Get Mystery Box with random crypto!

​​​​​​​​​​​​​​​ ➛ አንቺ ስትናፍቂኝ መውደድና ፍቅርሽ ደርሶ ትዝ ሲለ | አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን

​​​​​​​​​​​​​​​
➛ አንቺ ስትናፍቂኝ

መውደድና ፍቅርሽ ደርሶ ትዝ ሲለኝ
ካለሁበት ሁኜ አንቺ ስትናፍቂኝ
ከቶም አይጋርደኝ ጋራ ሸንተረሩ ፣
ችሎም አያደክመኝ በርሀ ሀሩሩ፣
አባጣ ጎርባጣው የመንገዱ እንቅፋት፣
ላፍታም ትዝ አይለኝ ትንሽንኳ ቅንጣት፣
የፅልመት መደቅደቅ የአውሬው ዋካታ፣
ፍፁም አያሰፈራኝ የናፈቅሽኝ ለታ ፣
ቀን ይሁን ሌት ይሁን ክረምት ወይም በጋ፣
ጊዜም ቦታም አልመርጥ ለምንም አልሰጋ፣
ብርዱና ወጨፉም ካፊያውና ዶፉ ፣
መችስ ያቆሙኛል ፊቴ ቢሰለፉ፣
መውድድና ፍቅርሽ ደርሶ ትዝ ሲለኝ
ካለሁበት ሁኜ አንቺ ስትናፍቂኝ
ስከንፍ እመጣለሁ ሳልነግርሽ በርሬ፣
ትዝታ እየጋለብኩ ያሳብ ጓዝ ቋጥሬ፣
ወዲያው እደርሳለሁ ካለሽበት ግድም፣
ካዛ ፊትሽ ቁሜ ሳልተነፍስ ቃልም፣
እንዲሁ በስስት እያዩሽ አይኖቼ ፣
እምባ ይረጥባሉ እነዛ ጉንጮቼ ፣
ደግሞ ቆየት ብዬ ላወራሽ ያምረኛል፣
የምሰሚኝ ያህል ያስለፈልፈኛል ፣

በቃ ስትናፍቂኝ••••

ላንቺ ባልታይም ፊትሽ ተገትሬ፣
ጆሮሽ ባይሰማውም የውስጦቼን ወሬ፣
ገላሽ ባይነካኛም ከጎንሽ አድሬ፣
መውደድና ፍቅርሽ ደርሶ ትዝ ሲለኝ
ካለሁበት ሁኜ አንቺ ስትናፍቂኝ
ዘበት እኔ አላቅም ሳልመጣ ቀርቼ
በትዝታ ግልቢያ ባሳብ ፈረስ ቼቼ

#ሼን
ሼር SHARE
  


@Eraza_fil
@Eraza_fil