Get Mystery Box with random crypto!

ናፍቆት ናፍቀሽኛል ብዬ ቃላት እያወጣሁ ናፍቆቴን ለመግለፅ ለናፍቆት | አንዳችን ለአንዳችን እናስፈልጋለን


ናፍቆት

ናፍቀሽኛል ብዬ ቃላት እያወጣሁ
ናፍቆቴን ለመግለፅ ለናፍቆት ቃል አጣሁ
ገና ናፍቀሺኛል ብዬ ሳልጀምረው
ተሰማኝ ናፍቆትሽ ውስጤን ሲያሸብረው
እኔ የፍሬ ናፍቆት ፣ አንቺ የጥበብ ሸማ
ሲመታ አዳምጪው ያን የልቤ ዜማ
በናፍቆት አለንጋ
ደምቶ የማይረጋ
ብዙ ቅኔ ያለው ናፍቆት ሞልቶት ልቤን
ናፈቅሺኝ እላለው ላይገልፀው የውስጤን
የመናፈቄን ጥግ የጉጉቴን መጠን
የመውደዴን አቅም የማፍቀሬን ወሰን
ድንበሩን ለማየት መግለጥ ያሻው ዶሴ
ይለካ እስትንፋሴ ።


ሼር SHARE
  


@Eraza_fil
@Eraza_fil