Get Mystery Box with random crypto!

ወደ ኋላ የዘገዩ የሂሳብ ምዝገባዎችን ማጠናቀቅ፣ የሂሳብ ማጥራት እና የIFRS ትግበራ ማፋጠንን አ | Ethiopian Trading Businesses Corporation (ETBC)

ወደ ኋላ የዘገዩ የሂሳብ ምዝገባዎችን ማጠናቀቅ፣ የሂሳብ ማጥራት እና የIFRS ትግበራ ማፋጠንን አስመልክቶ ማሳሰቢያ ተሰጠ
በኮርፖሬሽኑ የተለያዩ ዳይሬክቶሬቶች (ፋይናንስ፣ ኦዲትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ) ውስጥ የሚገኙ የፋይናንስ ባለሙያዎችን ጨምሮ የአራቱም ዘርፍ ሥራ አስፈጻሚዎች፣ የዘርፉ ሃብት መምሪያ ኃላፊዎችን ያካተተ የጋራ መድረክ ጥር 18/ 2015 ዓ.ም ተካሄደ፡፡ የመድረኩ ዓላማ ኮርፖሬሽኑ ያለውን ሃብት፣ ገንዘብና ንብረት በአግባቡ ለመከታተልና ለመቆጣጠር እንዲሁም የመንግስት የበላይ አካል ኮርፖሬሽኑ ያለበትን ሁኔታ አውቆ ውሳኔ ለመስጠት እንዲችል መሆኑን መድረኩን የመሩት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አቻ ደምሴ ገልጸዋል፡፡
ዋና ስራ አስፈጻሚው ወደ ኋላ የዘገዩ የሂሳብ ምዝገባዎችን ማጠናቀቅ፣ የሂሳብ ማጥራት እና የIFRS ትግበራ ማፋጠንን አስመልክቶ ከሂሳብ ምዝገባ፣ ሂሳብ ማጥራትና IFRS ትግበራ ጋር በተያያዘ ውዝፍ ስራዎች መኖራቸውን በመግለጽ ውዝፍ ስራዎቹን ኮሚትመንት በመጨመር በአጭር ጊዜ ውስጥ ማጠናቀቅ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ አያይዘውም የተሟላ መረጃ በማቅረብና በቁጭት ስሜት ከዚህ በፊት የተሰጡ የኦዲት ኮሜንቶች መስተካከል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ዘርፎች ያጋጠማቸውን ችግርና ከችግሩ እንዴት እንውጣ፣ ማን ምን ይስራ በሚል ሰፊ ውይይት አካሂደዋል፡፡ እያንዳንዱም ዘርፍ የደረሰበትን ለመድረኩ ሪፖርት ያደረገ ሲሆን ውዝፍ ስራውን እጅግ በፈጠነ ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እንዲቻል ታክስ ፎርስ እና ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል፡፡