Get Mystery Box with random crypto!

ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC)

የቴሌግራም ቻናል አርማ elohimlifechannel — ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC) E
የቴሌግራም ቻናል አርማ elohimlifechannel — ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC)
የሰርጥ አድራሻ: @elohimlifechannel
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 396
የሰርጥ መግለጫ

ይሄ የክርስቲያን ቻናል የተከፈተበት አላማ ክርስቲያኖችን ላቅ ወዳለና ተጽዕኖ ወደሚፈጥር ሕይወት ለማምጣት ነው።በዚህ ቻናል ውስጥ የተለያዩ ዘርፈ ብዙ ፕሮግራሞች ይቀርባሉ።
ከእነዚህም ውስጥ
፦የአዕማድ ሰዎች ንግግሮች
፦ከታማኝ ምንጭ የተገኙ ዜናዎች
፦የድሮም የአሁንም አዳዲስ ዝማሬዎች
፦ህይወት ለዋጭ፣የሚያንጽ ስብከቶችና ትምህርቶች ስነጽሁፎች፣ታሪክና ምሳሌዎች።
https://youtu.be/-bmaoih

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-03 10:36:42 ራሳችንን በምንድነው የምንለካው?
---------//-------------
"ደመወዜ ትንሽ ቢሆንም እኔ ግን ትንሽ አይደለሁም"

ዛሬ በስራ ምክንያት ወደ አንድ ቢሮ ስሄድ አንድ እስላም የሆኑ ሰው ይሄንን ንግግር ተናገሩ።እንደዚህ አይነት ንግግር በክርስቲያን መካከል እንኳ አልሰማሁምና ገረመኝ።ወገኖቼ አውነት ነው የእኛ ዋጋ ባለን ነገር አይለካም።የእኛ ዋጋ ያለው እግዚአብሔር ጋር ነው።ያለን ነገር እኛን አይለካም እኛ ውድ ዋጋ ያለው ሰው ነን እግዚአብሔር ያከበረን።የእንስሳት ደም መፍሰሱ ከእኛ ዋጋ ጋር ስለማይወዳቸር እግዚአብሔር የውድ ልጁን ደም አፈሰሰው ፊቱን አዞረበት።እኛ ዋጋ ያለን ሰዎች ነን።ባለን እና በጎደለን ነገር ራሣችንን አንለካ እግዚአብሔር እንደሚያየን፣እንደሚመለከተን ራሣችንን እንይ።

የእምነት ቃል

እኔ ሰው ያለኝን፣የሚለኝን፣የሚያስበኝን አይደለሁም።እኔ እግዚአብሔር ነህ ያለኝን ያንኑ ነኝ።እኔ ዋጋ ያለኝ ሰው ነኝ።
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
33 views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 22:36:47 እርሳስ ላጲስ አለው

መቼስ ካስተዋልናቸው ሁሉም ነገር ትምህርታችን ነው። ሁልጊዜ እርሳስ በምንገዛበት ጊዜ ከጭንቅላቱ ራሱን ሚያስተካክልበት ላጲስ አለው።የሁለቱ አገልግሎት ለየቅል ነው እርሳስ መሳልና መጻፍ፣ላጲስ ስህተቶችን ማጥፋት ግን ሁለቱም አንድ ቦታ ላይ ይፈላለጋሉ እርሱም ወረቀት ላይ ነው።ወረቀቱ እኛ እርሳሱ የምንሰማው፣የተቀረጸብን፣ያየነው ህይወታችን ነው።ላጲሱ ደግሞ እንደ ክርስቲያን መንፈስ ቅዱስ እንደ ሰውነታችን ደግሞ ህሊናችን ነው።እርሳስ የያዘ ሰው ላጲስ አልጠቀምም ቢል ስህተት የለብኝም ወይም በስህተቴ መቀጠል እፈልጋለሁ እያለ ነው።

