Get Mystery Box with random crypto!

#EthioTechs_News ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛው ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መ | Ethio techs Link

#EthioTechs_News

ኢትዮ ቴሌኮም የ5ኛው ትውልድ(5G) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት መጀመሩን ዛሬ አስታውቋል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ኩባንያው ላለፉት ወራት ያደረገውን ሙከራ አጠናቆ የ5ኛ ትውልድ ሞባይል ኔትዎርክ መጀመሩን ይፋ አድርገዋል፡፡

አገልግሎቱን በመዲናችን ውስን ቦታዎች ማግኘት እንደሚቻልም አሳውቀዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም የአገልግሎቱን ማብሰሪያ መድረክ ያከናውነው በሸራተን ሲሆን ፤ በዚሁ በሸራተን አካባቢ በአሁኑ ሰዓት 5G አገልግሎት በይፋ ጀምሯል።

በተጨማሪ በዩኒቲ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ ቸርችል ጎዳና እንዲሁም የኢትዮ ቴሌኮም መስሪያ ቤት አካባቢዎች የ5G አገልግሎት ተግባራዊ ሆኗል።

ኔትዎርኩ በቻይናው ሑዋዌ ኩባንያ አማከኝነት ነው የተዘረጋው።

እጅግ ፈጣን የሚባለውን የ5ኛ ትውልድ የኔትወርክ ቴክኖሎጂ ለመጠቀም ደንበኞች ከአገልግሎቱ ጋር የተስማማ የእጅ ስልክ እና የ5G ኔትወርክን የሚያቀርብ መሠረተ-ልማት ያስፈልጋቸዋል።

መረጀው ከኢትዮ ቴሌኮም፣ ከኢዜአ፣ ከኢትዮ ኤፍ ኤም እና ከጀርመን ሬድዮ የተውጣጣ ነው።

#tikvahethiopia

#Share
@ethio_techs @ethio_techs