Get Mystery Box with random crypto!

#MoE የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ስትራቴጂ | Top students

#MoE

የዲጂታል ትምህርት ስትራቴጂ እየተነደፈ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ስትራቴጂው በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት በመላ ሀገሪቱ ለመስጠት እንደሚያስችል በሚኒስቴሩ የአይሲቲና ዲጂታል ትምህርት ዋና ሥራ አስኪያጅ ዘላለም አሰፋ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ዓለም አቀፉ ኩባንያ 'ህዋዌ ቴክኖሎጂ' በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የአይሲቲ አካዳሚ መክፈት መጀመሩ ብዙ የአይሲቲ ባለሙያዎችን ለማፍራት እንደሚያስችል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ዘርፉ በቴክኖሎጂ የታገዘ መሆኑ ተማሪዎች ዓለም አቀፋዊ ዕውቀትን እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

ምስል፦ የሁዋዌ አይሲቲ አካዳሚ በቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሲከፈት

#ለፈጣን እና ታማኝ መረጃ



#share
#share



@ethio_schools
@ethio_schools
@ethio_schools