ወገኖቼ ለእርሳስ ስህተት ላጲስ አለው።ለእኛ ኃጥያት፣ጥፋት፣በደል እግዚአብሔር ቃሉንና መንፈሱን፣ጸሎትንም ሰጥቶናል።እኛ ግን አንዳንድ ጊዜ ጸሎትን የትርፍ ጊዜ ስራ ሲለንም አላስፈላጊ መስሎ ይታየናል፤ቃሉንም በዚሁ መልኩ እናየዋለን።በእግዚአብሔር ፊት ተንበርክከን ጸጋና ምህረት እንዲበዛለን ሁልጊዜ ሳናቋርጥ በጌታ ፊት እንንበርከክ፣እንጸልይ።ጸሎት ጸጋና ምህረት ወደሚሰጠን አባት ምንቀርብበት መንገድ እንጂ የኤቲ ኤ ም ማሽን ወይም ስጋ ቤት አይደለም።ጸሎት አባትና ልጅ የሚቀራረቡበት ቦታ ነው።ኃጥያት ከብዶአችኋል ወደ አባታችን እና አምላካችን እግዚአብሔር ቅረቡ።እርሱ ይራራልናል፣ያስብልናል፣ጸጋንም ይሰጠናል ያበዛልናል።

ወደቃሉም ስንቀርብ ራሳችንን ነግሮን ከጥፋት ያድነናል።ችግሩ ከሚቀጣን ቃሉ ይቅጣን፣ችግሩ ከሚቆጣን ቃሉ ተቆጥቶ ያስተካክለን እንፍቀድለት ወገኖቼ።መንፈሱ ያነጻናል፣ያጥበናል እንደገና በህይወት ያኖረናል።

#ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
41 views19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 20:59:57 ራይት እና ኤክስ

ትምህርት በምንማርበት ጊዜ የማይጠፉ ሁለት ምልክቶች አሉ።እርሱም ትክክል ለሆነው ትክክል ነህ ተብሎ ራይት ይሰጠዋል ለተሳሳተው ደግሞ ስህተት ነህ ተብሎ ኤክስ ይሰጠዋል። አብዛኛውን ራይት አግኝተን አንድ ኤክስ ቢገባብን በጣም ነው ምንበሳጨው አሁን ለዚህች ጥያቄ ብሎ አስተማሪው ኤክስ ይሰጠኛል?እንላለን።ግን መምህሩ ትክክል ነው ትክክል ካልሆነ የተማሪውን ውጤት ያስቀምጣል።በዚህ ምክንያት 10 ማግኘት የነበረበት 9 ሲያገኝ 100 ሊያገኝ የነበረው 99 ያገኛል።

እግዚአብሔርም ሁልጊዜ በፊቱ ሲያየን እንዲሁ ኤክስ ብቻ ነበርን።ሰው 9ኙን ፈጽሞ አንዱን ባይፈጽም ህጉን እንዳልፈጸመ ነበር በእግዚአብሔር ፊት የሚታየው።የሰማዩ መምህር፣የሁሉ መርማሪ ደብተራችንን ሲያየው ምንም ትክክል የሆነው ነገር የለም አንድ እንኳ ጎበዝ የለም።ከላዩ እስከታቹ ስህተት አለበት።እናም ይሄንን ሲያይ ትክክል የሆነውን ኢየሱስን፣ጻድቅ የሆነውን ክርስቶስን ላከልን።በእርሱ ጽድቅ ጻድቆች፣በእርሱ ቅድስና ቅዱስ ሕዝብ፣የንጉስ ካህናት፣ለርስቱ የተለየ ወገን ሆንን(ሰማይ እንድንገባ እርዳታ(ስኮላርሺፕ)ሰጠን)። እናይ ያልቻልነውን እርሱ ቻለን።አሁን ተፈጽሟል ውጤታችን በርሱ ፊት ታይቷል እርሱም ኢየሱስ ነው።እግዚአብሔር የረካው በእርሱ በፈጸመው ስራ ብቻ ነው።

ግን ይሄን ውጤት፣ስለእኛ የሚታይልንን፣ስለእኛ ፍጹምን ስራ የሰራውን አጥብቀን ልንይዝ ያስፈልጋል።የእርሱ ውጤት ለእኛ ነው ሚቆጠረው።ህይወታችን የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል እንዳይሆንብን።የተሰጠን ህይወት ቀላል ህይወት አይደለም።በራሳችን እንደሆነ ልንቆጥር አይገባንም ሁሉ በጸጋው ነው።እግዚአብሔርን የካደ ሰው እንዳንሆን ልንጠነቀቅ ያስፈልጋል።ሰው ሰው የሰጠውን ስጦታ ሳይሸጠው በከበረ ቦታ ላይ ያስቀምጠዋል የእግዚአብሔርንስ ስጦታ ኢየሱስንስ?እንዴት ይዘነዋል።በእውነት ዛሬ እንወደዋለን እንዳልነው ሆነን ያገኘናል ወይስ ጥለነው?ለተሰጠን ህይወት እንጠንቀቅ በነጻ ቢሆንም ውድ ዋጋ ተከፍሎበታልና።
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
51 views17:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 08:06:49 ሽቶ ቢደፋም መልካም መዐዛ አለው

