Link

#EthioTechs_News

ኢትዮ ቴሌኮም ዛሬ ስለሚያስጀምረው 5G ኔትዎርክ ጥቂት መረጃዎች!

- ይህ ኔትዎርክ በአለም ላይ መዘርጋት የጀመረው የዛሬ ሶስት አመት ነበር። ፍጥነቱም ከ4G ኔትዎርክ እስከ 100 እጥፍ ሊደርስ ይችላል።

- በአፍሪካ አሁን ላይ ደቡብ አፍሪካ፣ ኬንያ፣ ናይጄርያ፣ ሌሶቶ፣ እና ዩጋንዳ ይህንን ኔትዎርክ አስጀምረዋል። ኢትዮጵያ ዛሬ ስድስተኛዋ ሀገር ሆናለች ማለት ነው።

- ኢትዮጵያ ይህን ኔትዎርክ ለማስጀመር ለቻይናው ሁአዌይ ኩባንያ 40 ሚልዮን ዶላር ገደማ ክፍያ ፈፅማለች።

- 5G ኔትዎርክ በአሁን ሰአት በአለም ላይ ከፍተኛው የኢንተርኔት ግንኙነት ማግኛ ዘዴ ሲሆን ደቡብ ኮርያዎች 6G ኔትዎርክ ላይ ሙከራ እንደጀመሩ ታውቋል።

- 5G ኔትዎርክን በደንብ ያዳበሩት እና በስፋት እየዘረጉ ያሉት የቻይና ኩባንያዎች ናቸው፣ እንደ ሁአዌይ ያሉት እነዚህ ኩባንያዎች ግን በአሜሪካ እና አንዳንድ የበለፀጉ ሀገራት በደህንነት ምክንያት የ5G ኔትዎርኮችን እንዳይዘረጉ ታግደዋል።

*** እዚህም፣ እዛም ሳነብ ካገኘሁት ነው።

#Zola

#Share
@ethio_techs @ethio_techs