Get Mystery Box with random crypto!

#ጸጸትና_ምሬት #ምስጋና_ተስፋና_አዲስ_ጅማሬ በሚሉ ሃሳቦች ላይ የመጀመሪያውን ስልጠና በመስ | Empowering Next Generation - ENG

#ጸጸትና_ምሬት
#ምስጋና_ተስፋና_አዲስ_ጅማሬ

በሚሉ ሃሳቦች ላይ የመጀመሪያውን ስልጠና በመስጠት የ #Women_Empowerment_Project ትግበራችን አካል የሆነውን #የDay1_Capacity_Building ስልጠናችንን ጀምረናል፡፡ በጣም ደስ የሚልና #ኳሊቲ_ታይም ነበር ያሳለፍነው በውይይታችን እና ስልጠናችን፡፡

ሰዎች በህይወት ጎዳና በሚያጋጥሟቸው አሰልቺ የመከራ ድግግሞሽ ሳቢያ ምናልባት በህይወት እያሉ ታሪካቸውን ግን እንደ ሞተ ሰው ታሪክ እያሰቡ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ከንግዲ የማይለወጥ፣ተስፋ የሌለው፣ያበቃለት፣እንዲያ እንዲሆን ብቻ ተፈርዶ መዝገቡ የተመለሰና ከንግዲ ስለ መኖር አለመኖር እንጂ ስለ ለውጥ እንዳያስቡ ነገር ሁሉ ያከተመ፡፡

በለውጥ ውስጥ ካሉ ጥሩ ነገሮች አንዱና እጅግ አስደናቂው እውነት #ለውጥ_ከአስተሳሰብና_አተያይ ብቻ የሚጀምር መሆኑ ነው፡፡ ሰዎች ነገርን ካላዩበት አቅጣጫ አንድ ግዜ ዘወር ብለው ማየት ቢችሉ ብዙ ተስፋ፣እድል፣ምስጋና እና አዲስ ጅማሬ ሁሌም አለ፡፡

ብዙ የመከራን ዑደት፣ቀዝቃዛን ክረምት አሳልፎ ደግሞ እንደገና ካጎነበሱበት ቀና የማለት ህግ #Resilience ይባላል፡፡ ይህ በሁላችንም ውስጥ ያለ ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው፡፡ በተደጋጋሚ ከባድ በሆነ ፈተና ውስጥ ሰው ሲያልፍ፣የፈተናው ቁመንትና ክብደት ደንደን/ረዘም ሲል #አቀርቅሮ_በመቆየት_ብዛት የጠፋ ሊመስል ይችላል እንጂ እንደምታውቁት #ህግ_አይጠፋም፡፡ ትንሽ ደግሞ ጸሃይ ብቅ ሲል ከንደገና መዘረጋጋት፣ማበብ፣ወደ ድሮው መልክ መመለስ ፍጥረት ውስጥ አለ #ይፈተናል_እንጂ በልዩ ልዩ ሁኔታዎች፡፡