Get Mystery Box with random crypto!

ምንጊዜም ቢሆን ፩) እግዚአብሔርን መፍራትን እናስቀድማለን። ፪) ፍቅረ ቢጽን እናስከትላለን የሰው | 🇨🇬 ደጉ ሳምራዊ (ኢትዮጵና ቅድስት ቤተክርስቲያን )

ምንጊዜም ቢሆን
፩) እግዚአብሔርን መፍራትን እናስቀድማለን።
፪) ፍቅረ ቢጽን እናስከትላለን
የሰው ልጅ ዋና ጌጦች ፍቅር፣ ትሕትና፣ እውነት ናቸው። ለሰው ልጅ ለተፈጥሮው የሚስማማ ትሕትና ነው። እውነትን መናገር ለእውነት መኖር ለእውነት መሞት ትእዛዛትን መፈጸም ፍቅረ እግዚአብሔር ነው። ሰውን እንደ ራስ መውደድ ደግሞ ፍቅረ ቢጽ ነው። ሰው እግዚአብሔርን ሲወድ እንደ ሕጉ ይሄዳል። ሰው ሰውን ሲወድ ደግሞ ለሌላውም እንደራሱ አድርጎ ያስባል ይጠነቀቃል። ለስነልቡናው ለአካሉ ለጠባዩ ይጠነቀቃል። መጻሕፍት ሰውን እንደ ራስህ ውደድ አክብረው አሉ እንጂ አሽቃብጥለት አምልከው ፍራው አላሉም። ማንኛውም ሰው በፈጣሪ ቸርነት የሚኖር ስለሆነ የሚፈራ አይደለም። የሚያሽቃብጡለትም አይደለም። መፍራትስ መገዛትስ ለፈጣሬ ሰማያት ወምድር ነው።

የፍቅር አምላክ ፍቅሩን ያድለን።
ፎቶ:-@ጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም ቤተክርስቲያን

share and join
@Ethio_Betecrstian