Get Mystery Box with random crypto!

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል በጉባኤው ላይ ለመሳተፍም የህብረቱ አባል | Adey Drama - አደይ ድራማ

35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጀመራል

በጉባኤው ላይ ለመሳተፍም የህብረቱ አባል ሀገራት መሪዎች ዛሬ ማለዳውን ጨምሮ ሰሞኑን አዲስ አበባ እየገቡም ቆይተዋል።

ጉባኤው “የአፍሪካ አኅጉርን የሥርዓተ ምግብ አቅም በመገንባት፤ የሰው ሃብት ልማት፣ የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ልማትን ያፋጥናል” በሚል መሪ ሃሳብ ዛሬ እና ነገ የሚካሄድ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በሊቀመንበርነት የምትመራው የሁሉን አቀፍ የአፍሪካ የግብርና ዕድገት ፕሮግራም አፈጻጸምም ይቀርባል።

ሪፖርቱንም የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያቀርቡታል ተብሎ ይጠበቃል። ይህም ሪፖርት የግብርና መስክ ዕቅዶች አፈጻጸም የሚገኝበትን ደረጃ እና የተገኙ ውጤቶችን ያካትታል ነው የተባለው።

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት መሪዎች ለሁለት ዓመት በአካል በመገኘት የሚያካሂዱትን ጉባኤ ሳያደርጉ ቆይተዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያትም አንዳንድ ወገኖች የህብረቱ ጉባኤ በአዲስ አበባ እንዳይካሄድ ብርቱ ጥረት ቢያደርጉም፥ በተሰሩ የዲፕሎማሲ ስራዎች እና በአባል ሀገራቱ ውሳኔ ጉባኤው በህብረቱ ህገደንብ መሰረት በመዲናችን አዲስ አበባ እንዲካሄድ ተደርጓል።

@Esatethiopiantv
@Esatethiopiantv