2021-11-17 19:19:40
·
(የሚያለቅሱበት ቂሷ)
የሰኢድ ኢብን ጁበይርን አሟሟት አስገራሚ ታሪክ ያንብቡት፡፡
``````
ሐጃጅ ሰኢድን “ ሸቂዩ ኢብኑ ከሲር ነህ አይደል ?” አለው፡፡(በአረብኛ ሸቅይ የሰኢድ ተቃራኒ ነው)
ሰኢድ፡- ስሜን ያወጣችልኝ እናቴ ጠንቅቃ ታውቀዋለች፡፡
ሐጃጀ፡-(በቁጣ) አንተም እናትህም ፉግር እድለ ቢሶች(ሸቅይ) ናችሁ፡፡
ሰኢድ፡- ሸቅይማ የጀሀነም የሆነ ሰው ነው፡፡ የሩቅ ታውቃለህ እንዴ?
ሐጃጅ፡- ዱንያህን በአንገብጋቢ ጀሀነም ነው የምቀይርልህ፡፡
ሰኢድ፡- ወላሂ ይህን ማድረግ መቻልህን ባውቅ ከአሏህ ውጭ አምላክ አድርጌ እይዝህ ነበር፡፡
ሐጃጅ፡- ለኔ ያለህ አመለካከት ምንድን ነው?
ሰኢድ፡- በሙስሊሞች ደም ተጨማልቆ አሏህን የሚገናኝ በደለኛ ነህ፡፡
ሐጃጅ፡- ይልቅ ምን አይነት አገዳደል ልግደልህ? እራስህ ምረጥ፡፡
ሰኢድ፡- አንተ ራስህ መሞቻህን መንገድ ምረጥ፡ አሏህ አኔን በገደልከኘኝ መንገድ አንተንም ይገድልሃል፡፡
ሐጃጅ፡- ካንተ በፊትም ሆነ በኋላ! የማልገድልበትን አሰቃቂ ግድያ ነው የምገድልህ፡፡
ሰኢድ፡- ስለዚህ አንተ ዱንያየን ስታበላሽብኝ በኔ ምክንያት አኺራህ ይበላሻል፡፡
ሐጃጅ የሰኢድን ብርታት ባለመቋቋሙ ወታደሮችን ጠርቶ እየጎተቱ ወስደው እንዲገድሉት አዘዘ፡፡
ሰኢድም በሐጃጅ እየሳቀበት ከገዳዮቹ ጋር ሄደ፡፡ በዚህ ጊዜ ሐጃጅ በቁጣ ሰኢድን ተጣርቶ ምንድን ነው የሚያስቅህ? አለው፡፡
ሰኢድም : እኔማ የሚያስቀኝ አንተ በአሏህ ላይ ያለህ ድፍረት እና አሏህ ባንተ ስራ ያለው ትዕግስት ነው አለው፡፡
ሐጃጅ ፦ ይህንን ሲሰማ በቁጣ ገንፍሎ ወታደሮቹን እረዱት ሲል አንቧረቀባቸው፡፡
ሰኢድም፦ ወደ ቂብላ አዙራችሁ እረዱኝ አለ፡፡ አንገቱ ላይ ሰይፍ እንዳስቀመጡበትም
“ ወጅጀህቱ ወጅሂየ ሊልለዚ ፈጦረስሰማዋቲ ወል አርዶ ሀኒፈን ሙስሊመን ወማ አነ ሚነል ሙሽሪኪን ” አለ፡፡
ይህንን የሚከታተለው ሐጃጅ ፊቱን ከቂብላ ወደ ሌላ አቅጣጫ አዙሩት አላቸው፡፡
ሰኢድም ፦ “ወሊላሂል መሽሪቁ ወል መግሪቡ ፈአይነማ ቱወልሉ ፈሰምመ ወጅሁሏህ ” የሚለውን አያህ ቀራ፡
ሐጃጅም በፊቱ ድፉት አለ፡፡
ሰኢድም “ ሚንሃ ኸለቅናኩም ወፊሃ ኑዒዱክም ወሚንሃ ኑኽሪጁኩም ታረተን ኡኽራ ” የሚለውን አያህ አነበበለት፡፡
ሐጃጅ፡- አንተ ሰኢድ ምላስህ እንዴት ለቁርአን ፈጣን ነው!!! እረዱት አለ፡፡
በዚህ ጊዜ ሰኢድ “ አሽሀዲ አንላኢላሃ ኢልለሏህ ወአንነ ሙሀመደን ረሱሉሏህ ”
ሐጃጅ ሆይ የውመል ቂያማ እስከምንገናኝ ድረስ ይህችን ንግግሬን ያዛት አለና “ አሏህ ሆይ ከኔ በኋላ ማንንም እንዳይገድል አድርገው ” ብሎ አሏህን ተማጽኖ ተገደለ፡፡
የሚገርመው ነገር ግን ከሰኢድ ሞት በኋላ ሐጃጅ በየሌሊቱ “ ምነው ይህ ሰኢድ ልተኛ ስል እግሬን እየያዘ እረፍት ነሳኝ ” እያለ እየባነነ ይጮህ ነበር፡፡
ከሰኢድ ሞት 15 ቀናት በኋላ ሐጃጅ ማንንም ሰው ሳይገድል ሞተ፡፡ አንተ የጁበይር ልጅ ሆይ አሏህ ይዘንልህ፡፡ ካንተ ፅናት፣ አሳማኝ መረጃ እና የኢማንህ ንፅህና አንፃር እኛስ የት ነን?
@elunacalligraphy
148 views16:19