2022-06-27 22:05:48
ፓናማ ቦይ = Panama Canal
===========================
በዓለማችን ካሉ ገራሚና ወሳኝ የመርከብ መተላለፊያዎች አነዱ ፓናማ ቦይ(Panama Canal) ነው፡ ይህ "የውሃ ድልድይ" የፓሲፊክ (Pacific ocean) እና አትላንቲክ (Atlantic ocean) ውቅያኖስን የሚያገናኝ ሰው ሰራሽ ቦይ ሲሆን የሚገኘውም ሰሜንና ደቡብ አሜሪካ አህጉራትን በማገናት(የሁለቱ አህጉራት መለያ ድንበር) በመሳሳብ ወገበቧ በቀጠነችው አገር ዒዝመስ/Ithmus ፖናማ ነው።
ከአስፈላጊነቱ አንፃር በትክክል"ወሳኝ" የሚለው ከገለፀው ይህ ቦይ አንድ መርከብ ከአትላንቲክ ወደ ፓስፊክ ለመቅዘፍ በደቡብ አሜሪካ ጫፍ ኬፕ ሆርን ወይም በሰሜን አሜሪካ ሰሜን ዋልታ Arctic circle/north pole ቢሄድ በአማካይ እስከ 5940 ኖውቲካል ማይል (11,000 ኪ.ሜ )ን ወደ 44.27 ኖውቲካል ማይል (82 ኪ.ሜ ) ያሳጥራል። ለዚህም ይመስላል ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግ ፓናማውያን አሜሪካኖች እንዲሁም ስፔንና ፈረንሳዮች ከብዙ ሙከራ ድካምና ከትልቅ የግንባታ ወጭው በላይ 25,000 አካባቢ ሰራተኛ ዜጎቻቸውን በግንባታው ወቅት በአደጋ እንዲሁም የምድር ወገብ/Tropical area አካባቢ ስለሆነ በወባ ምክንያት መስዋዕትነት ከፍለውበታል። ትልቅና አስቸጋሪ እንዲሁም በምህንድስናው ዘርፍ ከተሰሩ ጀብዶዎች አንዱ ነው። The construction was one of the largest and the most difficult engineering projects ever undertaken, Certainty its one of the bigest engineering FEAT ever done.
ፓናማ ቦይን ከሌላው ቦይ የሚለየውና ድንቅ የሚያስብለው ግን ሁለት የተለየ ከፍታ ያላቸውን የውሃ አካላት ማገናኘቱ እንዲሁም መርከብን የሚያክል ግዙፍ የብረት ደሴት በበር ማሳለፋና በደረጃ ማውጣት ማውረዱ ነው/Gate and lock type canal. መርከብ ግን ምን ያክል ትልቅ ነው? ካላችሁ ደግሞ ...ለአብነትም አሁን ያለሁባት መርከብ መካከለኛ ልንለው እንችላለን/baby cap 260 ሜትር ርዝመት፡ 43 ሜትር ስፋት: 51ሜትር ከፍታ አላት: ከነጭነቷ ደግሞ 142,179.8 ሜትሪክ ቶን ወይም 142 ሚሊዮን ኪሎግራም በላይ ትመዝናለች፡ ውሃ ላይ ምትንሳፈፍበት ደግሞ 11,000 ካሬሜትር አካባቢ/ ከአንድ ሄክታር በላይ ትሸፍናለች።
ለመረዳት ያክል ለምሳሌ አንድ መርከብ ከፓስፊክ ወደ አትላንቲክ ውቅያኖስ ለማቋረጥ መርከቧ 3 ደረጀዎችን በመውጣት 85ጫማ/26ሜትር ከፍ ካለች በኋላ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ሐይቆች(Fresh wster) በማቋረጥ እንደገና 3 ደረጃዎችን በውረድ አትላንቲክ ትገባለች ማለት ነው።
ደረጃውን ለመውጣት መጀመሪያ መርከቧ ከመጀመሪያው በር/ሎክ ትገባለች በሩው ይዘጋል በመሬት ሰበት/gravity ከላይ ከሐይቁ ፈሶ የተዘጋውን በር እስከ ሚቀጥለው ደረጃ የውሃ ልክ ይሞላል የሞለው ውሃም መርከቧን ከሚቀጥለው ደረጃ ልክ ከፍያ ደርጋታል በዚህ ጊዜ የፊተኛው በር ተከፈቶ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ ትገባለች ... ስትወርድ ደግሞ የዚህ ተቃራኒ አሰራር ይሆናል ማለት ነው።
ርዝመቱ (Length) 82 ኪሎ ሜትር/ 51 ማይል
የተገነባው በተለያየ ጊዜ ስፔንና ፈረንሳይ የጀመሩት ቢሆንም አገልግሎት የሚሰጥ ቦይ በአሜሪካኖች ከ1904 --1914 GC ነው። በተጨማሪም ከ2007--2016 GC አቅሙን በእጥፍ ያሳደገ የማስፋትና ተጨማሪ ደረጃዎች ተሰረቶለታል (የማስፋፊያ ፕሮጀክቱ ዕቅድ ሲፀድቅ $5B በፓናማ ሕዝብ ሕዝበ ውሳኔ/Referendum ነበር )
የሚያስተዳድረው Panama Canal Authority
በቀን በአማካይ 40 መርከቦችን ያስተላልፋል
እንደ መርከቦች ርዝመትና ክብደት ይለያያል አንዴ ለማለፍ ትንሹ አማካይ ከ$2,500 - 10,000 ዩስ ዶላር ያስከፍላል
በታሪክ አንዴ ለማለፍ የተከፈለው ትልቁ $375,600 በኖርዌይ ክሩዝላይነር ሲሆን ትንሹ ደግሞ 60ኪግ የሚመዝን አሜሪካዊ አድቬንቸረር በዋና ለማለፍ የከፈለው $0.36 ሳንቲም ነው
እንደ 2021 ሪፖርት በአመት $2.7 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ያስገኛል
ቦዩን በመርከብ ለማቋረጥ 10 ስዓት አካባቢ ይወስዳል
ማለፍ ሚችለው ትልቁ መርከብ ፓናማክስ(Panamax) ይባላል
በአማካይ በአንድ አመት 14,000 መረከቦች ፖናማን በማቋረጥ ከ1,700 የወደብ ከተሞች ተነስተው 160 አገራትን ይደርሱበታል
ሌላው የገረመኝ ፓናማ አካባቢ የፓስፊክ የውሃ ልክ sea level ከ አትላንቲክ በ8 ኢንች(20 ሴንቲ ሜትር) ከፍ ይላል
(The mean sea level at the Pacific side is about 20 cm (8 in) higher than that of the Atlantic side due to differences in ocean conditions like water density and weather.)
የምድራችን ዘጠና ፐርሰንት (90%) የንግድ እቃ በመርከብ ይጓጓዛል ይህ ወሳኝ መተላለፊያም ለዓለም የባህር ትራንስፖርት ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ትርጉም አለው።
ምንጭ: - ጉዞ እና Wikipedia
መርከበኛው
22 - 06 - 2022 @ Panama canal, Ithmus Panama
Viá M/d computer
1.3K views19:05