Get Mystery Box with random crypto!

የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ተግባር አከናወኑ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ተግባር አከናወኑ
የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤትና የእህልና ቡና ንግድ ስራ ዘርፍ ሰራተኞች በዋና መ/ቤት የተተከሉ ችግኞችን የመንከባከብ ስራ ጥር 19/ 2015 ዓ.ም አከናወኑ፡፡
የኮርፖሬት ማህበራዊ ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ወ/ ሮ ትግስት አለማየሁ በ2014 ዓ.ም እንደ ኮርፖሬሽን ከ2ሺ በላይ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው ከዚህ ውስጥ 250 የሚሆኑት በኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት የተተከሉ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ ቅመማ ቅመም፣ አበባ፣ እንዲሁም እንደ ቡናና ሙዝ ያሉ የዛፍ ዝርያዎች ይገኙበታል፡፡
ኃላፊዋ አያይዘውም በዛሬው እለት የተካሄደው መርሃ ግብር የተከልናቸውን ችግኞች በቀጣይነት ለመንከባከብና ሰራተኛው ወደፊትም በባለቤትነት እንዲንከባከቡ ታስቦ የተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አክለውም በቀጣይ በሆለታ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ስራ እንደሚሰራ ገልጸው ዘርፎችም በዚህ መነሻነት በዘርፋቸው የተከሏቸውን ችግኞች እንዲንከባከቡ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