Get Mystery Box with random crypto!

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕገ ወጡን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማትቀበልና ቤተክርስቲያንን የ | ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሕገ ወጡን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት እንደማትቀበልና ቤተክርስቲያንን የመክፈል ሙከራን እንደምታወግዝ አስታወቀች፡፡

ከስድስቱ ኦሬንታል እህት አብያተክርስቲያናት አንዷ የሆነችው የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በፓትርያርኳ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ አግናጢዎስ ኤፍሬም ፪ኛ በኩል ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በጻፈችው ይፋዊ ደብዳቤ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ በለየው ሕገ ወጥ ቡድን የተፈጸመውን ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት የጨረቃ ሹመት በማውገዝ ከቅድስት ሐዋርያዊት ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያ ጎን መቆሟን ገልጻለች፡፡
የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትን ሕጋዊ እና ሐዋርያዊ ቅዱስ መሪነት ብቻ የምትቀበል መሆኑን በመግለጽ ቤተክርስቲያኗ ላይ ተከሰተው ፈተና እንዲያፍ በጸሎት እንደምትለምን ገልጻለች፡፡
EOTC TV