ሁልጊዜ መልካቸውን በሁኔታ ውስጥ ከማይቀይሩ ነገሮች አንዱ ሽቶነው።ሽቶ ልብስ ላይ ሲረጭም ሽቶ ነው፣ቢደፋም ሽቶ ነው።ሽቶ ሽቶነቱን ወይም መልካም መዐዛነቱን የማይለውጠው ስሪቱ ለመጥፎ ጠረን ስላልተሰራ ነው።ድንገት እንኳን እቃው ወድቆ ተሰብሮ እንኳን ብታገኙት ውስጡ ያለው መልካም ሽታ የሽቶው ብርጭቆ ስባሪ ላይ ይቀራል።ሽታው ግን አካባቢውን ያውደዋል።የሽቶን ሽታ ግን ሊቀይረው የሚችል አንድ ነገር አለ።እርሱም ከመጥፎ ሽታ ጋር በተደባለቀ ጊዜ ለምሳሌ ንጹህ ያልሆነ ነገር ላይ ሲረጭ ሽታው አንድ ላይ ተደባልቆ መልካሙን ሽታ ወደመጥፎ ይለውጠዋል።ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የሚለው "የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን ሽቱ ያገሙታል" የሚለው።

ይሄን ሁሉ ያልኩት ለአንድ ነገር ነው።እኛ ክርስቲያኖች ላይ የደረሰው ግፍ፣በደል፣ጭቆናም እና የመሳሰሉት መጥፎ ነገሮች እኛ ላይ ሲደርሱ የእኛ መልሳችን የተሰራንበትን ያንን ስሪት ማሳየት መሆን አለበት።የተሰራንበት ስሪት ፍቅር ነው።

ይሄንን ፍቅር በመጥፎም በመልካምም ጊዜ እንተግብረው የዛኔ ለክርስቶስ መልካም መዐዛ ያለው መስዋዕት ማቅረብ እንችላለን መንፈስ ቅዱስም በህይወታችን ለመስራት ቦታን ያገኛል።አልባስጥሮሷን የሰበረችው ሴት ስጸብረው የወጣው መልካም መዐዛ ነው።የሽቶው ውድነት ያለው ሽቶውን በያዘው እቃ ላይ አይደለም፣የሽቶው ውድነት ያለው ሽታው ላይ ነው።የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል።ግን ቅይጥ ማንነት አይገኝብን የዛኔ ለአለም የሚመች እንደ ኤሳው አይነት ማንነት ይኖረናል።ሃጥያትን በጸጋው ዙፋን ስር እንቁረጠው።ስር ሰዶ እንዳያድግብን።

የሞቱ ዝንቦች የተቀመመውን የዘይት ሽቱ ያገሙታል፤ እንዲሁም ትንሽ ስንፍና ጥበብንና ክብርን ያጠፋል።
መክብብ 10፡1
ወይም ስለ አንድ መብል በኵርነቱን እንደ ሸጠ እንደ ዔሳው ለዚህ ዓለም የሚመች ሰው እንዳይሆን ተጠንቀቁ።
ዕብ 12፡6
መልካሙን ሥራችሁን አይተው በሰማያት ያለውን አባታችሁን እንዲያከብሩ ብርሃናችሁ እንዲሁ በሰው ፊት ይብራ።
ማቴ 5፡16

#የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
78 views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 17:25:16
አገልጋይ እንደ ዶክተር
"We are saving life"

ዶክተር እንደ ተራው ወይም ባለሙያ እንዳልሆነው ማህበረሰብ በዘፈቀደ አይሄድም፣በዘፈቀደ አይወስንም።ምክንያቱም ሙያው ውሳኔን፣ትዕዛዝ መስጠትን፣እናም ከሰው ጋር መግባባትን በሙያዊ እና በተማረው መንገድ እንዲያደርግ ይፈልጋል።እንደፈለገ ግን መድሀኒት ቢያዝ፣በዘፈቀደ ነገሮችን ቢያደርግ ዶክተር የሰው ህይወትን ስለሆነ የሚሰራው ብዙ ነገር ያበላሻል፣ህይወትንም ያጠፋል።አገልጋይም እንዲሁ ነው የሚሰራው።አገልጋይ ለህይወቱ፣ለአነጋገሩ እንዲሁም ለሰዎች ስለሚያጎርሰው የህይወት ቃል መጠንቀቅ አለበት።

