Get Mystery Box with random crypto!

እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል! ሰው በሁኔታዎች ሲለካ አምላክ ግን ከሁኔታዎች በላይ ነው ፤ ሰው | ቁምነገር

እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል!

ሰው በሁኔታዎች ሲለካ አምላክ ግን ከሁኔታዎች በላይ ነው ፤ ሰው ደስታን ሲመኝ ደስታ በእራሱ ፈጣሪ ነው ፤ ሰው አምላኩን ፍለጋ ሲደክም እርሱ ግን በውስጡ አለ ። የነገሮች መደራረብ ፣ የሃዘን ብዛት ፣ የጭንቀቱ ማየለ የአንድ ሰሞን ሁኔታ ነው ። የችግሮች ክብደት ጊዜያዊ ሁኔታ ነው ። ከነዚህ በላይ የሆነ አምላክ ግን ምንጊዜም አብሮን አለ ፤ ውስጣችን ይገኛል ። "አምላክ የት ይገኛል ቢባል ሁሉም ቦታ ይገኛል ?" በተለይ የእጅ ስራው በሆነውና አምሳሉ በሆነው የሰው ልጅ ውስጥ በሙላት ይገኛል ፤ ዘወትር ይመላለሳል ። ስራውን ለመስራት፣ ተአምራትን ለማድረግ ግን የእኛን ፍቃድ ይፈልጋል ።

አዎ! ጀግናዬ..! ጫጫታ ውስጥ ሆነህ የአምላክህን ድምፅ አትሰማም ፤ ውስጥህን አታዳምጥም ፤ ከመንፈስህ ጋር አትገኛኝም ፤ ተዓምራዊውን አንተ አታገኘውም ። የእራስህ ጊዜ ያስፈልግሃል ፤ አምላክህን በግልፅ የምታወራበት ፣ መንፈስህን የምታናግርበት ፣ ውስጥህን የምትቃኝበት ፣ ሰላምን የምትሰብክበት የተነጠለ ፣ ከምንም ያልተገናኘ ያንተና የፈጣሪህ ብቻ የሆነ ጥርት ያለ ጊዜ ያስፈልግሃል ። ብቸኝነት አያስፈራም ፤ ከእራስህ ጋር ስታወራ ከአምላክ ጋር እንደምትወያይ አስብ ፤ ቀጣይ እርምጃዎችህን ሲመራህ ትመለከታለህ ፤ ልዩነትህን ያሳይሃል ፤ የሁኔታዎችን አላፊት ያንተን ጥንካሬ ያስገነዝብሃል ።

አዎ! እርሱ ከሁኔታዎች ይበልጣል ፤ የተሰጠህ አቅም በትናንሽ ክስተቶች የሚደክም አይደለም ፤ ሰውነትህ በጊዜያዊ ክስተቶች የሚከስም አይደለም ። ስራውን የሚሰራው ፣ ያልቻልከውን የሚያስችልህ ፣ የከበደህን የሚያቀልልህ ፣ ዛሬህንም ሆነ ትናንትህን ወደ ታሪክ የሚቀይር ፣ የሰጠህን የሚያስችልህ ፣ የመጣብህን የሚያሳልፍህ የዘወትር ጠባቂህ ፈጣሪህ ነው ። በእርግጥ ከገንዘብህ ፣ ከንብረትህ ፣ ከዝናህ ፣ ከወዳጅህ በላይ በአምላክህ ሃይል የተማመንክበት ጊዜ ካለ አስታውስ ። በቸገረህ ሰዓት መጠለያህ ማነው ? በፈተና ወቅት መደበቂያህ የት ነው ? በጨለብህ ጊዜ ብረሃንህን የት ትፈልጋለህ ? ሁሉን አንድ ላይ የያዘ ፣ የጥያቄዎችህን ምላሽ ከምታገኝበት ከአባትህ እቅፎፍ አትራቅ ፤ በቻልከው ልክ ተጠጋው ፤ ከሁሉም በፊት እርሱን አስቀድም ።


@enkopawiyan
@enkopawiyan
@enkopawiyan

         @betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