Get Mystery Box with random crypto!

#የ 'Mermaid' እንቆቅልሽ #ከፊል_ሰው_ከፊል_ዓሣ_የባሕር_ፍጡራን ---------------- | ድብቅ ዕይታ

#የ "Mermaid" እንቆቅልሽ
#ከፊል_ሰው_ከፊል_ዓሣ_የባሕር_ፍጡራን
------------------------------------------------------
እነዚህ ፍጡራን ዝም ብሎ አቧራ ለማስነሳት
አሉ የሉም የሚባሉ ወይም ጊዜያዊ ንግርቶች አይደሉም።
ከሠው ልጅ የጥንት አኗኗር ጋር የተቆራኙ በጥንታዊ ስልጣኔዎች
(Mesopotamia, Bablylonia, Sumeria, Greece, Egypt, Native American Tribes)
# ሰውን_መሰል_የባሕር_ፍጡራን እየተባሉ
በባህሎች፣ ቅርፃቅርፆች፣ ሥዕሎች፣ በጥንታዊ መጽሐፍት የተጠቀሱ፣ ተረትና ታሪኮች በብዛት ያሏቸው እንጂ።

#ከተማቸው_Atlantis
የኔፕቱን ከተማ "የጠፋችው/የሰጠመችው ከተማ"
#The_lost_City_Of_Atlantis በመባል የምትታወቅ።
በአንድ ወቅት ኃያል፣ ግዙፍ፣ በስልጣኔ የረቀቀችና ጫፍ የደረሰች ከተማ
ለMermen (ወንዱ)
Mermaid (ሴቷ) መኖሪያቸው ነበረች ይባላል።
ፈላስፋው ፕሉቶ በወቅቱ ስለዚህች ከተማ (Timaeus & Critias) በተባሉ ፪ ሥራዎቹ ገልጿል።

እስካሁንም በተደረጉ ጥናቶችና አሰሳዎች አንዳንድ ግኝቶች እየተገኙ ስለሆነ።
ከተማዋ ወደ ጥልቁ ባሕር ከነግሳንግሷ ብትሰጥምም በውስጧ ይኖሩባት
የነበሩት እንደ ዓሣ በባሕር የሚዋኙ፣ በየብስም እንደ ባሕር አንበሳ የሚቆዮት Mermaid ግን አልጠፉም ተብሎ ይታመናል።

#እውነት_አሉ?
የነዚህ ፍጡራን ህልውና እስካሁን እንቆቅልሽ ሆነው ከሚገኙ ምስጢራት አንዱ ነዉ።
Mermaid ታዩ የተባለው በ 1814 እ.ኤ.አ (West coast of Scotland) ባሕር ላይ ነው ይህም ለምርምር ፈር ቀዳጅ ሆኗል።

የትንሿ mermaid ታሪክ በአሴርያን (1000 BC) አፈ ታሪክ ያለ እንዲህ ይላል።
goddess Atargatis (mother of Assyrian) ንግስት Semiramis አንድ
እረኛ ትወዳለች ሳታስበውም ትገድለዋለች በድርጊቷ ስላፈረችም ወደ ባሕር
ዓሣ ሆና ትገባለች። ባሕሩ ግን ውበቷን አልወደደላትም ስለዚህም የ mermaid
(ከላይ ሰው ከወገብ በታች ዓሣ) ቅርፅ በመያዝ ባሕር ውስጥ መኖር ጀመረች ይላል።

#ሳይንሱ_ምን_ይላል ?
በጠቅላላው ባይሎጂካል ቅርፃቻውን ሊሆን ይችላል በሚል ይስማማል።

# እውነታው
የሰው ልጅ ወደ 90% የባሕር ፍጡሮችን አያውቃቸውም ወይም ገና መርምሮ አልደረሰባቸውም።
ከበላዩ ያለውን ሕዋ (space)'ን እንደመመርመሩ ከስሩ
ያለውን ጥልቅ ባሕር አላሰሰም።
ልክ Alien, UFO, Extraterrestrials የሌሎች ዓለማት ፍጡራን አሉ/የሉም የሚለው አወዛጋቢ እንደሆነው ሁሉ
Mermaids #ይኑሩ_አይኑሩ_በተቀረውና
"ተጠንቷል" በተባለው 10% ብቻ አፍን ሞልቶ ለመናገር አያስደፍርም።

አንዳንድ ባሕረኞችና መርከበኞች እነዚህን ፍጡራን እንዳዩ ገልፀዋል።
በአርኪዎሎጂ ቁፋሮዎችም የነሱን የመሰለ ከወገብ በታች ያለ የአካል ክፍል ተገኝቷል ይባላል።

የእስራኤል ከተማ Kiryat Yam ማንኛውም ስለ mermaid መኖር ተጨባጭ
ማረጋገጫ መስጠት የሚችልን ሰው 1 million $ እስጣለሁም ብላለች።
በርካታ ምርምሮች፣ ጥናቶች፣ ፊልሞችና ዶክመንተሪዎች በነዚህ ፍጡራን ዙርያ ተሰርተዋል።

ምስጢራቸውን ግን ባሕሩም ዝም እነሱም ሊገናኙን ፍቃደኞች አይደሉም መሰል
እንቆቅልሽ ሆነው እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ አሉ።