በእግዚአብሔር አለም ውስጥ "የትም ፍጪው ዱቄቱን ግን አምጪው" የሚል principle/መርህ አይሰራም።ዱቄቱ የሚመጣው ከየት ነው? ከሀሰተኞች ነው?፣ከዲያብሎስ ነው?፣ከእግዚአብሔር ድምጽ? ነው።ይሄ ራሱ መረጋገጥ አለበት።ስለዚህ አገልጋይ ለህይወቱ እና ለአገልግሎቱ መጠንቀቅ አለበት።የሚያደርገው ሁሉ ነገር በሰዎች እና በእግዚአብሔር ፊት ነውና መጠንቀቅ አለበት።በእግዚአብሔር ፊት ፍርድ በሰዎች ፊት ማሰናከል እና ህይወትን ማበላሸት አለና።ለምንወጋው መርፌ ለሰዎች ስለምንሰጠው መጠንቀቅ አለብን።በአዲስ ኪዳን ሁሉ ክርስቲያን ካህን ወይም አገልጋይ ነው።

የምንሰራው ከህይወት ቃል ተምረን ህይወትን ነው።ዶክተርም ህይወት ላይ እኛም ህይወትን ነው ምንሰራውና እንጠንቀቅ።

በእኔም ከሚያምኑ ከነዚህ ከታናናሾቹ አንዱን የሚያሰናክል ሁሉ፥ የወፍጮ ድንጋይ በአንገቱ ታስሮ ወደ ጥልቅ ባሕር መስጠም ይሻለው ነበር።
ማቴ 18፡6

#የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
85 views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 21:03:52 "ጠሪ አክባሪ ነው "

ብዙ ጊዜ በአገራችን የሚባል አስተማሪ አባባል ነው።ይሄንን አባባል ስናስብ ብዙ ነገሮች ወደ አዕምሯችን ይመጣሉ ምክንያቱም አንድ ዘመዳችን፣ወዳጃችን፣ጎረቤታችን ድግስ ወይም ዝግጅት ላይ ሲጠሩን ጠሪ አክባሪ ነው ብለን መሄድ ባንፈልግም ብንፈልግም እንሄዳለን።የምንሄደው ከጠሪው አክባሪነት የተነሳ ነው።

እግዚአብሔርም ለአገልግሎቱ የሾመን እና የጠራን ከእኛ ማንነት ተነስቶ ሳይሆን ከራሱ ማንነት እና ከፍቅሩ፣ከአክባሪነቱ፣ታማኝ አድርጎ ከመጥራቱ የተነሳ ነው።ጳውሎስ በዚህ ሸክላ ዕቃ ውስጥ የከበረ መዝገብ አለ ይላል።በዚህ ታማኝ ባልሆነና ተሰባሪ በሆነ ማንነት ውስጥ እግዚአብሔር ራሱን ታምኖና ታማኝ አድርጎ ስጦታውን፣ጸጋውን፣አገልግሎትን አስቀመጠ።ስለዚህ ለዚህ ጥሪ እንኑር በታማኝነት፣በሀቀኝነት፣በግልጸኝነት፣በአክባሪነት፣በፍቅር፣በትህትና ለተጠራንበት ጥሪ ያለመታከት፣ያለመሰላቸት እናገልግል።

ለአገልግሎቱ ሾሞኝ ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረኝ፥ ኃይል የሰጠኝን ክርስቶስ ኢየሱስን ጌታችንን አመሰግናለሁ፤
1ኛ ጢሞቴዎስ 1:12

ነገር ግን የኃይሉ ታላቅነት ከእግዚአብሔር እንጂ ከእኛ እንዳይሆን ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን፤
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:7
#ከታዘብኩት
#ሼር
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
81 viewsedited  18:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-26 13:46:46
የትኛውም ችግር ከክርስቶስ ፍቅር አይበልጥም።

ትዝታው ሳሙኤል
@ELOIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
69 views10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 17:13:38 ELOHIM LIFE CHANNEL(ELC) pinned a photo
14:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-25 09:15:19 ትዝብት ከማራቶን...........................

