Get Mystery Box with random crypto!

ትላንትና #ሰላም_በሚል_ርዕስ ላይ አንድ በአብዛኛው ወጣቶች በሚሳተፉበት የስልጠና መርሃግብር ላይ | Empowering Next Generation - ENG

ትላንትና #ሰላም_በሚል_ርዕስ ላይ አንድ በአብዛኛው ወጣቶች በሚሳተፉበት የስልጠና መርሃግብር ላይ ተጋብዤ ስልጠና እየሰጠሁ ነበር፡፡ ታዲያ እያንዳንዱ ተሳታፊ የነበረው ንቃትና ተነሳሽነት እጅግ ደስ የሚል እና ተስፋን የሰጠኝም ነበር፡፡ ታዲያ #ሲምፕል በሆኑ መሰረታዊ ሃሳቦች ላይ የሚያጠነጥን #ትሬኒንግ ልሰጥ በተገኘሁበት #ፕሮፌሰር_ዲባባ የተሰኙ በሰላም ዙሪያ ብዙ ርቀት ሄደው ያጠኑ ድንቅ ሰው ጋር ተገናኘሁና፤ ከነጭራሹ “በቀጣይ ሃሳቦቹን በጥልቀት የምታስደግፍበት” ይሁንህ ሲሉ እጅግ ብዙ ዋጋ የሚያወጡና ተደክሞባቸው የተገኙ #ማቴሪያሎችን ለኔና ለድርጅቴ አበረከቱልን፡፡

መቼም ሰዎች ወደድንም ጠላንም በህይወት ስንኖር በአንድ ሲስተም ውስጥ ወይ #የመፍሄው_አካል ወይ #የችግሩ_አካል ካልሆነም #የችግሩ_ሰለባ ሆነን ልንኖር የግድ ነው፡፡ አንዳንዴ ደግሞ የማይጋጩ ሁለት ቤቶች ውስጥ እንደሁኔታው ልንኖር እንችላለን፡፡ በዚህ አጋጣሚ እንደ ግለሰብ ከየትኛው ወገን ነኝ ብለው ያስባሉ? ከሆነስ ለምን?

ከሚያመጣው ተቀራራቢ ወጤት አንጻር ሰዎች #በአመጽና_ትውድን_ሰላም_በመንሳት አካሄድ ውስጥ በዋናነው በሁለት መንገድ ይሳተፋሉ፡፡ #1ኛው በቀጥታ እጃቸውን ሰንዝረው በአመጽ ውስጥ በማስገባት፡፡ 2ኛው #በተለያየ_መልክ_ራሱን_በሚገልጥ_ኢግኖራንስ፡፡ በጉዳዩ ላይ #እንደማያገባው_ሰው_አክት ለማድረግ በመሞከር፡፡ አብዛኛው የኔ ቢጤ ሰው #በ2ኛው መንገድ ነው የሚሳተፈው ብዬ አስባለሁ፡፡

ታዲያ ግን ከሰላም ጋር በተያያዘም ብቻ ሳይሆን በብዙ #አስፔክት_ኦፍ_ላይፍ #ኢግኖራንስ በጣም አደገኛ ነው፡፡ #ሰዎች_ለማወቅና_ጥቂት_አክት_ለማድረግ ከሚከፍሉት ዋጋ አንጻር #ባለማወቅና_ጥቂት_አክት_ባለማድረግ የሚከፍሉት ዋጋ ብዙና አሳዛኝ ነው፡፡ምናልባት ግን እርሶስ በየትኛው መንገድ ተሳታፊ ኖት? ከሆነስ ለምን?