Get Mystery Box with random crypto!

ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲያካሂድ የነበረውን ዓውደ ርዕይ አጠናቀቀ በአዲስ አ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ኮርፖሬሽኑ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሲያካሂድ የነበረውን ዓውደ ርዕይ አጠናቀቀ

በአዲስ አበባ የንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አዘጋጅነት ከየካቲት 16-20/2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው በዚሁ ርዕይ ላይ ኮርፖሬሽኑ ባደረገው ተሣትፎ ከአገር ውስጥ አምራቾች በተወዳዳሪ ዋጋ የሚረከባቸውንና ከውጭ አስገብቶ ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚያቀርባቸውን የተለያዩ የፍጆታ ምርቶች ለዕይታ አቅርቧል፡፡

በተጨማሪም ኮርፖሬሽኑ ባሉት ሰፊ የእህልና ቡና ማደራጃ አውታሮች አዘጋጅቶ ለውጭ ገበያ የሚያቀርባቸው የተለያዩ የቡና ዓይነቶችና የቅባት እህሎች ለተሳታፊ ለሆኑ ግለሰቦችና ተቋማት ዕይታ ቀርበዋል፡፡
በተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ የንግድ መስኮች የሚሠሩ ተቋማት ተሣታፊ በሆኑበት በዚህ ዓውደ ርዕይ ላይ ኮርፖሬሽኑ ምርትና አገልግሎቱን ማስተዋወቅ ከመቻሉ ባሻገር የተለያዩ የፍጆታ ምርቶችን ለተሣታፊው በአነስተኛ ዋጋ አቅርቧል፡፡

የየዘርፉ ባለሙያዎች ርዕዩ ምርትና አገልግሎትን ለማስተዋወቅ በቂ ጊዜና አመቺ ቦታ እንደፈጠረ ገልጸዋል፡፡ የዓውደ ርዕዩ ጎብኚዎች በሰጡት አስተያየት የኮርፖሬሽኑ ምርቶች ዋጋ ገበያ ላይ ካለው ዋጋ አኳያ ቅናሽ ያለው መሆኑን እንደተገነዘቡ በመግለጽ ኮርፖሬሽኑ ይህንኑ አሠራሩን አጠናክሮ እንዲጥል ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