Get Mystery Box with random crypto!

የኔ_አላህ የኔ አላህ ይቅር ባይ ነው ይቅር ማለትንም ይወዳል የሰው ልጅ ሊጎዳን እንደማይችል | ᎷUᏚᎯᏰ™ Islamic Page

የኔ_አላህ

የኔ አላህ ይቅር ባይ ነው ይቅር ማለትንም ይወዳል የሰው ልጅ ሊጎዳን እንደማይችል ውስጡ ሲያውቅ ይቅር ሊለን ይችላል፤ የኔ አላህ ግን ቻይ ሆኖ፤ የፈለገውን ነገር ማድረግ እየቻለ ነው ይቅር የሚለን፤ መቅጣት እየቻለ የሚያልፈን ነው።
አል-አፉው ከባድ ሚዛን ያለው ስም ነው። በእርግጥ የአላህ ስሞች ሁሉ ውብ ናቸው ለእኔ ግን አል-አፉው ትልቅ ስፍራ አለው አስቡት! አል-አፉው እኮ ማለት ይቅር ባይ ማለት ብቻ አይደለም! ሀጢያቱ መጀመሪያውኑ እንዳልተፈፀመ አድርጎ ይቅር ማለት ቢሆን እንጂ ሀጢያቱን ከመማሩ ማጥፋቱ ከማጥፋቱም እንደፈፀምነው እራሱ እንዳናውቀው ማስረሳቱ ከዛም አልፎ ስራችንን መውደዱና መቀበሉ ከውዴታው በኃላ ሳንጠይቀው የሚያስደስተንን የሆነ ሀላል ስጦታ መስጠቱን በውስጡ ስለያዘ ይህንን ስም በጣም እንድወደው አድርጎኛል! ግን እኛኮ ያልነው ይቅር በለን ብቻ ነበር አይደል?አላህዬ ግን ጥበቡ ሰፊ ነዋ፤ ባህሪያቶቹ ከአዕምሮ በላይ ናቸው።

የኔ አላህ ከሰራኸው ወንጀል በላይ ወደሱ መዋደቅህን ይወደዋል፤ በውብ ስሞቹ እየጠራህ ምህረቱን እንድትለምነው ይፈልጋል፤ በአል-አፉው ስም ከልብህ ስትለምነው አላህ ከተቀበለው ወንጀልህን ያስረሳሃል፤ ከመጥፎ ስራ መዝገብ ላይም ያጠፋታል፤ ይጠርጋታል የውመል ቂያማ ስትመጣ እንዲህ ሰራህ ብሎ አያስታውስህም፤ አይጠይቅህምም! ያ አላህ!

ግን ይሄ ሁሉ ለምን አያስብልም? ጌታዬ ስለሚወድህ ባንተ መወደድም ስለሚፈልግ ነው ለሱ በምድር ላይ ትልቁ ፍጥረት ነህና ሊያዝንልህ ይፈልጋል፤ ወንጀልህን ጠርጎልህ ጀነቱ እንድትገባ ይጓጓል!

ይህ ነው እንግዲህ የኛ አላህ! በስሙ ለመኖር ዝግጁ?
وَيَعْفُ عَن كَثِيرٍ
ከብዙም ይቅርታ ያደርጋል፡፡

ኢላሂ! አንተ ይቅር ባይ ነህ ይቅር ማለትንም ትወዳለህና ይቅር በለን!

@Islamic_direction