Get Mystery Box with random crypto!

አቤሴሎም አባቱን ለመግደል እና በአባቱ አስከሬን ላይ ለመፎከር እያዋጋ በጫካ ሲያልፍ የሚመካበትን | ፍኖተ-ወራዙት ዘኦርቶዶክስ ⛪

አቤሴሎም አባቱን ለመግደል እና በአባቱ አስከሬን ላይ ለመፎከር እያዋጋ በጫካ ሲያልፍ የሚመካበትን የውበቱ መገለጫ የሆነውን ጸጉሩ እሾህ ያዘውና በቅሎው ሲሔድ እርሱ በዛፉ ላይ ተንጠልጥሎ ቀረ። “አቤሴሎምም በበቅሎ ተቀምጦ ነበር፥ በቅሎውም ብዙ ቅርንጫፍ ባለው በታላቅ ዛፍ በታች ገባ፥ ራሱም በዛፉ ተያዘ፤ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ፥ ተቀምጦበትም የነበረ በቅሎ አለፈ” /2ኛ ሳሙ 18 ፤ 9/ ተብሎ እንደተጻፈ ምሳሌያዊ በሆነ መንገድ በሰማይና በምድር መካከል ተንጠለጠለ። አስተውሉ ክርስቲያኖች ሁላችንም ቢሆን እንዲሁ በመካከል ሆነን ወይ ከምድር ወይ ከሰማይ ሳንሆን እንዳንቀር መጠንቀቅ አለብን።
እግዚአብሔር የቲፎዞ፣ የብሽሽቅ፣ የሽንገላ፣ የማስመሰል እና በአጠቃላይ ምድራዊ በሆኑ ነገሮች የታጀበን ሁሉንም ነገር አይቀበልም። እነዚህ እንዲያውም የነፍስ ቫይረሶች እና መንፈሳዊነትን የሚያበላሹ የሰይጣን ባክቴሪያዎች ናቸውና እነዚህን በመሰሉት ተለከፈን ጾም ጸሎታችንን እንዳናበላሸው እንጠንቀቅ። ከለፍላፊነት እና ከተሳዳቢነት በሽታም እንፈወስ። ይልቁንም ጦርነታችን የአቤሴሎም ጦርነት መሆኑን አወቀን የዳዊትን ልቡና ገንዘብ በማድረግ በመንፈሳዊነት እንዋጋ። ያን ጊዜ ጉልበተኛውን፣ ሸንጋዩን እና እንደ አቤሴሎም የሰውን ልብ ለጊዜው በማስመሰል የሰረቁትን ሁሉ ራሱ ፈጣሪያችን እንደ አቤሴሎም ያንጠለጥላቸዋል። አምላካችን የዳዊትን የንስሐ እና የማስተዋል ልቡና ለሁላችን አድሎን ከአምላካችን ጋር ታርቀን ጠላታችን ዲያብሎስን ድል የምንነሣበት ሱባኤ ያድርግልን፣ አሜን።