Get Mystery Box with random crypto!

ለዚህ ነበር? . (#ፈይሠል_አሚን) . የዘላለም ያህል ረዝሞ. . . ዘጠኝ ወር አግቶኝ፤ ዘንቶ ለ | Eluna Calligraphy and Islamic posts

ለዚህ ነበር?
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
የዘላለም ያህል ረዝሞ. . .
ዘጠኝ ወር አግቶኝ፤
ዘንቶ ለመቀመጥ፣
መወለድ አጓጉቶኝ፤
ሆዷን እረግጣለሁ፣
እጋላበጣለሁ. . .
"ውለጂኝ!" እላለሁ።
.
ማሕፀን ውስጥ አልቀረሁ፣
ተወለድኩ. . .
ተሰወርኩ!
.
ደርሶ ተከፈተ፣የመዓሲያው በር፣
"ኑሮ" በሚሉት የብላሽ አጎበር፣
በከረፋው ቀንበር፣
ታስሬ ልሰበር፣
ሆዷን የረገጥኩት፣ለዚህች ሕይወት ነበር?
.
@elunacalligraphy