ጎይቶቶም ገ/ስላሴ ማራቶን ባሸነፈችበት የቅርቡ ውድድር ላይ የተፈጠረ የሚያስገርም ነገር ነበር።ምንድነው ሲባል ከኬንያዊቷ ኮሪር ጋር ለብቻዋ በቀረችበት ጊዜ ላይ ሩጫው ሊያልቅ 40 ኪሎ ሜትር ሲቀር ኬንያዊቷ ቅደሚ ቅደሚ ብላ እየነገረቻት ነበር የኢትዮጲያዋ አትሌት ጎይቶቶም ግን እግር በእግር ተከታትላ በመጨረሻው ጊዜ ላይ ኬንያዊቷ ስትደክምላት ግን ወደ ውድድሩ ማብቂያና ወደ ወርቁ ገባች፣አገኘች ሪከርድም ሰበረች።

ይሄ ምን ማለት ነው? ኬንያዊቷ ኢትዮጲያዊቷን ወዳት እንዳይመስላችሁ፣ወይም ስፖርታዊ ጨዋነት እንዳይመስላችሁ፣ወይም ማስቀደም ፈልጋ አይደለም።አንድ ነገር ነው እያደረገች የነበረው ውድድሩ ሊያልቅ ትንሽ ሲቀረው 40 ኪሎ ሜትር ላይ ከኬንያዋ አትሌት ቀድማ ብትወጣ ኖሮ ኢትዮጲያዊቷ ትሸነፍ ነበር ምክንያቱስ ሲባል ኢትዮጲያዊቷ ትደክማለች በዚህን ጊዜ ላይ ኬንያዊቷ ለመቅደም ይመቻታል፣ወርቁንም ታሸንፍ ነበር።ግን ኢትዮጲያዊቷ ይህንን ታክቲክ ስለምታውቀው እንደኬንያዊቷ ሃሳብ አልሆነችም፣አልፈለገችም፣አልሮጠችም።

ወገኖቼ ሰይጣን ወደ ኃጥያት ግቡ የሚላችሁ ውሸቱን ነው።ወደገደል ግቡ እያላችሁ ነው።ኃጥያትን አቅልሎ የሚያሳይ መንፈስ እና አሳብ ሁሉ ከጌታ ዘንድ አይደለም።ሊያደክማችሁ ነው በአጭር ሊያስቀራችሁ እንቢ በሉት።እግዚአብሔር ያሰበላችሁ ትልቅ ነገር አለ ከወርቅ የሚበልጥ እርሱ ጋር እንዳትደርሱ ነው።ስለዚህ የጠላትን አሳቦች እየተውን ወደ ትክክለኛው ፍጻሜ ድረሱ።ከእግዚአብሔር የሚለያችሁን አሳብ አራግፉት። ሰይጣን ውሸቱን ነው።ጥሩ የሚመስሉ ጎዳናዎች ግን መርዝ የሞላባቸው አሉና እንጠንቀቅ።

“እናንተ ከአባታችሁ ከዲያብሎስ ናችሁ የአባታችሁንም ምኞት ልታደርጉ ትወዳላችሁ። እርሱ ከመጀመሪያ ነፍሰ ገዳይ ነበረ፤ እውነትም በእርሱ ስለ ሌለ በእውነት አልቆመም። ሐሰትን ሲናገር ከራሱ ይናገራል፥ ሐሰተኛ የሐሰትም አባት ነውና።”
— ዮሐንስ 8፥44
#ketazebkut
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
81 views06:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 21:32:15
ሲምፕሰን

ክሮሎፍርምንና ሌሎች መድሀኒቶችን ያዘጋጀ ሳይንቲስት ነው ሲምፕሰን አንድ ጊዜ እንዲህ የሚል ጥያቄ ቀረበለት “እስከ አሁን ከተረዳኸው ነገር ሁሉ የሚበልጠው የትኛው ነው ?“ የሚል ጥያቄ ቀርቦለት እንዲህ ብሎ ነበር ”ከተረዳሁት ሁሉ የሚበልጠው ኃጥያተኛ መሆኔንና የምድነውም በእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን መገንዘቤን ነው“ (http://t.me/ELOHIMLIFECHANNEL)ብሏል።

ከእግዚአብሔር ጸጋና ምህረት ውጭ የምናወራው ምን አለን?የሆንነውን ያደረገን ጸጋው ነው።

#የጌታ ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።
#share
@ELOHIMLIFECHANNEL
@ELOHIMLIFEBOT
@Heliccv
119 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