Get Mystery Box with random crypto!

የሰውን ልጅ በተንኮል የሚገድል ሁሉ የተረገመ ነው። ሲገደል አይቶ የማይከላከል፣ የማይናገር ሁሉም | 🇨🇬 ደጉ ሳምራዊ (ኢትዮጵና ቅድስት ቤተክርስቲያን )

የሰውን ልጅ በተንኮል የሚገድል ሁሉ የተረገመ ነው። ሲገደል አይቶ የማይከላከል፣ የማይናገር ሁሉም እንዲሁ የተረገመ ነው።

ኩፋሌ 5፣ 92 "እግዚአብሔር ከአቤል እጅ መሥዋዕትን
ተቀብሎአልና፥ ከቃየን እጅ ግን መሥዋትን
አልተቀበለምና በሦስተኛው ኢዮቤልዩ መጀመሪያ ቃየን አቤልን ገደለወገደለው ስለ ተገደለም በምድረ በዳም እየተካሰሰ ደሙ ከምድር እስክ ሰማይ ጮኸ" እግዚአብሔርም ስለ ገደለው ስለ አቤል ቃየንን ዘለፈው፤ ስለ ወንድሙ ስለ አቤል ደም በምድር ላይ ተቅበዝባዥ አደረገው፥ በምድርም ረገመው። ለዚህ ወንድሙን በተንኰል የሚገድል ሰው የተረገመ እንደ ሆነ በሰማይ ጽላት ተጻፈ። ያዩም ሁሉ ይሁን አሉ። አይቶም ያልተናገረ ሰውእንደ እርሱ የተረገመ ይሁን። ስለዚህም እኛ በሰማይና በምድር፥ በብርሃንና በጨለማ በሁሉም የሚደረገውን ኀጢአት ሁሉ በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት እንናገር ዘንድ መጣን አሉ፤ አዳምና ሚስቱም ስለ አቤል አራት የዘመን ሱባዔ እያለቀሱ ኖሩ።
============================
በሰላም ጊዜ በየአውደ ምህረቱ እየተንገዋለሉና ፈረንጅ በሠራው ድምፅ ማጉያ እያዝገመገሙ ያጠኑትን ጥቅስ የሚያጎርፉ ሰባኪያን ወገኖቻቸው እንደ እንሰሳ በተደራጀና በተቀናጀ ሥርዓት ሲታረዱ አሁንም ዝም ማለት ብቻ ሳይሆን የጭፍጨፋ ተራቸውን የሚጠብቁትን "አጨብጭቡና እልል በሉ፤ ገንዘብ አምጡ" ከማለት አልፈው ራሳችሁን ከመጣባችሁ መዋቅራዊ ጥቃት ጠብቁ ማለት ለምን ተሳናቸው? ይባስ ብለውም ለማረሳሳት ብልጭልጭ ነገርን አብዝተው ማቅረባቸው እና የሕልውናን አጀንዳ እየተቃወሙ በጊዜአዊና ጊዜ በሚሰጥ ጉዳይ ምእመናንን ስለምን ያዘናጋሉ? በወለጋና በመላው ኦሮሚያና ትግራይ ኦርቶዶክሳዊያን ከእምነታቸው እንዲወጡና በጦእነትና በተደራጀ ገዳይ ፍጅት ሲፈጸም እንዴት ከጀንዳ መሆን አልቻለም?

በእግዚአብሔር መለኮታዊ አንደበት "አይቶም ያልተናገረ ሰው እንደ እርሱ (እንደቃየን) የተረገመ ይሁን"።

Fa. Wa

Share and post
@Ethio_Betecrstian